Site icon የሕይወት እንጀራ

“ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም፡፡”

በርካታ ክርስቲያኖች ለሙስሊም ወዳጆቻቸው የኢየሱስን ልዩ መሆንና መለኮታዊነት ለመናገር ካላቸው ከፍተኛ ቅንአት የተነሳ በታላቅ ድምፅ፣ ‹‹ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው!›› ለማለት ፈጣኖች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህን ለመቀበል ለሙስሊሞች ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ አያስተውሉም፡፡ እስልምና የአንድ አምላክ ብቻ ሃይማኖት ነው! ለሙስሊም ከአንዱ አምላክ በቀር ሌላ ማንኛውንም ነገር ሆነ ማንኛውንም አካል አምላክ ብሎ መጥራት ሃይማኖቱን እንደ መካድ እና ከፍተኛ ኃጢአት እንደ መሥራት ነው፡፡ ለዚህ ነው ቁርአን ኢየሱስ ከአንዱ እዉነተኛ አምላክ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ራሱን የቻለ ሁለተኛ አምላክ ነው የሚለውን አስተሳሰብ የሚቃወመው!

ሱረቱ አል-ማኢዳህ (5)፡72

They do blaspheme who say: “God is Christ the son of Mary.” But said Christ: “O Children of Israel! Worship God, my Lord and your Lord.” Whoever joins other goods with God-God will forbid him the Garden, and the Fire will be his abode.

ቀናተኛ ክርስቲያኖች፣ ‹‹ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው፤›› ሲሉ አንድ ሙስሊም ሲሰማ እንዲህ ብሎ ሊያስብ ይችላል፡- ‹‹ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ‹‹አባታችን ሆይ›› ብሎ ከፀለየ፣ ደግሞም ክርስቲያኖች እንደሚሉት እርሱ እግዚአብሔር ከሆነ፣ ክርስትና ቢያንስ ሰለ ሁለት አማልክት የሚያስተምር ሃይማኖት ነው!›› ብሎ ይደመድማል፡፡ ከዚህ የተነሳ ሙስሊሙ ለሌሎች የክርስትና ምስክርነቶች ፊቱን እንዲያዞር ይገደዳል፡፡ 

ክርስቲያኖች፣ ሁለት አማልክት ወይስ ኢየሱስ በማርቆስ 12፡29 ላይ እንደ ተናገረው አንድ አምላክ ብቻ እያመለኩ ስለመሆናቸው ራሳቸውን ሊጠይቁ ይገባል፡፡ ክርስቲያኖች፣ በሙስሊሞች ዘንድ ከአንድ በላይ አምላክ እንደ ሚያመልኩ ሊያስመስላቸው ለሚችሉ ማንኛውም የተሳሳቱ አገላለጾቻቸው ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባቸዋል፡፡ ይህ አካሄድ ለሙስሊሙ የእግዚአብሔርን ርህራሄ በመግለፅ የዓለም አዳኝ ሆኖ የመጣውን፣ የወደቀውን የሰው ዘር ሊቤዥና ከኃጢአት እርግማን ሊዋጅ የተገለጠውን ኢየሱስን በማስተዋወቅ ሂደት ውስጥ ቀላል የሆነውን የወንጌል መልዕክት እንዳይሰማ የእንቅፋት ድንጋይ ይሆንበታል፡፡ 

ምናልባትም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ በግልፅና በቀላሉ ‹‹ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር ያልተጠቀመው፣ ‹‹አምላካችን እግዚአብሔር አንድ ነው፡፡›› የሚለውን እውነታ ብዥታ ውስጥ ላለመክተት ይሆናል፡፡ ከዚህ ይልቅ ቅዱሳት መጻሕፍት የኢየሱስን መለኮታዊነት የምንረዳበትን የሚከተሉትን ሌሎች አገላለፆች ይጠቀማሉ፡- 

እነዚህ ማስረጃዎች ራሱን በኢየሱስ በኩል በሙላት ስለ ገለጠው ስለ አንዱ እግዚአብሔር ይተርካሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አቀራረብና የቃላት አጠቃቀም ብንዋስ፣ በአንዱ አምላክ በእግዚአብሔር እንደምናምን ለማስረገጥ እንችላለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለሙስሊም ወዳጆቻችን መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ቁርአን ኢየሱስን የእግዚአብሔር ቃል ብሎ እንደ ሚጠራው በማስታወስ በኢየሱስ መለኮታዊነት ማመናችንንም ጭምር ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ይህ ጠቃሚ ነጥብ ነው፡፡ ምክንያቱም በርካታ ሙስሊሞች የእግዚአብሔር ቃል የማይፈጠርና ዘላለማዊ እንደሆነ፣ መለኮታዊ ባሕሪም እንዳለው ይስማማሉና! ይህንን መንገድ በመጠቀም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ሕያው ቃል ስለ መሆኑ እና ስለ መለኮታዊ ባሕሪው መናገር እንችላለን!

በኢየሱስ ባሕሪ ዙሪያ ያለውን ታላቅ ምስጢር ለሙስሊም ወዳጅህ የማስረዳት ግዴታ እንዳለብህ አይሰማህ፡፡ የሚበሰብስ ሥጋን ከተሸከምን ከኛ መካከል ማን ነው መለኮታዊውን ጉዳይ በሙላት ሊገነዘብ የሚችል? ቀላልና ግልፅ የሆነውን የወንጌል መልዕክት አለማወሳሰብህን እርግጠኛ ሁን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ በእኛ ላይ ያልጫነውን ከፍተኛ የሥነ-መለኮታዊ መረዳቶችን በሙስሊሙ ወዳጅህ ላይ ለመጫን አትታገል፡፡ በአዲስ ኪዳን በየትኛውም ስፍራ ላይ ድኅነትን/መዳንን ለማግኘት የኢየሱስን ማንነት በሙላት መገንዘብ እንዳለብን የሚያሳስብ ክፍል አናገኝም፡፡ ድኅነት/መዳን የኢየሱስን መለኮታዊነት በሙላት በመገንዘባችን እና ማብራራት በመቻላችን ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ዘር ሁሉ የተላከ አዳኝ እንደሆነ ከልብ በማመን እና በእርሱም በኩል ብቻ የኃጢአት ቤዛነትንና ይቅርታ እንደሚገኝ በመቀበል ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህ ነው የምሥራቹ ዜና!

Exit mobile version