መጽሐፍ ቅዱስ- ከስህተት የጸዳ፣ እንከን የሌለው፣ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት የጻፉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ- ከስህተት የጸዳ፣ እንከን የሌለው፣ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በመነዳት የጻፉት የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

የጥናቱ ማውጫ
ሀ1. መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ይናገራል
ሀ2. መጽሐፍ ቅዱስ ከስሕተት የጸዳ ነው
ሀ3. መጽሐፍ ቅዱስ በማናቸውም ርዕስ ጉዳዮች ላይ ስሕተት የለበትም
ሀ4. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስት ያሉ ቃላት በተመረጡ ሰዎች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ናቸው
ሀ5. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አስተምህሮዎን ለምን አጠናለሁ፣ ለምንስ እታዘዛቸዋለሁ?
ሀ6. የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን እንዴት ልማራቸው እችላለሁ?

1. መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ፣ ስለ ራሱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ይናገራል

“የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።’’ (2ጢሞ 3፡16)

“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” የሚለው የተጻፈውን የእግዚአብሔርን ቃል ያመለክታል፡፡ “ቅሱሳት መጻሕፍት ሁሉ” የሚለው ብሉይና አዲስ ኪዳንን ያመለክታል፡፡

ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን ቅዱሳት መጻሕፍት ብሎታል (ሉቃስ 24፡27፣ 44፣ 45፤ ዮሐ 5፡39፣ 46፣ 47) ጴጥሮስ የጳውሎስን ደብዳቤዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ብሏቸዋል (2ጴጥ 3፡15፡16) መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ፣ በዚህ ቃል ላይ የሚጨምርም ሆነ የሚቀንስ የእግዚአብሔር ፍርድ በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡ “ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤ ’’ (ራዕ 22፡18፣ 19)

2. መጽሐፍ ቅዱስ ከስህተት የጸዳ ነው

የእግዚአብሔር መንፈስ “ቅዱሳን የእግዚአብሔር ሰዎችን” (2ጴጥ 1፡21) በማንጻት፣ እንዲጽፉት በማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ሰፍረው የሚገኙት ቅዱሳት መጻሕፍት ያለስህተት ተጠብቀው እንዲቆዩ አድርጓል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ መለኮታዊ በሆነ ምሪት የእነዚህን ቅዱሳት መጽሐፎች ፀሃፊዎች በመምራት፣ እግዚአብሔር ማለት የፈለገው እንዲሰፍር እና የመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች ሁሉ ከስህተት የጸዱ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃላት በእግዚአብሔር ከስህተት እንዲጸዱ ተደርገዋል (ኢሳ 40፡8፤ ማቴ 24፡35) ሐ) ብሉይ ኪዳን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣ ነው፣ ስለዚህም ስህተት የለበትም (ኢያሱ 1፡8፤ 2ነገ 22፡8፣ 11፣ 13) መ) ያለምንም ልዩነት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስህተት ሊገኝ አይችልም ክርስቶስ እንዲህ አለ፣ “መጽሐፉ ሊሻር አይችልም – ’’ (ዮሐ 10፡35)፡፡

ኢየሱስ በእብራይስጥ፣ አራማይክና ግሪክ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉን የቋንቋዎቹን ምቶች፣ የድምጽ ጥብቀትና መላላት ሕግጋቶች ሳይቀር ያለስህተት በመጠቀም ሰብኳል፡፡ እነዚህ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ በመጀመሪያ የተጻፈባቸው ቋንቋዎች ናቸው፡፡ “ከሕግ እንዲት የውጣ (የእብራይስጥ ትንሳሿ ፊደል) ወይም አንዲት ነጥብ (በፊደል ላይ በመቀመጥ መጥበቅና መላላቱን የምታመለክት ጭረት) ከቶ አታልፍም፣ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ” (ማቴ 5፡18)፡፡

3. መጽሐፍ ቅዱስ በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስህተት የለበትም

ኢየሱስ፣ ብሉይ ኪዳን ከስህተት የጸዳ መሆኑን አረጋግጧል። በብሉይ ኪዳን ተአምራዊ ታሪኮችን በመጥቀስ፤ ቅዱሳት መጻሕፍቱ እዉነተኛ፣ ትክክለኛ፣ ከስህተት የጸዱ እና በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ ነገር እንደሌለባቸው አረጋግጧል፡፡

ዘፍጥረት የፍጥረት ታሪክ መዝገብ እንደሆነ አረጋግጧል (ማቴ 19፡4)
አዳምና ሔዋን (ማቴ 19፡4-6፤ ዘፍ 1፡26፣ 27፣ 2፡7፣ 18)
ቃየልና አቤል (ማቴ 23፡35፤ ዕብ 11፡4፤ ዘፍ 4፡1-15)
ሰይጣን (ሉቃስ 11፡18፤ ሕዝ 28፡11-19)
ኖህ (ማቴ 24፡37፣ 38፤ ዘፍ 6፡1-14)
ዮናስ (ማቴ 12፡39፣ 40፤ ዮናስ 1፡7)
የሎጥ ሚስት (ሉቃስ 17፡32፤ ዘፍ 19፡26)

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፣ እያንዳንዱ ቃል እውነት እንደሆነ፣ ሙሉ በሙሉም ሊታመን እንደሚገባ ኢየሱስ አሳይቶናል፡፡

ብሉይ ኪዳን በማናቸውም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከስህተት የጸዳ መሆኑን ክርስቶስና ሐዋሪያት አረጋግጠውልናል።

አንዳንድ ዘመነኛ የሃይማኖት ሊቃውንት ግን በሚከተሉት መጻሕፍት ላይ ጥርጣሪያቸውን አሳይተዋል፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ምላሽ ይሆንዎ ዘንድ እነሆ፡-

ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋዊያን፣ ዘኁልቁ፣ ዘዳግም- እነዚህ መጻሕፍት በሙሴ የተጻፉ ሲሆኑ ኢየሱስ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ ዮሐ 5፡46፣ 47 ይመልከቱ፡፡ በእነዚህ ሊቃውንት በሰፊው ለጥቃት ከተጋለጠው የዘዳግም መጽሐፍ ኢየሱስ ክርስቶስ – በ ማቴ 4፡4፣ 7-10 እንደተገለጸው ሰይጣንን ድል ለመንሳት ጠቅሷል (ዘዳ 6፡16 እና 10፡20)፡፡ እነዚህ መጻሕፍት “… የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ … የእግዚአብሔር ቃል …” (ኤፌ 6፡17) ባይሆኑ ኖሮ፣ ኢየሱስ ጠቅሶ ይጠቀማቸው ነበርን? ፈጽሞ! ሊጠቀምባቸው አይችልም! እንግዲያው እነዚህ መጽሐፍት የእግዚአብሔር ቃል ናቸው፡፡

ኢሳያስ – አዲስ ኪዳን ውስጥ ሃያ-አንድ ጊዜያት ያህል ተጠቅሷል፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን ያገናዝቡ፡- ማቴ 15፡7-9 እና ኢሳ 29፡13፤ ማቴ 3፡3 እና ኢሳ 40፡3፤ ሐዋ 8፡28-33 እና ኢሳ 53፡7፣ 8። እነዚህ ሦስት ጥቅሶች ከኢሳያስ መጽሐፍ የተለያዩ ሦስት ክፍሎች የተውጣጡ ናቸው፡፡

ዳንኤል – ኢየሱስ፣ ዳንኤል በእግዚአብሔር መንፈስ የተነዳ የመጪው ዘመን ጠቋሚ ነቢይ እንደሆነ ጠቅሷል (ማቴ 24፡15፤ ማር 13፡14)፡፡

ዮናስ – ኢየሱስ፣ የዮናስን መጽሐፍ ትክክለኛነትን በማቴ 12፡40፣ 41 ላይ አረጋግጧል፡፡

4. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ቃላት በተመረጡ ሰዎች አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጡ ናቸው፡፡

ሀ) “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያላባቸው ናቸው፤ …” (2ጢሞ 3፡16) “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው” የሚለው የግሪክ አቻው theopneustos ሲሆን የቃል በቃል ፍቺውም “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ደራሲ ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከቅዱሳት ሰዎች አንደበትና ብዕር የወጡት ቃላት “የእግዚአብሔር እስትንፋስ” ውጤቶች ናቸው (2ጴጥ 1፡21)፡፡

ለ) ዳዊት፣ ጽሑፎቹ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተገኙ እንደሆነ ሲያረጋግጥ እናያለን፡፡ ዳዊት በርካቶቹን የዳዊት መዝሙር ክፍል የጻፈ ሰው ነው፡፡ ዳዊት እንዲህ ይላል፡- “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ … (2ሳሙ 23፡2፤ በተጨማሪ 1ዜና 28፡11፣ 12 ይመልከቱ)፡፡

5. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አስተምህሮዎችን ለምን አጠናለሁ፣ ለምንስ እታዘዛቸዋለሁ?

ሀ) ለመንፈሳዊ እድገት ቅዱሳት መጻሕፍት የመንፈሳዊ እድገታችን መንፈሳዊ ምግቦች ናቸው (ኤር 15፡16፤ ሕዝ 3፡1-3፤ 1ጴጥ 2፡2፤ 1ቆላ 3፡1፣ 2፤ ዕብ 5፡12-14)

ለ) ከኀጢአት ለመጠበቅ የእግዚአብሔር ቃል ከኀጢአት እንዲርቁ ያደርጎታል፡፡ በአንጻሩ ኀጢአት ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ያርቆታል (መዝ 119፡ 9፣ 11፣ 133)

ሐ) ጤናንና ፈውስን ለመለማመድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛትን መታዘዝ፣ አካላዊ ጤናና የፈውስ ውጤት አላቸው (ዘዳ 15፡26፤ መዝ 107፡20፤ 119፡50)፡፡

መ) ለመበልጠግ ኢያሱ መጽሐፍ ቅዱስ የያዘ የመጀመሪያ ሰው ነበር፡፡ ይህንን መጽሐፍ በማንበብና በመታዘዝ በረከትና ብልጥግና እንደሚያገኝ ቃል ኪዳን ተቀበለ (ኢያሱ 1፡8)፡፡ ፍሪያማና ውጤታማ ለመሆን የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን ያሰላስሉ (መዝ 1፡1-3)፡፡

ሠ) በእግዚአብሔር መንገድ ለመጓዝና አለማስተዋልን ለመበቀል ቅዱሳት መጻሕፍት የመንገዳችን መብራቶ ናቸው (መዝ 119፡104፣ 105)፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት አለማስተዋልን ይገፋሉ (መዝ 119፡130)፡፡

6. የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን እንዴት ልማራቸው እችላለሁ?

(ዮሐ 20፡31)፡፡ (ዮሐ 5፡39)፡፡ በየምዕራፉና በእየገጾቹ ላይ ኢየሱስን ይፈልጉ፡፡ (ሉቃስ 24፡44)፡፡

ሀ) በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ይማራሉ

“ቃሉን ከመመገቦ” በፊት በጾሎት በእግዚአብሔር ፊት ይሁኑ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲያስተምርዎና ማስታልዎን እንዲቀባ ይጠይቁ (ዮሐ 14፡26፤ 1ቆሮ 2፡12-14፤ 1ዮሐ 2፡27)፡፡ ከአይኖችዎና ልብዎ ላይ መጋረጃ እንዲነሳና ብሉይ ኪዳንን መረዳት እንዲችሉ ይጸልዩ (2ቆሮ 3፡14-16)፡፡ መንፈስ ቅዱስ ማስተዋልዎን ይከፍትልዎ ዘንድ ይጸልዩ (ሉቃስ 24፡25፣ 27፣ 44፣ 45)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያነቡበት ወቅት “…የጥበብና የመገለጥ መንፈስ…” በልብዎና በአእምርዎ ላይ እንዲሆን ይጸልዩ (ኤፌ 1፡ 17፣ 18)፡፡

ለ) በመደበኛ ንባብ ይማራሉ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ቢያንስ 30 ደቂቃ ይፀልዩ፡፡

በየዕለቱ አንድ የመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ቢያነቡ መዝሙረ ዳዊትን በአመት ሁለት ጊዜ ማንበብ ይችላሉ ማለት ነው፡፡ ከምሳሌ መጽሐፍ በየዕለቱ አንድ ምዕራፍ ቢያነቡ ይህን መጽሐፍ በወር አንድ ጊዜ ያነባሉ ማለት ነው፡፡ ከብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሦስት ገጾችን በየዕለቱ ቢያነቡ፣ በአመት ውስጥ ይህን መጽሐፍ አንብበው መጨረስ ይችላሉ፡፡ ከአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ሦስት ገጾችን በየዕለቱ ቢያነቡ፣ በአመት ውስጥ ሦስት ጊዜ ይህንን መጽሐፍ ያነባሉ ማለት ነው፡፡ በሚያነቡበት ወቅት፣ እርሳስ ወይም ሀይላይተር በመጠቀም እርሶ ስላሉበት ሁኔታ የሚናገሩ ክፍሎችን ወይም የባረኮት ጥቅስ ስር ያስምሩ፡፡

ሐ) በተቀናጀ አጠናን ይማራሉ

በእዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማጣቀሻ /Topical concordance/ ስር ያሉትን ዝርዝሮች በየዕለቱ ለ25 ደቂቃዎች ያጥኑ፡፡ ትምህርቶቹን በሚያጠኑበት ወቅት የሚያገኙዋቸውን እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያንብቡ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስዎ ላይ ከጥቅሶቹ ትይዩ ወይም ግርጌ የግልዎን ማስታወሻዎች ያስፍሩ፡፡ ከ 55 ደቂቃ ንባብዎ ውስጥ አንድ ጥቅስ በመምረጥ ጥቅሱን ያጥኑ፡፡ 5 ደቂቃ በመውሰድ ጥቅሱን እና የጥቅሱን ምዕራፍና ቁጥር ለማስታወስ ይሞክሩ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስዎን ለማጥናት የወሰዱት ይህ 60 ደቂቃ (1 ሰዓት)፣ ሰይጣን ቀኑን ሙሉ እንዳይቋቋምዎ ይረዳዎታል፡፡

መ) የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ማጠቃለያ

ሕግ በዋናነት በመጀመሪያዎቹ አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ ይገኛል- ከዘፍጥረት አንስቶ እስከ ዘዳግም፡፡ እነዚህን መጻሕፍት በአግባቡ መረዳት በቀጣይ መጽሐፎች ውስጥ ያሉ ቁም ነገሮችን ለመጨበጥ ወሳኝ ነው፡፡

ታሪክ በብሉይ ኪዳን ከኢያሱ መጽሐፍ እስከ አስቴር መጽሐፍ የሚገኝ ሲሆን፣ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከማቴዎስ እስከ የሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍ ድረስ ይገኛል፡፡ እነዚህ የታሪክ መጻሕፍት በጌታ ኢየሱስ የቤዛነት ሥራ ላይ የሚያጠነጥኑ ዘገባዎች ናቸው፡፡ ቤዛነት፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ ሃሳብ ወይም ጭብጥ አሳብ ነው፡፡

ሥነ ግጥም በዋናነት ከኢዮብ መጽሐፍ እስከ ሰለሞን ዝማሪዎች (ማኃልየ፡ ማኃልይ ዘሰሎሞን) ይዘልቃል፡፡ በርካታዎቹ የትንቢት መጽሐፍት ምዕራፎችም በእብራይስጥ ግጥም የተጻፉ ናቸው፡፡

ትንቢት በብሉይ ኪዳን ከኢሳያስ ጀምሮ እስከ ሚልኪያስ መጽሐፍ ባሉት ስር ሰፍሮ የምናገኘው ሲሆን በአዲስ ኪዳን ደግሞ የዮሐንስ ራዕይና ከፊል የወንጌል መጻሕፍት ለስለመጪው ዘመን ይናገራሉ፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ስለእግዚአብሔር መጻኢ አላማና የተቤዡ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ስለሚያደርጉት ንግሥና ያስተምራሉ (ራዕ 20፡4፤ 1ቆላ 6፡2)፡፡

የኑሮ መርህዎች በዋናነት በአዲስ ኪዳን እና በጥበብ መጻሕፍት ማለትም፣ በምሳሌ እና በመክብብ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡

ሠ) በመጽሐፍ ቅዱስ የተካተቱ ርእሰ ጉዳዮች አጭር ማጠቃለያ

የሰማያት መፈጠር፡ ዘፍ 1፡1

የሰይጣን አመጽና ውጥንቅጥ ውጤቱ፡ ዘፍ 1፡2

የምድር አፈጣጠር፡ ዘፍ 1 እና 2

የሰው ልጅ አመጽና ማህበራዊ ቀውስ፡ ዘፍ 3

የጥፋት ውሃ፡ ዘፍ 6-10

በኖህ በኩል የሆነ ተሃድሶ፡ ዘፍ 9-10

የባቢሎን ግንብ አመጽ፡ ዘፍ 11፡1-9

የአሕዛብ ቋንቋ መከፋፈል (መደበላለቅ)፡ ዘፍ 11፡8-9

የአብርሃም፣ ይስሃቅ፣ ያዕቆብና ዮሴፍ መመረጥ፡ ዘፍ 12-36

ዮሴፍ በግብጽ ለባርነት መሸጥ፡ ዘፍ 37-50

እስራኤላዊያን በሙሉ በግብጽ ባርነት መውደቅ፡ ዘፍ ዘጸ 1-6

እግዚአብሔር ሙሴንና እስራኤል እንደ ሕዝብ መምረጡ፡ ዘጸአት

የማይታዘዘው ሕዝብ፡ የነቢያት መጽሐፎች

የእስራኤል ሕዝቡ መበታተን፡ ኤር፣ ሕዝ፣ ዳን

ቤዛነት (የጸጋ ልዩ ዘመን)፡ አዲስ ኪዳን

የኢየሱስ ክርስቶስ በሰው አምሳል ወደምድር መምጣት፡ ነቢያቶችና ወንጌል

የኢየሱስ በሰዎች መሰቀል፡ የወንጌል መጻሕፍት

የኢየሱስ ከሞት መነሳት፡ ወንጌል

ጴንጤቆስጤ፣ የቤተክርስቴያን መመረጥ፡ የሐዋሪያት ሥራ

ቤተክርስቲያን በአለምና በሰይጣን መሰደዷ፡ የሐዋሪያት ሥራና ራዕይ

የሙታን ትንሳኤና የፍርድ ቀን፡ መልዕክታትና ራዕይ

የበጎና የክፉ የመጨራሻ መለያ፡ ራዕይ

ሰማይ፣ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፣ አዲስ ሰማያትና ምድር፡ ራዕይ

ገሀነም እና ዘላለማዊ ስቃይ፡ ራዕይ

Leave a Reply

%d bloggers like this: