ኢየሱስ – ፍጹም ሰውና ፍጹም እግዚአብሔር

ሀ) ልደቱ

– ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ – ማቴ 11

– ከሴት የተወለደ – ገላ 4፡4፤ ሉቃስ 1፡29-33

– በቤተልሔም የተወለደ – ማቴ 2፡1

– ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ – 1ጢሞ 2፡5

– የሰው ልጅ ተባለ – ማቴ 12፡8፤ 16፡13፤ 25፡31፤ ዮሐ 3፡14፤ 8፡28፤ 13፡31

– በሥጋና በደም ሰውነታችንን ተካፈለ – ዕብ 2፡4፤ 1ዮሐ 4፡፡14

– መንፈስ፣ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ ይመሰክራል – 1ዮሐ 4፡2-3

ለ) በአካሉ ተወሰነ

– ደከመ – ዮሐ 4፡6-8

– ሲደክመው ተኛ – ማር 4፡38

– በጥበብና በቁመት በተፈጥሮ ሕግ አደገ – ሉቃስ 2፡52

– በተወጋው ጎኑ ደምና ውሃ ወጣው – ዮሐ 19፡32-34

– ተራበ – ማቴ 4፡1-11፤ ማር 11፡12

– አዘነ – ማቴ 26፡38፤ ዮሐ 11፡35

– ተቆጣ – ማር 10፡14

ሐ) የሰውና የመለኮት ባሕሪያት አንድ መሆን (መዋሀድ)

– የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተገልጧል – ቆላ 1፡14 – ሁለቱም ተፈጥሮዎች በአንድ ምንባብ ስር ተጠቅሰዋል ቃል-ሥጋ ሆነ – ዮሐ 1፡14

የዳዊት ዘር – የእግዚአብሔ ልጅ – ሮሜ 1፡3-4

የእግዚአብሔር ልጅ – በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ – ሮሜ 8፡3

ክርስቶ በሥጋ መጣ – ከሁሉ በላይ አምላክ ነው – ሮሜ 9፡5

ከሴት የተወለደው – የእግዚአብሔር ልጅ – ገላ 4፡4

ምሳሌ ተገኘ – ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው – ፊል 2፡7፣ 11

– ሰዋዊ መለያ ባሕሪይ ከ መለኮታዊ ስያሜ ጋር

ድንግል ወንድ ልጅን ትወልዳለች – “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ይባላል – ማቴ 1፡23 ፤ ኢሳ 7፡14

– የኢየሱስ ደም “የእግዚአብሔር ደም” ተብሏል – ሐዋ 20፡28

– እግዚአብሔር እንደመንፈስነቱ “ደም” የለውም፡፡ የኢየሱስ “ደም” እንደ “እግዚአብሔር ደም” መቆጠሩ ኢየሱስና እግዚአብሔር ያላቸውን መለኮታዊ አንድነት ይገልጣል፡፡

– ተሰቀለ – የክብር ጌታ – 1ቆሮ 2፡8

– መለኮታዊ መለያ ባሕሪይ ከ ሰዋዊ ስያሜ ጋር

ከሰማይ መጣ – የሰው ልጅ – ዮሐ 3፡13

የሰው ልጅ – ወደ ሰማይ አረገ – ዮሐ 6፡62

ክርስቶ በሥጋ መጣ – ከሁሉ በላይ አምላክ ነው – ሮሜ 9፡5

Leave a Reply

%d bloggers like this: