እግዚአብሔር ራሱን ለሰዎች እንዴት ይገልጣል?

ሀ) በተአምራት

ተአምራቶቹ እግዚአብሔርን ያከብራሉ – ዘኅ 14፡22

አንዳንዶች እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል – ዮሐ 2፡23

ነገር ግን አንዳንዶች ላያምኑ ይችላሉ – ዮሐ 12፡37

እውነተኛ ተአምራት

የሚነድ ቁጥቋጦ – ዘፍ 3

በግብጻዊያን ላይ ወረርሽኝ – ዘዳ 4፡12

የቀይ ባሕር መከፈል – ዘፍ 14

የዮርዳኖስ ወንዝን መሻገር – ኢያሱ 3

ኤሊያስ – 1ነገ 17-18፤ 2ነገ 1

ኢሳያይስ – 2ነገ 20

ኤልሳዕ – 2ነገ 2፡-6፡፤ 13

የኢየሱስ ተአምራት – ክፍል ለ9 ይመልከቱ

የደቀ መዛሙርት ተአምራት – ክፍል F9፣ ረ11 ይመልከቱ

አንዳንድ ተአምራት በሰይጣን ሊደረጉ ይችላሉ – ዘዳ 13፡1-3፤ ዘጻ 7፡9-12፤ ረዕ 13፡14፤ 16፡14፤ 19፡20

ለ) በፍርድ

ፈርኦን – ዘጸ 4፡12

ናቡከደነጾር – ዳን 4፡28-37

ብልጣሶር – ዳን 5

አናንያና ሰጲራ – ሐዋ 5፡1-11

ሄሮድስ – ሐዋ 12፡22-23

የክፉው ሰራተኞች በሙሉ – ራዕ 20፡10፣ 14-15

ሐ) በሕልምና ራዕዮች

አንዳንድ ሕልሞችና ራዕዮች እግዚአብሔርንና የእርሱን አላማዎች ይገልጣሉ፡፡ – የሚከተሉት መጻሕፍት እግዚአብሔርን የሚገልጡ በርካታ ሕልሞችና ራዕዮችን አካተዋል – ሕዝቅኤል፤ ዳንኤል፤ ዘካሪያስ፤ ዓሞጽ፤ ናሆም፤ የሐዋሪያት ሥራ፤ ራዕይ

ሕልሞችና ራዕዮች በእግዚአብሔር ሊፈቱ ይገባቸዋል

ለዮሴፍ – ዘፍ 41፡15-16

የዮሐንስ ራዕዮች ራዕ 1፡20፤ 7፡13-14

ለዳንኤል – ዳን 2፡27-28

የጴጥሮስ ራዕይ – ሐዋ 10፡11-15፣ 34-35

ሕልሞችን፣ ራዕዮችንና ትንቢቶችን ለመመዘን ከዚህ በታች ያሉትን የእግዚአብሔር መስፈርቶች አይዘንጉ፡-

ሁሉን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይፈትሹ – መዝ 138፡2፤ ምሳሌ 30፡5-6

መንፈስን ሁሉ አይመኑ – 1ዮሐ 4፡1-3

ሁሉንም ነገሮች ይመካከሩባቸው – ምሳሌ 11፡14፤ 15፡22

ምስክርነት እስኪያገኙ ይታገሱ – ማቴ 18፡16፤ 1ቆሮ 14፡29፤ 2ቆሮ13፡1

እግዚአብሔር ለእርሱ ያለንን ፍቅር ሊፈትን ሃሰተኛ ቃላት በሕይወታችን እንዲያልፉ ሊፈቅድ ይችላል – ዘዳ 13፡3

ከእግዚአብሔር ፈቀቅ የሚያደርጎት ከሆነ ይህ ከሃሰት ነው – ዘዳ 13፡1-3

ተጨባጭ ተአምር ሃሰት ሊሆን ይችላል – ዘዳ 13፡1-3

የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ከሕልም፣ ወዘተ በላይ ናቸው – ዘዳ 13፡4

