በውኑ አምላክ ከባድ ኃጢአቶችን ይቅር ይል ይሆን? ነፍሰ ገዳዩንስ ይቅር ይል ይሆን?

ብዙ ሰዎች፣ እግዚአብሔር እንደ ውሸት፣ ቁጣና ከፉ ሀሳብ የመሳሰሉ “ትንንሽ” ኃጢአቶችን ይቅር እንደሚል ያምኑና  ነገር ግን እንደ ግድያ እና ምንዝርና ያሉትን “ትላልቅ” ኃጢአቶች ይቅር እንደሚል ለማመን ይቸገራሉ። ይህ እውነት አይደለም። እግዚአብሔር ይቅር የማይለው “ትልቅ” ኃጢያት የለም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሲሞት የመላው ዓለምን የኃጢአት ዋጋ ለመክፈል ሞቷል (1ኛ ዮሐንስ 2፡2)። አንድ ሰው ድነትን ለማግኘት በኢየሱስ ክርስቶስ ሲያምን፣ ለሁሉም ኃጥያቶቹ ይቅርታን ያገኛል። ይህም ይቅርታ ያለፈ፣ የአሁን፣ እና የወደፊት “ትልቅም ሆነ ትንሽ” ኃጥያቶቹን ያካትታል። ኢየሱስ የሞተው ለኃጢአቶቻችን ሁሉ ቅጣት ለመቀበል ነው። እናም ኃጢአተኛው ሰው ይቅር ከተባለ ዘንዳ ከሁሉም ኃጢአቶች ይቅርታን ያገኛል ማለት ነው (ቆላስያስ 1፡14; ሐዋርያት ሥራ 10:43)።

ሁላችንም በኃጢያታችን ምክንያት በደለኞች ነን (ሮሜ 3፡23)። በበደላችን ምክንያት ደግሞ ዘላለማዊ ቅጣት መቀበል ይገባናል (ሮሜ 6 23)። ነገር ግን፣ መድሃኒታችን ኢየሱስ ቅጣታችንን ተቀብሎ ስለ እኛ ሞቷል (ሮሜ 5፡8)። ማንም ሰው ምንም ዓይነት ኃጢአት ቢሠራም እነኩዋን ለመዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ፣ የኃጥያት የቅርታን ያገኛል (ሮሜ 6 23; ዮሐንስ 3:16)። ነፍሰ ገዳይ ወይም አመንዝራ ከውሸታሙ ሰው ይልቅ ለክፉ ተግባሩ (ህጋዊ፣ ማሀበራዊ፣ ወዘተ) ከባድ ችግሮች ሊደርስበት ይችላል። ነገር ግን ለድነቱ በክርስቶስ እስከታመነ ድረስ ለኃጥያቶቹ ሁሉ እንደማንኛውም ኃጢአተኛ ፍጹምና ዘላለማዊ ይቅርታን ያገኛል።

የኃጢያት ይቅርታን ለማግኘት  ወሳኙ ነገር የኃጢአቱ አይነትና መጠን ሳይሆን ለኃጢያት ስርየት በክርስቶስ የተከፈለው የመስዋዕት መጠን ነው። ኃጢያት የሌለበት የእግዚአብሔር በግ (አኢየሱስ ክርስቶስ) የአለሙን ሁሉ ኃጢያት ሊያስወግድ የሚችል ከሆነ፣ ይህ መስዋዕት ሊከድነው የማይችለው የኃጢአት አይነትም ሆነ መጠን ሊኖር አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ “ተፈጸመ” ብሎ ሲናገር፣ የተሟላ ስርየት ተደረገ፤ እግዚአብሔር በመስዋዕቱ ረካ፤ ፍጹም ምህረት ተገኘ፤ ሰላም ተፈጠረ፤ ከኃጢአት ሁሉ መቤዠት ተገኘ ማለቱ ነው። የክርስቶስ መስዋዕት እውን እና የተሟላ ነው። ይህ መስዋዕት የጎደለው ነገር ስለሌለ በላዩ ላይ ማንም ምንም ነገር ሊጨመርበት አይችልም፤ ሊቀለበስውም እንዲሁ።

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።

Leave a Reply

%d bloggers like this: