በብሉይ ኪዳን ወቅት አብ በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት፣ ወልድ በግልጽ ይታይ ነበር፡፡ በአሁኑ ዘመን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ ይታያል፡፡
ሀ) በብሉይ ኪዳን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
– በፍጥረት ሥራ – ዘፍ 1፡2
– ትንቢትን በመስጠት – ሕዝ 2፡2፤ 8፡3፤ 11፡1-5
በልአም – ዘኁ 24፡2-9
ሳኦል – 1ሳሙ 10፡6፣ 10
ዳዊት – ሐዋ 1፡16
– ችሎታን በመስጠት
ለባስልኤል የግንባታ ጥበብ – ዘጸ 31፡2-5
– የመንግስት አስተዳደር ጥበብ
የሴፍ – ዘፍ 41፡38-44
ሙሴና 70ዎቹ ሽማግሌዎች – ዘኁ 11፡14-17፣ 25-29
ጎቶንያል – መሳ 3፡9-10
ሳምሶን – መሳ 14፡19፣ 15፡14
ዳዊት – 1ሳሙ 16፡13
ጌዴዎን – መሳ 6፡34
ሳኦል – 1ሳሙ 10፡10
– አኗኗርን በመቀየር
ፍትህ፣ ጻድቅና ሰላም – ኢሳ 32፡15-20
ለጌታ አምልኮ – ኢሳ 44፡3-5
አዲስ ልብ – ሕዝ 36፡26-28
ለ) መንፈስ ቅዱስ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር ያለው ግንኙነት
– የቅዱሳት መጽሐፍ ደራሲ
መንፈስ ቅዱስ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር እንዲናገሩ መራ – 2ጴጥ 1፡20-21
ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የ “እግዚአብሔር እስትንፋ” (መንፈስ) ውጤቶች ናቸው – 2ጢሞ 3፡16
መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራል – ራዕ 2፡7፣ 11፣ 17፣ 29
– የእግዚአብሔርን ጥበብ የሚፈታ (የሚገልጥ፣ የሚያብራራ) – 1ቆሮ 2፡9-14፤ ኤፌ 1፡17፤ ዮሐ 15፡26-16፡15
ሐ) ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
– መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ የነበረው ሚና
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተጸነሰ – ሉቃስ 1፡35፤ ማቴ 1፡18
ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን በጥምቀቱ ወቅት ተቀበለ – ሉቃስ 3፡21-22
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በሰይጣን ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረበዳ ተመራ – ማር 1፡12፤ ማቴ 4፡1
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ተጓዘ – ሉቃስ 4፡14
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ቅባት ሰበከ – ሉቃስ 4፡18
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አጋንንትን አስወጣ – ማቴ 12፡28
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሃሴት አደረገ – ሉቃስ 10፡21
ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ከሞት ተነሳ – ሮሜ 8፡11
– መጥምቁ ዮሐንስ
በማሕፀን ውስጥ ሳለ በመንፈስ ተሞላ – ሉቃስ 1፡15
መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ ሲመጣ አየ – ማቴ 3፤ 16፤ ዮሐ 1፡31
ኢየሱስ በመንፈስ ያጠምቃል ብሎ መሰከረ – ማር 1፡7-8
መ) በቤተ ክርስቲያን ዘመን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት
– መንፈስ ቅዱስ፣ ከእስራኤል ሌላ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ድርሻ ያላቸው መኖራቸውን አስታወቀ።
– የአሕዛብ መካተት ምስጢር – ኤፌ 3፡5-8
– በአሕዛብ ሁሉ ላይ የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ – ኢዩ 2፤ 28 ከ ሐዋ 2፤ 16-18 ጋር
ሠ) ስለ መንፈስ ቅዱስ የአስተምህሮ ምንባብ – ዮሐ 14፡16-16፡15
በኢየሱስ ስም ከአብ ዘንድ የተላከ – ዮሐ 14፡26
ከአብ ዘንድ በኢየሱስ የተላከ – ዮሐ 15፡26
ስለ ኢየሱስ የሚመሰክር – ዮሐ 15፡26-27
ኃጢአተኞችን የሚወቅስ – ዮሐ 16፡7-8
ወደ እውነት የሚመራን – ዮሐ 16፡13
ስለ አብና ወልድ የሚናገር – ዮሐ 16፡14-15
ረ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ግብር የአስተምህሮ ምንባብ – ሮሜ 8፡1-39
ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነፃ አወጣን – ሮሜ 8፡2
የሕግን ፈቃድ በመንፈስ በመጓዝ እናሟላለን – ሮሜ 8፡4 ለ
ሰውነታችን ሃይልን ይሰጣል – ሮሜ 8፡11
በመንፈስ ሰላምና ሕይወት አለን – ሮሜ 8፡5-6
ክፉ ተግባሮቻችን በመንፈስ ተወግደዋል – ሮሜ 8፡13
በድካማችን እንድንጸልይ ይረዳናል – ሮሜ 8፡26
በመንፈስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ልጆች እንጂ ባሮች አይደለምን – ሮሜ 8፡15-17
ሰ) መንፈስ ቅዱስ በኤፌሶን መጽሐፍ
የእግዚአብሔር መሆኔን በምን አውቃለሁ? በክርስቶስ፣ በመንፈስ – ኤፌ 1፡13-14
መንፈስ እንዴት ይረዳናል? የጥበብና የመገለጥን መንፈስ በመስጠት – ኤፌ 1፡17
በሰማይ ወደ አለው አብ እንዴት መቅረብ እችላለሁ? በመንፈስ ወደ አብ መግባት እንችላለን – ኤፌ 2፡18
እግዚአብሔር በመካከላችን (በቤተ ክርስቲያን በመቅደሱ) እንዴት ይኖራል? እግዚአብሔር በመንፈስ አማካኝነት በመካከላችን ያድራል – ኤፌ 2፡22
አሕዛብ በኢየሱስ አማካኝነት ምህረት እንደ ተደረገላቸው እግዚአብሔር እንዴት ገለጠው? የእግዚአብሔር መንፈስ ለሐዋሪያትና ነቢያት ገለጠው – ኤፌ 3፡4-6
ኢየሱስ በልባችን ይኖር ዘንድ እንዴት ልንጠነክር እንችላለን? የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጥ ሰውነታችን ያጠነክረናል – ኤፌ 3፡16-17
በውስጣችን ካለው የእግዚአብሔር መንፈስ ጋር እንዴት በሰላም እንኖራለን? መራርነትና ንዴት የመሰሉትን በማስወገድ – ኤፌ 4፡30-32
ለሕይወቴ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድን ነው? በመንፈስ ቅዱስ እንድሞላ – ኤፌ 5፡17-18
ከመከላከያ የዘለለው የእግዚአብሔር የጦር እቃ ምንድን ነው? የመንፈስ ሰይፍ (የእግዚአብሔር ቃል ) – ኤፌ 6፡17
– በመንፈስ ቅዱስ መጸለይ – ኤፌ 6፡18
– መንፈስ ቅዱስ ደኅንነታችንን (ድነታችንን) ያረጋግጥልናል/በሕይወታችንም እንድናጣጥመው ያደርገናል
– ስለኃጢአት፣ ጽድቅና ፍርድ ይወቅሰናል – ዮሐ 16፡7-8
– ከመንፈስ መወለድ አለብን – ዮሐ 3፤ 3-6፤ ቲቶ 3፡5
– ከዚህ ልደት በኋላ መንፈስ በአማኙ ውስጥ ያድራል/ይሞላል – ሐዋ 2፡4፤ ኤፌ 5፡18፤ 1ቆሮ 6፡19
– በኃጢአት ጸንቶ የማይኖር ሕይወት እንድንኖር ሃይል ይሰጠናል – ሮሜ 8፡2
– የእግዘዚአብሔርን አገልግሎት እንድናገለግል በሃይል ይሞላናል – ዮሐ 14፡11-17፤ ሐዋ 1፡8፤ 1ቆሮ 2፤ 4
– ይመራናል ያስተምረናል – ዮሐ 14፡26፤ 16፡13
– በአማኙ ሕይወት ውስጥ የመንፈስ ፍሬን ያፈራል – ገላ 5፡22-23