ሀ) የእግዚአብሔር ሶስትነትና አንድነት
እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው 1ጢሞ 3፡16
የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ማን ሊመረምር ይችላል ኢዮብ 11፡7-8
እነዚህ ሦስቱም መለኮታዊ ናቸው
አብ – ክፍል ለ7 ይመልከቱ
ወልድ – ክፍል ለ8፣ ለ9፣ ለ10፣ ለ11 ይመልከቱ
መንፈስ ቅዱስ – ክፍል ለ12፣ ለ13 ይመልከቱ
ሦስቱም አንድ ናቸው
እግዚአብሔር አንድ ነው ዘዳ 6፡4-5፤ ማር 12፡29፤ ያዕ 2፡19
ኢየሱስ እርሱና አብ አንድ እንደሆኑ ተናግሯል ዮሐ 10፡30
“ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” ብዙ ቁጥር ዘፍ 1፡26
“ማንን እልካለሁ?’’ (ነጠላ ቁጥር) ‘‘ማንስ ይሄድልናል?’’ (ብዙ ቁጥር) ኢሳ 6፡8
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ (ብዙ ቁጥር) ስም (ነጠላ ቁጥር) እያጠመቃችኋቸው…” ማቴ 28፡19-20
ለ) መንፈስ – እግዚአብሔር መንፈስ ነው ዮሐ 4፡24
ስለዚህ የተቀረጸ ምስል፣ ጣኦቶች አይኑርህ ዘዳ 5፡8፤ ኢሳ 42፡8፤ 1ዮሐ 5፡21
ስለዚህ መንፈሳዊ አምልኮ አስፈላጊ ነው ዮሐ 4፡24
ስለዚህ ሃሰተኛ ሃይማኖት ዋጋ ቢስ ነው ክፍል ረ6 ፣ ሰ5 ይመልከቱ
ስለዚህ በመንፈስ መወለድ የግድ ይሆናል ዮሐ 3፡3-8፤ 1ቆሮ 15፡30
ሐ) በራሱ ሕልው (ህያው) ነው
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ዘፍ 1፡1፤ ዮሐ 1፡1
አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ወልድ በራሱ ሕይወት አለው ዮሐ 5፡26
እርሱ የሕይወት ምንጭ ነው መዝ 36፡9፤ ኤር 17፡13
ለተፈጥሮ ሕይወትን የሚሰጥ እርሱ ነው ዘፍ 2፡7
ለዳግም ልደት ሕወትን የሚሰጥ እርሱ ነው ዮሐ 3፡6፤ 1ቆሮ15፡45
የዘላለምን ሕይወት የሚሰጥ እርሱ ነው ራዕ 21
መ) የእግዚአብሔር ልዩነትና አንድነት
‹‹አንዱ አምላክ›› ዮሐ 5፡44፤ ይሁዳ 25
ጌታ አንድ ነው ዘዳ 4፡35፤ ማር 12፡29
ከእርሱ በፊትም ሆነ በኋላ ማንም የለም ኢሳ 43፡10-13፤ ራዕ 1፡8
አንድ እግዚአብሔር 1ቆሮ 8፡4፤ 1ጢሞ 2፡5
ወደ እርሱ የሚያደርስ አንድ መንገድ ብቻ አለ ዮሐ 14፡6
ሊመለክና ሊታዘዙት የሚገባ እርሱ ብቻ ነው ዘጻ 20፡2-3፤ ዕብ 5፡9