ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ማለት ምን ማለት ነው?

ስለ ፋሲካ ብዙ ሰዎች የተለያየ ትርጉምና ምልከታ አላቸው። ይህ ክብረ በአል ከማንም በላይ ከአይሁድ ባህል ጋር የጠበቀ ግንኙነት ይኑረው እንጂ፣ ለክርስቲያኖች ልዩ ስፍራ አለው። ለመሆኑ ፋሲካ ምንድን ነው? በፋሲካ ምን ሆነ? የፋሲካ በአል ጥላነቱ ለማን ነው? አማናዊው ፋሲካ ማን ነው? በፋሲካ ለሰው ልጆች ምን ሆነ? ይህን ሃሳብ ለመረዳት ከሰው ልጆች ውድቀት መነሳት ግድ ስለሚል ከዛ እንጀምርና ምስጢሩን አንመርምር፡-

  1. ከዚህ በታች በቀረቡት ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ፣ የሰው ልጅ በውድቀት ወቅት በእግዚአብሔር ፊት ምን ይመስል እንደነበረ እና ከዚህ ውድቀቱ እግዚአብሔር ሲታደገው ደግሞ ምን እንደሆነለት ይናገራል፡፡

ሮሜ. 3፡10-12 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፡- ፃድቅ የለም፣ አንድስ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፣ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ የለም፡፡

ሮሜ. 3፡10-12 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ፡- ፃድቅ የለም፣ አንድስ እንኳ፤ አስተዋይ የለም፣ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፡፡ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፣ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ የለም፡፡

ኤፌ. 2፡1-9 በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው፣ በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው ኑሮ፣ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፣ በፊት ተመላለሳችሁባቸው፡፡ በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ የስጋችንንና የልቦናችንን ፈቃድ እያደረግን በስጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን፤ እንደ ሌሎችም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን፤ ነገር ግን ግን እግዚአብሔር በምህረቱ ባለጠጋ ስለ ሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ህይወትን ሰጠን፡፡ በፀጋ ድናችኋል፤ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የፀጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሳን፤ በክርስቶስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡ ፀጋው በእምነት አድኖአችኃልና፣ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም፡፡

ኤፌ. 2፡12 ከእስራኤል መንግስት ርቃችሁ፣ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፣ በዚህም አለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ፡፡

ሮሜ. 5፡6-10 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቷልና፡፡ ስለ ፃድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ገና ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከፀደቅን በእርሱ ከቁጣው እንድናለን፡፡ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኃላ በህይወቱ እንድናለን፡፡

ኤፌ. 4፡17-19 እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ፣ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ፣ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፣ ከእግዚያብሔርም ሕይወት ራቁ፤ ደንዝዘውም በመመኘት ርኩሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ፡፡

  1. ክርስቶስ ስለእኛ በመሞት ቤዛ ሆነን የሚለውን ቁም ነገር ለመጨበጥ አሁንም ከቀድሞ አባትና እናታችን (አዳም እና ሔዋን) ስህተት መነሳት ይኖርብናል።

ሀ. የእግዚአብሔር ጸጋ፣ አዳምና ሔዋን ባለመታዘት እግዚአብሔርን በበደሉበት ወቅት ተገልጧል፡፡ በጥላ መልክ የተገለጠው ይህ ጸጋ ኋላ ላይ ለሚመጣው አማናዊው ጸጋ አመልካች ነበር። ለመሆኑ በአዳም ውድቀት ወቅት የተገለጠው ይህ ጥላ (ምሳሌ) ምን ነበር?

ዘፍጥረት 2፡15-17 ‘‘እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በኤደን ገነት አኖረው ፡፡እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው ፡-ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ & ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና፡፡”

ዘፍጥረት 3፡

፡6-7 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፣ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፣ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ። የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ።

፡8-12 እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፣ ተሸሸግሁም። እግዚአብሔርም አለው። ዕራቁትህን እንደ ሆንህ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ በላህን? አዳምም አለ። ከእኔ ጋር እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት እርስዋ ከዛፉ ሰጠችኝና በላሁ።

፡13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፡- ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው? አላት ፡፡ ሴቲቱም አለች ፡- እባብ አሳተኝና በላሁ፡፡”

፡20 ”አዳምም ለሚስቱ ስም አወጣ የሕያዋን እናት ናትና፡፡”

፡21-24 እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፣ አለበሳቸውም። እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፣ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፣ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፣ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ። አዳምንም አስወጣው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።

አዳምና ሔዋን አንድ ሕግ ተሰጣቸው፤ እርሱንም አልታዘዙም፡፡ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ሞከሩ (ይህ የበለስ ቅጠሎች ሰፍተው በመልበሳቸው ተመስሏል፡፡) እርስ በእርሳቸው ተካሰሱ፡፡ ለአመጻቸውም የሚገባቸውን አገኙ፤ ይህም ፍትህ ይባላል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር የማይገባቸውን ነገር ሰጣቸው፤ ይህ ደግሞ ፀጋ ይባላል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ያዘጋጀው እንስሳ በእነርሱ ፈንታ በመታረዱ ተመስሏል፡፡ ምንም በደል የሌለበት እንስሳ በእነርሱ ኃጢያት ምክንያት ታርዷል፡፡ የዚህ እንስሳ መስዋዕት፣ ኋላ ለሚመጣውና ለሰው ልጆች ሁሉ ኃጢያት ራሱን ለመስቀል ሞት አሳልፎ ለሚሰጠው ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌው ነበር፡፡

ለ. ፋሲካ፣ ክርስቶስ በእኛ ምትክ/ቤዛ መሆን ምሳሌ ነው።

ዘጸአት 12፡1 በግብፅ ምድር እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፡-

፡12-13 እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፣ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም።

፡21-22 ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው። በየቤታችሁ ጠቦት ምረጡ፣ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱት። ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፣ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፣ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።

፡23 እግዚአብሔር ግብፃውያንን ይመታ ዘንድ ያልፋልና፤ ደሙንም በጉበኑና በሁለቱ መቃኖች ላይ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር በደጁ ላይ ያልፋል፣ አጥፊውም ይመታችሁ ዘንድ ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አይተውም

፡24-27 ለእናንተ ለልጆቻችሁም ለዘላለም ሥርዓት አድርጋችሁ ይህችን ነገር ጠብቁ። እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወደ ሚሰጣችሁ አገር በገባችሁ ጊዜ ይህን አምልኮ ጠብቁት። እንዲህም ይሆናል፤ ልጆቻችሁ። ይህ አምልኮ ለእናንተ ምንድር ነው? ባሉአችሁ ጊዜ፣ እናንተ። በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፣ ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ይህች ናት ትሉአቸዋላችሁ።

፡29-30 እንዲህም ሆነ፤ እኩል ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር፣ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በግዞት እስካሉት እስከ ምርኮኞቹ በኵር ድረስ፣ የግብፃውያንን በግብፅ ምድር የተገኘውን በኵር ሁሉ፣ የእንስሳውንም በኵሮች ሁሉ መታ። ፈርዖንም ባሪያዎቹም ሁሉ ግብፃውያንም ሁሉ በሌሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌለበት ቤት አልነበረምና በግብፅ ምድር ታላቅ ልቅሶ ሆነ።

ዮሐ. 1፡29 በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ ፡- እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ፡፡

1ቆሮ. 5፡7 “ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንዲያቦካ አታውቁምን እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፡፡

እስራኤላውያን በግብፅ የባርነት ቀንበር ስር ነበሩ፡፡ ጠቦት በእነርሱ ምትክ ተገደለ፡፡ የጠቦቱ ደም ባለበት ቤት ላይ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍርድ ይከለከል ነበር፡፡ ጌታ ደሙን በመቃኖቹ ላይ እና በጉበኑ ላይ ሲመለከት ፍርድ ከዚያ ቤት ላይ ይርቅ ነበር፡፡

በሃጢአታችን ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተናል (ሮሜ 5፡10) ጠላቶቹም ሆነናል። በዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ጥለኞች ነን። ጠላቶቾም ስለሆንን ከእግዚአብሔር ቁጣ ስር ወድቀናል (ኤፌሶን 2፡3)። ከአዳም ዘር የሆነ ሁሉ ሃጢአትን ስለሰራ (ሮሜ. 3፡10-12፤ ቲቶ 3፡3-8) ከዚህ ቁጣ ስር ነው። ከዚህ ከእግዚአብሔር ቁጣ ለማምለጥ ያለን አማራጭ አንድ ብቻ ነው (1ተሰሎንቄ 1፡9-10፤ 1ተሰሎንቄ 1፡5፡9)። የዮሐንስ ወንጌል 3፥36 ደግሞ እንዲህ ይላል፣ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ‘‘…በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን’’ (ሮሜ 5፡9)። ከዚህ ከእግዚአብሔር ቁጣ ለመዳን በበጉ ደም መከለል ይኖርብናል። ይህ፣ የዓለምን ኃጢአት ሁሉ የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ ወይም ፋሲካችን ደግሞ ኢየሱስ ነው (ዮሐንስ 1፡29)። ይህ በግ ለእኛ ታርዶልናል (1ቆሮ. 5፡7)። ደሙንም እኛን ከእግዚአብሔር ቁጣና ፍረድ ለማዳን ሲል አፍስሶልናል። በዚህ ደም የተሸሸገ እና የታመነ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ አብቅቶ ወዳጅ ይሆናል። በዚህ በግ ያልታመነና ያልተደገፈ ሁሉ ደግሞ የእግዚአብሔር ፍርድ ይጠብቀዋል (ዮሐንስ 3፡18)።

ሐ. ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በእኛ ፈንታ›› መሞት ወይም ቤዛ መሆን፣ እግዚአብሔር ለእኛ ያዘጋጀው ብቸኛ የድነት መንገድ ነው፡፡

ኢሳ. 53፡4-6 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።

2ቆሮ. 5፡21 እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ፅድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢያት ያላወቀውን እርሱን ስለእኛ ኃጢአት አደረገው፡፡

ገላ. 3፡13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተፅፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከህግ እርግማን ዋጀን፡፡

1ጴጥ. 3፡18 ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ አመጸኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክኒያት ሞቶአልና፣ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፣

  1. የዳንኩት ስለሚገባኝ ሳይሆን (NOT BECAUSE I AM DESERVING) ከፍቅሩ የተነሳ ነው፡፡

ቲቶ 3፡3-7 እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፣ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፣ የምንጣላ፣ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፣ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፣ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።

ዮሐ. 6፡37 አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፡፡ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡

ዮሐ. 6፡44 የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደእኔ ሊመጣ የሚችል የለም፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ፡፡

ሮሜ. 3፡10-12 ፃድቅ የለም አንድስ እንኳ አስተዋይም የለም እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም ሁሉ ተሳስተዋል በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድስ እንኳ

ሮሜ. 4፡4-8 ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ፣ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል። እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቆጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል። ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።

ኤፌ. 1፡3-8 በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፣ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፣ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፣ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን።

ቲቶ 3፡3-8 እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፣ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፣ የምንጣላ፣ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፣ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፣ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው። ቃሉ የታመነ ነው። …

  1. በ ‹‹ክርስትና›› እና በ ‹‹ሐይማኖት›› መካከል ያለው ልዩነት ምንድ ነው?

‹‹ሐይማኖት›› በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖርህ አንተ ራስህ አንድ ነገር ማድረግ ትችላለህ ብሎ ሲያስተምር፣ ‹‹ክርስትና›› ግን በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖርህ የሚያደርግህ ክርስቶስ በአንተ ፈንታ ያደረገልህ የመስቀል ስራ ብቻ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡

ዮሐ. 14፡6 እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም

ሐዋ. 4፡12 መዳን በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና

መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትዎ ጌታ በማድረግ ቀሪው ዘመንዎን ለመኖር ወስነው ከሆነ፣ ይህንን ሊንክ በመጫን ስምዎንና የኢ-ሜይል አድናሻዎን ይላኩልንና፣ ለመንፈሳዊ ሕይወት እድገትዎ የሚቻለንን ሁሉ እገዛ እናደርግሎታለን።

 

Leave a Reply

%d bloggers like this: