“ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የሚለው መጽሐፍ በዶክተር ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር ተጽፎ በተክሉ መንገሻ የተተረጎመ እና በላፕስሊ ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ አስቀድመን ስለ እነዚህ ቅዱሳን ትጋት እና የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል ለከፈሉት ዋጋ ምስጋናችን እናቀርባለን፡፡ በመቀጠል ጽሁፉን ኮፒ እና ፕሪንት በማድረግ ለግልም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማዋል የተፈቀደ ቢሆንም ያለአሳታሚው ፈቃድ ጽሁፉን መለወጥም ሆነ ለሽያጭ ማዋል ግን ፈጽሞ በሕግ የተከለከለ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ መልካም ጥናት!
መግቢያ
ይህ መጽሐፍ የሥነ-መለኮት ሥልታዊ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ ያሟላል በሚል አሳብ የተጻፈ አይደለም። መጠነኛና እጅግ አስፈላጊ በሆኑ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች ላይ በማተኮር፥ ጥልቅ የሆነ የሥነ-መለኮት ትምህርት የሌላቸውን አማኞች ለመርዳት የተጻፈ ነው። “ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጭብጦች” የመገለጦች መልህቅ ነው። አስተዋይ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በአዲስ ኪዳን ጥልቅና መሠረታዊ ትምህርት መደነቁ እርግጥ ነው (ማቴ. 7፡28፤ ዮሐ. 7፡16-17፤ ሐዋ. 2፡42፤ ሮሜ 6፡ 17፤ ኤፌ. 4፡14፤ 1ኛ ጢሞ. 1፡3፤ 4፡6፥ 16፤ 6፡1፤ 2ኛ ጢሞ. 3፡ 10፥ 16፤ 4፡2-3፤ 2ኛ ዮሐ. 9-10)። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ የእምነት ትምህርት በሚገባ የማይረዳ አማኝ ኤፌሶን 4፡ 14 ውስጥ “እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን..” የሚለውን እውነት ይደርስበታል። ጠንካራ ናቸው የሚባሉ አማኞች በአሁኑ ጊዜ በሀሰት ትምህርት መወሰዳቸው ለዚህ ማረጋገጫ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የመለኮት ዓላማ፥ “ቃሉን ስበክ፤ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፥ ምከርም፤ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሥበት ዘመን ይመጣልና” በሚለው ቃል መሠረት የጌታ ተከታይ የሆነ ሁሉ ዝግጁ እንዲሆን ነው። በዚህ መጽሐፍ የተካተቱ ምዕራፎች በሙሉ በክብሩና በጸጋው ባለጠጋ ለሆነ ጌታ ክብር ይሆን ዘንድ በጸሎት በመታገዝ ቀርበዋል። የጌታ ልጆች የሆኑ አማኞችም “ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርትን ለመናገር ብቃት እንዲኖራቸው ያግዝ ዘንድም ይህ መጽሐፍ ተዘጋጀ። ሉዊስ ስፔሪ ቼፈር
የትምሕርቶቹ ዝርዝር
ሀ. ውስጣዊ ማረጋገጫ
ለ. ውጫዊ ማረጋገጫ
ሀ. የእስትንፋሰእግዚአብሔር ንድፈ-አሳቦች
ለ. የክርስቶስ ምስክርነት
ሐ. ስለ-እስትንፋሰ እግዚአብሔር ጠቃሚ ምንባቦች (ጥቅሶች)
መ. ተጨማሪ ማብራሪያዎች
ሀ. ኢየሱስ ክርስቶስ በመልእክትነት
ለ. የሰው ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ
ሐ. የመጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ
ሀ. የመለኮታዊ መገለጥ ዓይነቶች
ለ. ልዩ መገለጥ
ሐ. ትርጉም ወይም ፍቺ
ሀ. በእግዚአብሔር ሕልውና ማመን
ለ. የሥላሴ መለኮታዊ አንድነት
ሐ. የእግዚአብሔር ስሞች
መ. የእግዚአብሔር ባሕርያት
ሠ. የእግዚአብሔር ልዕልና
ረ. የእግዚአብሔር ድንጋጌ
ሀ. አብ የመጀመሪያው አካል
ለ. ለፍጥረት ሁሉ አባትነት
ሐ. በቅርብ ግንኙነት የሚመሠረት አባትነት
መ. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት
ሠ. በክርስቶስ የሚያምን ሁሉ አባት
7 እግዚአብሔር ወልድ፡- መለኮታዊነቱና ዘላለማዊነቱ
ሀ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነትና መለኮትነት ቀጥተኛ ገለጣ
ለ. የእግዚአብሔርን ልጅ ዘላለማዊነት የሚያመለክቱ ሁኔታዎች
ሀ. ክርስቶስ ሰው የመሆኑ እውነት
ለ. የተሠማው ምክንያቶች
ሀ. የልጁ ሞት የሚያከናውናቸው ነገሮች
ለ. የወልድን ሞት አስመልክቶ ያለ የግንዛቤ ስህተት
ሀ. ትንሣኤ በብሉይ ኪዳን
ለ. ክርስቶስ ስለ ራሱ ትንሣኤ የተናገራቸው ትንቢቶች
ሐ. የክርስቶስ ትንሣኤ ማረጋገጫዎች መ. የክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያቶች
ሠ. የክርስቶስ ትንሣኤ ጠቃሚነት
11 እግዚአብሔር ወልድ፡- ዕርገቱና የክህነት አገልግሎቱ
ሀ. የክርስቶስ ዕርገት እውነትነት
ለ. ክርስቶስ ሰማይ የመግባቱ ማረጋገጫ
ሐ. የዕርገቱ ትርጉም
መ. ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በሰማይ የሚያከናውነው ተግባር
ሠ. ክርስቶስ በአሁኑ ጊዜ በምድር የሚያከናውነው ተግባር
ሀ. ያልተፈጸመ ትንቢት
ለ. ስላመነጠቅ የተነገሩ ትንቢቶች
ሐ. ክርስቶስ ለቅዱሳኑ መምጣቱ እና ከቅዱሳኑ
መምጣቱ ሲነጻጸሩ
13 እግዚአብሔር ወልድከቅዱሳኑ ጋር ስለ መምጣቱ
ሀ. ከክርስቶስ ዳግም ምፅአት የሚቀድሙ ዐበይት ሁኔታዎች
ለ. ከዳግም ምጽእቱ ጋር የሚዛመዱ ወሳኝ እውነታዎች
ሐ. ዳግም ምጽአቱ ከመነጠቅ ጋር ሲነጻጸር
ሀ. የአካልነቱ አስፈላጊነት
ለ. ቅዱሳት መጽሐፍ ውስጥ የተገለጠው የመንፈስ ቅዱስ አካልነት
ሐ. መንፈስ ቅዱስ የአብ አካል እንደመሆኑ ከአብና ከወልድ ጋር እኩል ነው
ሀ. መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን
ለ. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ዘመን
ሐ. በጰንጠቆስጤ ዕለት የመንፈስ ቅዱስ መውረድ
16 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የዳግም ልደት ሥራ
ሀ. የዳግም ልደት ትርጉም
ለ. በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወለድ
ሐ. በዳግም ልደት የተገኘ የዘላለም ሕይወት
መ. የዳግም ልደት ውጤት
17 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- በሰው ውስጥ ማደሩና ማተሙ
ሀ. የዚህ ዘመን አዲስ ገጽታው
ለ. የመንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ ውስጥ ማደር
ሐ. መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ስለማደሩ በሚሰጠው አስተምህሮ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች
መ. የመንፈስ ቅዱስ በሰው ውስጥ ማደር ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር ሲነጻጸር
ሠ. በመንፈስ ቅዱስ መታተም
18 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የማጥመቅ ተግባሩ
ሀ. የመንፈስ ቅዱስ ማጥመቅ ትርጉም
ለ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከጳንጠቆስጤ ዕለት በፊት
ሐ. በዚህ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተጠምቀዋል
መ. በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ ወደ ክርስቶስ አካል መጨመር
ሠ. መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ ውስጥ ማጥመቁ
ረ. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ከመንፈሳዊ ልምምድ ጋር ሲዛመድ
19 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- የመሙላት ተግባሩ
ሀ. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ሲብራራ
ለ. ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች
ሐ. ሰመንፈስ የመሞሳት ውጤቶች
ሀ. የሥፍረ-ዘመናት ትርጉም
ለ. የንጽህና ሥፍረ-ዘመን የነጻነት ዘመን
ሐ. የሕሊና ሥፍረ-ዘመን የሰው የመምረጥና የመወሰን ዘመን
መ. የሰው መንግሥት ሥፍረ ዘመን የኖህ ጋር የተደረገ ቃል ኪዳን
ሠ. የተስፋ ሥፍረ-ዘመን ከአብርሃም ጋር የተደረገ ቃል ኪዳን ረ. የሕግ ሥፍረ-ዘመን
ሰ. የጸጋ ሥፍረ-ዘመን
ሸ. የእግዚአብሔር መንግሥት ሥፍረ-ዘመን
ሀ. ሥነ-መለኮታዊዎቹ ቃል ኪዳኖች
ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ኪዳኖች
ሀ. የመላእክት አፈጣጠር
ለ. ያልወደቁት መላእክት
ሐ. የወደቁ መላእክት
መ. የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት
ሀ. የሰይጣን ማንነት
ለ. የሰይጣን ኃይል
ሀ. ሰይጣንን በሚመለከት የሚቀርቡ ስህተተኛ ፅንሰ-ሐሳቦች
ለ. የሰይጣን ሥራ
ሐ. የሰይጣን ፍጻሜ
ሀ. የሰው ፍጡርነት
ለ. የሰው አፈጣጠር
ሀ. አዳም ከውድቀት በፊት
ለ. አዳም ከወደቀ በኋላ
ሐ. የአዳም ኃጢያት በሰው ዘር ላይ ያመጣው ውጤት
ሀ. ሰው ስለ ኃጢያት ያለው አስተሳሰብ
ለ. ሰለ ኃጢያት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ
ሀ. የድነት ትርጉም
ለ. ድነት እግዚአብሔር ለኃጢያት እንዳዘጋጀው መድኃኒት
ሐ. ድነት ከመስቀሉ በፊትና በኋላ
መ. የድነት ሦስቱ ጊዜያት
ሠ. ድነት በክርስቶስ የተፈጸመ ሥራ
ረ. ድነት የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ
ሰ. ድነት፥ ከዳነ ሰው ኃጢያት ጋር ያለው ግንኙነት
ሸ. በእምነት ብቻ የሚገኝ ድነት
ሀ. ከኃጢያት ነጻ መሆን ለክርስቲያኖች ብቻ
ለ. የኃጢያት ችግር በክርስቲያን ሕይወት
ሐ. ሕግ እንደ ሕይወት መመሪያነት
መ. ጸጋ እንደ ሕይወት መመሪያ
ሠ. ብቸኛው የድል መንገድ.
ረ. ድል በመንፈስ ቅዱስ
ሀ. እግዚአብሔር ጳድቅ ነው
ለ. የሰው ጽድቅ
ሐ. የተላሰፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ.
መ. በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የተሰጠ ጽድቅ
ሀ. የትክክለኛ አተረጓጎም አስፈላጊነት
ለ. የቅድስና ትርጉም
ሐ. የቅድስና መንገድ
መ. ሦስት ዓበይት የቅድስና ገጽታዎች
ሀ. የፅንሰ-አሳቡ አስፈላጊነት
ለ. የድነትን ምንነት መረዳት
ሐ. የክርስቲያናዊ ልምምድ ምስክርነት
መ. የመጽሐፍ ቅዱስን የተስፋ ቃሎች እውነተኛነት መቀበል
ሀ. የአርሚኒያውያን የድነት ዋስትና አመለካከት
ለ. አብ በደኅንነት ያለው ሥራ
ሐ. የወልድ ሥራ
መ. የመንፈስ ቅዱስ ሥራ
ሀ. የምርጫ ውሳኔ
ለ. የመለኮታዊ ምርጫ እውነትነት
ሐ. የምርጫ አስተምህሮ መረጃ
ሀ. ቤተ ክርስቲያን-የዚህ ዘመን የእግዚአብሔር ዓላማ
ለ. ቤተ ክርስቲያን-የአዲስ ኪዳን መገለጥ
ሐ. አይሁድ፥ አሕዛብና ቤተ ክርስቲያን
መ. ከአይሁድና ከአሕዛብ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን
ሠ. የቤተ ክርስቲያን አባላት
ሀ. ዓለም ውስጥ የአሁኑ መለኮታዊ ዓላማ
ለ. የቤተ ክርስቲያን አመሠራረት
ሐ. የአማኙ ተልዕኮ
ሀ. አገልግሎቷ ለእግዚአብሔር
ለ. የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለሰው
ሐ. የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ አጠቃቀሟ
38 ቤተ ክርስቲያን፡- አምልኮዋ በጸሎትና በምስጋና
ሀ. ጸሎት ከክርስቶስ መምጣት በፊት
ለ. የመንግስትህ ትምጣ ጸሎት
ሐ. የክርስቶስ ጸሎት