ሃሰትን ከመካከላችን ልናስወግድ ይገባል – ዘዳ 13፡5

ሕልሞችና ራዕዮች መጽናናትን ሊያመጡ ይችላሉ

ለአብርሃም – ዘፍ 15፡1

ለጳውሎስ – ሐዋ 18፡9

ሕልሞችና ራዕዮች ከእግዚአብሔር ዘንድ ማስጠንቃያን ሊያመጡ ይችላሉ

ጌዴዎን የሰማው ሕልም – መሳ 7፡13-15

ዮሴፍ ከግብጽ ወደ እስራኤል ተመራ – ማቴ 2፡19

ዮሴፍ ወደገሊላ ተመራ – ማቴ 2፡22

አናኒያ ለጳውሎስ እንዲጸልይ ተመራ – ሐዋ 9፡10

ጳውሎስ ለአናኒያ መምጣት ተዘጋጀ – ሐዋ 9፡12

ጳውሎስ ወደሜቄዶኒያ እንዲጓዝ ተመራ – ሐዋ 16፡9

ሕልሞችና ራዕዮች ስህተት ሊሆኑ ይችላሉ

የአንድ ሰው የገዛ ልብ ክፋትን ሲመኝ – ኤር 14፡14፤ ኤር 23፡16

ሕልሞች – ኤር 23፡25፣ 32

አንዳንድ ሕልሞች ከእግዚአብሔር ያርቁናል – ኤር 23፡27

እነዚህን የሃሰት ሕልሞች መከተል የለብንም – ኤር 27፡9

የገዛ ራሳችን ሕልሞች ሃሰተኛ ሊሆኑ ይችላሉ – ኤር 29፡8

ሃሰተኛ ሕልሞች ወደ ሃሰተኛ ትንቢቶች ሊመሩ ይችላሉ – ሕዝ 13፡7

ሃሰተኛ ሃይማኖቶች ሃሰተኛ ሕልሞችና ራዕዮችን ያቀርባሉ – ዘካ 10፡2

አንዳንድ ሕልሞችና ራዕዮች ግልጽ ቅዠቶች ናቸው

በመራብና በመጠማት ምክንያት – ኢሳ 29፡8

የሥራ ብዛት ውጤት – መክ 5፡3፣ 7

አንዳንድ ሕልሞች ፍፁም ስጋዊ ናቸው – ይሁዳ 1፡8

አልኮልና አደንዛዥ እጾች የሃሰተኛ ሕልሞችና ራዕዮች ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ – ኢሳ 28፡7

መ) እግዚአብሔር በሕልም ይናገራል – ኢዮብ 33፤ 15-18

ብሉይ ኪዳን

አቤሜሌክ – ዘፍ 20፡3-7

ያዕቆብ – ዘፍ28፡12፤ 31፡10

ላባ – ዘፍ 31፡24

ዮሴፍ – ዘፍ 37፡5-9

ሰሎሞን – 1ነገ 3፡5-15

ናቡከደነጾር – ዳን 2፡1፣ 31፤ 4፡5፣ 8

ዳንኤል – ዳን 7

አዲስ ኪዳን

ዮሴፍ- ማቴ 1፡20-21፤ 2፡13፣ 19-20

የጥበብ ሰዎች – ማቴ 2፡11-12

የጲላጦስ ሚስት – ማቴ 27፡19

ሠ) እግዚአብሔር በራዕይ ይናገራል – ኢዮብ 33፡15-18፤ መዝ 89፡19

ብሉይ ኪዳን

አብርሃም – ዘፍ 15፡1

ያዕቆብ – ዘፍ 46፡2

ኢሳያይስ – ኢሳ 6፡1-8

ዳንኤል – ዳን 2፡19፤ እና ምዕረፍ 7፣ 8፣ 10

ናሆም – ናሆም 1፡1

ዓሞጽ – ዓሞጽ 7፡1-9፤ 8፡1-6፤ 9፡1

ዘካርያስ – ዘካ 1፡8፤ 3፡1፤ 4፡2፤ 5፡2፤ 6፡1

ሕዝቅኤል – ሕዝ 1፣ 8፣ 10፣ ወዘተ…

ናቡከደነጾር – ዳን 2፡28

አዲስ ኪዳን

ጳውሎስ – ሐዋ 9፡3፣ 6፣ 12፤ 16፡9፤ 18፡9፤ 22፡18፤ 27፡23፤ 2ቆሮ 12፡1-4 አናኒያ – ሐዋ 9፡10-11

ጴጥሮስ – ሐዋ 10፡9-17

ቆርነሊዎስ – ሐዋ 10፡3

ዮሐንስ – የዮሐንስ ራዕይ

Leave a Reply

%d bloggers like this: