ሀ) መግቢያ
– በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትን ፈጠረ – ዘፍ 1፡1 ይህ የሆነው ምናልባት መላዕክት በተፈጠሩበት ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡
– የምድርና ቅርብ ያሉ ሰማያት መፈጠር – ዘፍ 1፡1-31 ይህ ስለምድርና አካባቢዎ ስላሉ ፍጥረታት ይመለከታል
ለ) የፍጥረት ልደት
– እግዚአብሔር አጽናፈ አለሙን ካለመኖረ ወደ መኖር አመጣ – ዘፍ 1፡1፤ ኢሳ 42፡5፤ ዓሞጽ 5፡8
እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ደግሞ ሊያበጅ ይችላል (ያበጃልም) – አሳ 65፡17፤ ራዕ 21፡1
– የተፈጠረው ነገር ሲፈጠር እጅግ መልካም ነበር – ዘፍ 1፡31 የክፋት ችግር ከዚህ የፍጥረት ልደት በኋላ የመጣ ነው የክፋት ችግር ከሰው እንጂ ከእግዚአብሔር አልመጣም
– የፍጥረት ባለቤት አብ – ሮሜ 11፡36 ወልድ፣ ቃሉ – ዮሐ 1፡1-3 መንፈስ ቅዱስ – ዘፍ 1፡2
– በምድር ለሚኖሩ ሕዝቦች እስትንፋስን የፈጠረ እግዚአብሔር ነው – ኢሳ 42፡5፤ ዘካ 12፡1
– መንፈሳዊ ሃይላትንና ስልጣናትን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው – ቆላ 1፡16-17 እግዚአብሔር ብቻውን መናፍስትን ሊያጠፋ ይችላል – ማቴ 10፡28፤ ሉቃስ 12፡4-5
– እግዚአብሔር በአፉ ቃል ፈጠረ – ዘፍ 1፡3፤ መዝ33፡6፣ 9፤ ዕብ 11፡3 እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፣ አላማና ጥበብ – ኤፌ 1፡11፤ ራዕ 4፡11
– እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ፈጣሪ ስለሆነ፣ ከዋክብትን፣ መናፍስትን፣ ጣኦትን፣ ሰዎችን፣ እፅዋትን ወይም እንስሳትን ልናመልካቸው አይገባም – ሮሜ 1፡20-25
ሐ) መግቦቱና መገኘቱ አይቋረጥም
– እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በቃሉ ደግፎ ይይዛል – ዕብ 1፡3
– እርሱ ለሁላችንም ቅርብ ነው – ሐዋ 17፡27-28
በተለይም ለአማኞች ግድ ይለዋል – ዕብ 13፡5
እንደያዕቆብ፣ መገኘቱን ላናስተውል እንችላለን – ዘፍ 28፡16
– የምንኖረው በእግዚአብሔር ያልተቋረጠ መግቦት ነው – መዝ 36፡6
– እግዚአብሔር ፍላጎቶችን ይሞላል – መዝ 23፡1-6፤ 147፡1-9፤ 1ጴጥ 5፡6-7፤ ማቴ 5፡45፤ 6፡25-34፤ ሐዋ 14፡17
– እግዚአብሔር ይጠብቀናል ያድነናል – ዘፍ 28፡15፤ ዘዳ 32፡11፤ ኢሳ 25፡4፤ ማቴ 23፡37፤ ዮሐ 17፡11፤ ፊል 4፡6-7፤ 2ተሰ 3፡3፤ ይሁዳ 24-2
– እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጪ በተአምራት ይሰራል – ክፍል ለ2
መ) እግዚአብሔር ድነትን ለሁሉ አቅርቧል – ክፍል ሠ
ሠ) እግዚአብሔር በሚከተሉት መልኮች ከሰው ልጅ ጋር ሕብረት ማድረጉን አላቋረጠም፡
– እንደ አባት – የእግዚአብሔር አባትነት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ለ7
– እንደ ፈጣሪ – የፍጥረት ልደት የሚለውን ይመልቱ
– እንደ ባል – ለእስራኤል – ኤር 3፡20
– እንደ ንጉስ – የእግዚአብሔር መንግስት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል መ6
– እንደ ፈራጅ – ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሸ
– እንደ አዳኝ – ደኅንነት የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሠ
– እንደ መምህር – መንፈስ ቅዱስ/የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን ይመልቱ – ክፍል ለ12 እና ለ13
– እንደሙሽራና ባል – ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ይመልከቱ – ክፍል ሸ
ረ) እግዚአብሔር ሰማያትና እና ምድርን ዳግመኛ ይፈጥራል – ራዕ 21፡5
– የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያው ምድር ይጠፋሉ – ራዕ 21፡1
– አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር – ራዕ 21፡1፣ 5፤ ኢሳ 65፡17 –
በእዚያ ሃዘን፣ ሞትና በሽታ የሉም – ራዕ 21፡4
– እኛም ኢየሱስን እንመስላለን – 1ዮሐ 3፡2