መ. ጸሎት በጻጸጋ ግንኙነት ሥር
ሠ. የምስጋና ጸሎት
ሀ. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር
ለ. የቤተ ክርስቲያኝ ስልጣን
ሐ. የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች
40 ቤተ ክርስቲያን፡- የክርስቶስ አካልና ሙሽራ፥ የሚጠብቃት ሽልማቷ
ሀ. ሰባቱ የክርስቶስና የቤተ ክርስቲያኑ ተምሳሌቶች
ለ. ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ አካል
ሐ. ክርስቶስ እንደ ሙሽራ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽሪት
መ. ሙሽራይቱ አጊጣና ተሸልማ
ሀ. ሰንበት በብሉይ ኪዳን
ለ. ሰንበት በአሁኑ የቤተ ክርስቲያን ዘመን
ሐ. ሰንበት በሚመጣው ዘመን
መ. የክርስቶስ ትንሣኤና የሳምንቱ መጀመሪያ ዕለት
ሠ. አዲሱ ፍጥረት
ረ. የጌታ ቀን (እሁድ)
ሀ. አሕዛብ በእግዚአብሔር ዕቅድ
ለ. አሕዛብን የሚመለከቱ ቀደምት ትንቢቶች
ሐ. የአሕዛብ ዘመናት
ሀ. እስራኤል ከሥፍረ ዘመናት ጋር ያላት ግንኙነት
ለ. እስራኤል ከቃል ኪዳኖች አንጻር
ሐ. የእስራኤል ታሪክ በብሉይ ኪዳን
መ. የእስራኤል ታሪክና የተፈጻመ ትንቢት
ሠ. ስለ እስራኤል 490 ዓመታት የነገረ ትንቢት
ረ. ስለ መሢሑ ምጽዓት የተነገረ ትንቢት
ሰ. ስለ እስራኤል በመጨረሻ መበተንና መሰብሰብ የተነገረ ትንቢት
ሸ. ስለ መጨረሻው ዘመን የተነገረ ትንቢት
ቀ. ስለ መሐዊው መንግሥትና የጌታ ቀን የተነገረ ትንቢት
44 ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብለው የሚከናወኑ ሁኔታዎች
ሀ. የአሁኑ ዘመን ዓበይት ሁኔታዎች
ለ. ከመነጠቅ በኋላ የሚኖረው የዝግጅት ጊዜ
ሐ. የሠላም ጊዜ.
መ. የስደት ጊዜ
ሀ. ታላቁ መከራ ከአጠቃላይ መከራ ጋር ሲነጻጸር
ለ. ስለ ታላቁ መከራ የብሉይ ኪዳን እስተምህሮ
ሐ. የፍዳው ዘመን በአዲስ ኪዳን አስተምህሮ
ሀ. የዳግም ምጽአቱ ጠቀሜታ
ለ. ስለ ዳግም ምጽአት የተነገሩ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች.
ሐ. የክርስቶስ ዳግም ምጽአት በአዲስ ኪዳን ጎለጫ መሠረት
ሀ. የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ
ለ. የኢየሩሳሌሙ የቅዱሳን ትንሣኤ
ሐ. የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ
መ. የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ትንሣኤ
ሠ. የታላቁ መከራ ወቅት ቅዱሳን ትንሣኤ
ረ. የሺህ ዓመቱ ቅዱሳን ትንሣኤ
ሰ. የኃጢያተኞች ትንሣኤ
ሀ. ከሞት የተነሣ እሥራኤላውያንና አሕዛብ ፍርድ
ለ. በሕይወት የሚቆዩ እሥራኤላውያን ፍርድ
ሐ. በሕይወት የሚኖሩ አሕዛብ ፍርድ
ሀ. የእግዚአብሔር መንግሥት ፅንሰ-አሳብ
ለ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት-የእግዚአብሔር አገዛዝ በምድር ላይ
ሐ. በሺህ ዓመቱ መንግሥት ክርስቶስ እንደ ንጉሠ ነገሥት
መ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት ዓበይት ገጽታዎች
ሠ. በሺህ ዓመቱ መንግሥት የእሥራኤል ልዩ ሥፍራ
ረ. የሺህ ዓመቱ መንግሥት መንፈሳዊ በረከቶች
50 በሰይጣንና በወደቁ መላእክት ላይ የሚሰጠው ፍርድ
ሀ. በክርስቶስ መስቀል አማካይነት በሰይጣን ላይ የተሰጠ ፍርድ
ለ. የሰይጣን ከሰማይ መጣል
ሐ, የሰይጣን ታሥሮ ወደ ጥልቁ መጣል
መ. የሰይጣን የመጨረሻ ፍርድ
ሀ. የታላቁ ነጭ ዙፋን የመጨረሻ ፍርድ
ለ. የሰማይና የምድር ውድመት
ሐ. ድነት ያላገኙ ሙታን ትንሣኤ
መ. የሰዎችን ሥራዎች የሚገልጡ መጻሕፍት ተከፈቱ
ሀ. አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር
ለ. የእዲሲቱ ኢየሩሳሌም አጠቃላይ ገለጣ
ሐ. የአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ራእይ