ዮሐንስ 9፡31 ‘‘እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን’’ ይላል። ከዚህ በተጨማሪ፣ ‘‘እግዚአብሔር፣ ኢ-አማኒው ኢየሱስን ለመቀበል ሲል የሚያደርገውን የንስሃ ፀሎት ብቻ ነው ሰምቶ የሚመልሰው’’ የሚል የተለመድ አባባል አለ። በእነዚህ ምክንያቶች አንዳንዶች እግዚአብሔር፣ የማያምኑ ሰዎችን ፀሎት ሰምቶ እንደማይመልስ ያምናሉ። የዮሐንስ 9፡31 የአውድ ትርጉም ግን እግዚአብሔር በማያምን ሰው እጅ ተአምራትን አያደርግም የሚል ነው። በ 1ዮሐንስ 5፡14-15 መሰረት፣ እግዚአብሔር ፀሎትን የሚመልሰው በፈቃዱ ላይ በመንተራስ እንደሆነ እናነባለን። በሌላ አነጋገር፣ ፈቃዱ ከሆነ ይመልሳል፤ ካልሆነ አይመልስም ማለት ነው። ይህ መርህ በማያምኑት ላይ ሳይቀር የሚሰራ ነው። የማያምን ሰው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሰረት ቢፀልይ እግዚአብሔር በፈቃዱ መሰረት ይመልስለታል ማለት ነው።
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ እግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎችን ፀሎት ሰምቶ ሲመልስ ያስነብቡናል። በዛ በሚሉት በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ኢ-አማኒያኑ ሲፀልዩ እናነባለን። በአንድ ወይም በሁለቱ ታሪኮች ውስጥ ደግሞ እግዚአብሔር የኢ-አማኒያኑን የልብ ጩኸት ሲመልስ እናያለን። በእርግጥ በታሪኮቹ ውስጥ ጩኸቶቹ ወደ እግዚአብሔር ስለመቅረባቸው እርግጠኛ የሚያደርገን ነገር አናገኝም። በሌሎቹ ታሪኮች ውስጥ ደግሞ የኢ-አማኒያኑ ፀሎት ከንስሃ ጋር የተቀላቀለ መሆኑን እናነባለን። በተቀሩት ታሪኮች ውስጥ ደግሞ ኢ-አማኒያኑ ለምድራዊ በረከት ፀልየው ሲቀበሉ እናነባል። በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ ሁሉ እግዚአብሔር ከርህራሄው ወይም ከኢ-አማኒያኑ ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ወይም ከአስደናቂ መታመናቸው በመነሳት ፀሎታቸውን ሲመልስ እናነባለን። ከዚህ በታች በኢ-አማኒያኑ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ የተወሰኑ ታሪኮች ቀርበዋል፡-
የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔር ሊያመጣባቸው ካለው ቅጣት ለመዳን ፀለዩ (ዮናስ 3፡5-10)። እግዚአብሔር ፀሎታቸውን ሰማ፤ ሊያመጣባቸው ከነበረው ቅጣትም እጁን ከለከለ።
አጋር ስል ልጇ እስማኤል፣ ወደ እግዚአብሔርን ፀለየች (ዘፍጥረት 21፡14-19)። እግዚአብሔርም የአጋርን ፀሎት ሰማ፤ እስማኤልን በብዙ ባረከው።
አክዓብ፣ ነቢዩ ኤሊያስ ባመጣለት ትንቢት ምክንያት ጾመ፣ አዘነ። እግዚአብሔርም ሊመጣበት ያለውን ጥፋት በእርሱ ዘመን አላመጣበትም (1ነገስት 21፡17-29 በተለይ ከቁጥር 27-29 ይመልከቱ)።
ከጢሮስ እና ሲዶና አገር የሆነች አንዲት ሴት ኢየሱስ ልጇን ከርኩስ መንፈስ ቁራኛ እንዲፈውስላት ጠየቀች (ማርቆስ 7፡24-30)። ኢየሱስም ርኩስ መንፈሱን ከልጅቷ እንዲወጣ አዘዘው። ፈወሳትም።
በሐዋሪያት ስራ 10 ላይ ታሪኩን የምናነበው የሮም መቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ደግመሞ መልካም ሰው እንደነበረ እና ፀሎቱ በእግዚአብሔር እንደተሰማለት እናያለን። ይህ ሰው አዘውትሮ ወደ እግዚአብሔር ይፀልይ ነበር (ሐዋሪያት ስራ 10፡2)። እግዚአብሔርም ለዚህ ሰው ሐዋሪያው ጴጥሮስን ላከለት።
እግዚአብሔር ላመኑም ይሁን ላላመኑ ሁሉ የሚሰራ በኤርሚያስ 29፡13 ላይ እንደተዘገበው አይነት ተስፋ ሰጥቷል፣ ‘‘እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ’’። እንደ ቆርኔሌዎስ (ሐዋሪያት ስራ 10፡1-6) ያሉ ሰዎች የዚህ ተስፋ ተጠቃሚ ናቸው። ያም ሆኖ፣ የፀሎቱ ሃሳቦቹ በሚገኙባቸው አውዶች መሰረት፣ ክርስቲያኖችን (አማኞችን) ብቻ የሚመለከቱ በርካታ ተስፋዎች እንዳሉ ልንዘነጋ አይገባም። ለአብነት፣ ኢየሱስን እንደ ቤዛቸው በመቀበል የዳኑ ክርስቲያኖች፣ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሁሉ ከእግዚአብሔር እርዳታን ለማግኘት ወደ ፀጋው ዙፋን በድፍረት የመቅረብ መብት ተሰጥቷቸዋል (ዕብራውያን 4፡14-16)። አንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምንም ፀሎታችን እንደሚሰማና የጠየቅነውን እንደምናገኝ ቃል ተገብቶልናል (1ዮሐንስ 5፡14-15)። ከእነዚህ በተጨማሪ፣ ክርስቲያኖችን በሚመለከት ስለፀሎታቸው የተሰጣቸው በርካታ ተስፋዎች አሉ (ማቴዎስ 21፡22፤ ዮሐንስ 14፡13፣ 15፡7)።
እግዚአብሔር የኢ-አማኒያንን ፀሎት የማይሰማበት ሁኔታ እንዳለ ሁሉ፣ ከቸርነቱና ከምሕረቱ የተነሳ በሕይወታቸው ጣልቃ በመግባት ለፀሎታቸው ምላሽ የሚሰጥበ ወቅቶችም እንዳሉ ሊዘነጋ አይገባም።