ሀ) የእግዚአብሔር መልካምነት ማቴ 19፡16-17
ለ) የእግዚአብሔር ምህረትና ጭከና ሮሜ 11፡22
ሐ) ቅዱስ ራዕ 4፡8
– እንደእግዚአብሔር ያለ ቅዱስ የለም 1ሳሙ 2፡2፤ ራዕ 15፡4
– እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ፍጹም ነው ሌዋ 19፡2፤ ማቴ 5፡48
– ከቅድስናው ተካፋዩ ልንሆን ይገባል ዕብ 12፡10፣ 14፤ 1ጴጥ 1፡16
– መንፈስ ቅዱስ ሊቀድሰን ይመጣል ሮሜ 15፡16
– ቅድስና ውብ ነው 2ዜና 20፡21፤ መዝ 29፡2
– ቅድስና-ንጽሕና የሚለውን ርዕስ በተጨማሪ ይመልከቱ ክፍል ሠ11
መ) ጻድቅና ትክክል ራዕ 16፡15፤ 19፡2
– እግዚአብሔር ኅጢአትን ይጸየፋል ዕብ 1፡8-9
– በመንግስቱ ክፋት አያድርም 1ቆሮ 6፡9-10
– በተጨማሪ እነዚህን ጥቅሶች ይመልከቱ ኢዮብ 34፡12፤ መዝ 7፡9፤ 116፡5፤ 119፡137
– ጽድቁን ልንካፈል ይገባል 1ዮሐ 3፡7 – ኃጢአትን ልንጠላ ይገባል ዕብ 12፡4፤ 1ዮሐ 3፡8-9
ሠ) አፍቃሪና ርኅሩኅ ዮሐ 3፡16፤ መዝ 69፡16፤ ሰ.አር 3፡22-23
– እግዚአብሔር ፍቅር ነው 1ዮሐ 4፡8፤ ቲቶ 3፡4-5
– ፍቅሩን ልንካፈል ይገባል ዘሌ 19፡18፤ ሉቃስ 10፡27፤ ሮሜ 13፡9፤ ገላ 5፡14
– እግዚአብሔርን ለእኛ ያለው ፍጹም ፍቅር ፍርሃታችንን አስወግዶ ይጥላል 1ዮሐ 4፡18
– ወደ እግዚአብሔር በድፍረት መግባት ሆኖልናል ዕብ 4፡16
– ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን የለም ሮሜ 8፡38-39
– ከፍቅር ጋር በተያያዘ ለትምህርት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል 1ቆሮ 13፡4-7
ረ) ታማኝና እውነተኛ ኢሳ 25፡1፤ ራዕ 3፡14፤ 19፡11
– ሰው ሃሰተኛ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ይኖራል ሮሜ 3፡4፤ ዮሐ 17፡3
– ተስፋን የሰጠው አምላክ የታመነ ነው ዕብ 10፡23፤ 11፡11
– ለመታደስ እርሱን ተስፋ እናደርጋለን 1ተሰ 5፡23-24፤ 2ጢሞ 1፡12
– ከኃጢአት ሊያስመልጠን እርሱ የታመነ ነው 1ቆሮ 10፡13
– ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው ምሳሌ 20፡6
– እግዚአብሔር እንደ እርሱ ታማኝ የሆኑ ሰዎችን ይፈልጋል (ራዕ 2፡10፤ 17፡14፤ 2ጢሞ 2፡2) ሙሴ – ዘኁ 12፡7፣ ዳንኤል – ዳን 6፡4፣ ኤጳፍራ፣ ቲኪቆስ፣ አናሲስም – ቆላ 1፡7፤ 4፡7፣ 9፣ ዳዊት – 1ሳሙ 22፡14፣ ኢየሱስ – ራዕ 19፡11
– እግዚአብሔር ታማኞችን ይጠብቃል – መዝ 31፡23
– የእግዚአብሔር አይኖች በታማኞች ላይ ነው – መዝ 101፡6
– እግዚአብሔር ታማኝ ባሪያን ይሸልማል – ማቴ 25፡21
ሰ) ለጋስ
– እግዚአብሔር ይሰጣል
ቅዱሳት መጻሕፍትን – 2ጢሞ 3፡16
አንድያ ልጁን – ዮሐ 3፡16፤ ሮሜ 8፡32
መንፈስ ቅዱስን – ሉቃስ 11፡13፤ 1ተሰ4፡8፤ ሮሜ 5፡5 ንስሃን – 2ጢሞ 2፡25
የዘላለም ህይወት ስጦታን – ሮሜ 6፡23፤ 1ዮሐ 5፡11
ለትሁታን ጸጋን – 1ጴጥ 5፡5፤ ያዕ 1፡5
ለደካማው እረፍትን – ማቴ 11፡28
ጥበብን – ዳን 2፡23፤ ያዕ 1፡5
በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ድልን – 1ቆሮ 15፡57
የማገልገል ብቃትን – 1ጴጥ 4፡11፤ ኤፌ 3፡7
ለፍጥረት ሁሉ ምግብን – መዝ 136፡25 ኅ
ብት የማፍራት ችሎታን – ዘዳ 8፡18
ለምድራዊ ገዢዎች ስልጣንን – ዳን 2፡37
– ከእግዚአብሔር የልግስና ባሕሪ ልንካፈል ይገባል። መስጠት የሚለውን ክፍል በተጨማሪ ይመልከቱ – ክፍል ሰ8
ሸ) የእግዚአብሔር ታላቅነት
ሁሉን አዋቂ – በሁሉ ስፍራ የሚገኝ – ሁሉን ማድረግ የሚችል – ዘላለማዊ – የማይለወጥ
ቀ) እግዚአብሔር ጠቢብ፣ ሁሉን አዋቂ ነው – ሮሜ 16፡27
– እግዚአብሔር አዋቂ ጌታ ነው – 1ሳሙ 2፡3
– ጥበቡ ጥልቅ ናት – ኢዮብ 9፡4
– ከሰው መረዳት በላይ ነው – መዝ 139፡4-6፤ ሮሜ 11፡33
– የእግዚአብሔር ጥበብ ባሕርይ – ያዕ 3፡17
ንጹሕ – ከሃሰት ጋር የማይቀየጥ
ሰላማዊ – ጠብን የማይጭር
ጨዋ – አስቸጋሪ/የማይመች ወይም ግትር ያልሆነ
መኀሪ – ሕግን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚገልጥ
የማያዳላ – ለራስ ወይም ለወገኔ ይጠቅማል በሚል የማይሰራ
ግብዝነት የሌለበት – የሚለውን የሆነ
– እግዚአብሔርዊ ያልሆነ ጥበብ ባሕሪይ
አለማዊ፣ ሥጋዊ፣ የአጋንንት ጥበብ – ያዕ 3፡14-16
ለእግዚአብሔር ሞኝነት የሆነ – 1ቆሮ 3፡18-20
– ለአማኞች ጥበብ ተዘጋጅቷል – ያዕ 1፡5-7፤ ቆላ 1፡9፤ ኤፌ 1፡17
ክርስቶስ ጥበባችን ነው – 1ቆሮ 1፡24፤ ቆላ 2፡2
የክርስቶ ቃል ጥበባችን ነው – ቆላ 3፡16
– የጥበብ ቃል መንፈሳዊ ስጦታ – ክፍል ረ11
በ) እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ በአንድ ጊዜ ይገኛል – መዝ 139፡7-12
– ስለዚህ በየትኛውም ስፍራ ብንጸልይ እርሱ ይሰማናል፡፡
– ሁሉን ነገር በሁሉ ረገድ ይሞላል – ኤፌ 1፡22-23
– ከማናችንም ሩቅ አይደለም – ሐዋ 17፡27-28፤ ኤር 23፡23
– በሲኦል፣ በሰማይ – መዝ 139፡8፤ ዓሞጽ 9፡2-3
– ከእርሱ ልንደበቅ አንችልም – ኤር 23፡24
– ይህ ማለት እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ውስጥ አለበት ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች በሚከተሉት ነገሮች ሲወቅሳቸው እናነባለን፡
ጣኦትንና ዲያብሎስን ሲያመልኩ – ኢሳ 2፡8-11፤ 20-21፤ ራዕ 9፡20
የተፈጠሩትን ሲያመልኩ – ሮሜ 1፡25
መላዕክትን ሲያመልኩ – ቆላ 2፡18፤ ራዕ 22፡8-9
የሙታን መናፍስትን ሲያመልኩ – ዘሌ 20፡6፤ ዘጻ 18፡9-11፤ ኢሳ 8፡19
– ማስታወሻ፡ በድፍረት መጸለይ እንችላለን – ኤር 33፡3
ተ) እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው
– እርሱ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ነው – ዘፍ 1፡1
– ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው – ቆላ 1፡17
– ሃይሉ ታላቅ ነው – ኢዮብ 9፡4
– ስለዚህ ሊያድንና ሊታደግ ይችላል – ኢሳ 50፡2
– ሁሉ ለእግዚአብሔር ይቻላል – ማቴ 19፡26፤ ኤር 32፡17
– ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? – ኤር 32፡27
– የእግዚአብሔር ድካም ከሰዎች ብርታት ይበረታል – 1ቆሮ 1፡25
– ሃይሉን ልንካፈል ይገባል – ኢዮ 3፡10፤ 2ቆሮ 12፡10፤ ዕብ 11፡34
– በእግዚአብሔር ጸጋ ልንበረታ ይገባል – 2ጢሞ 2፡1
– በሃይ ልንበረታ ይገባል – ኤፌ 6፡10
– ሰይጣንን ለመርታት ልንበረታ ይገባል – 2ቆሮ 10፡3-5
– በእምነት ልንበረታ ይገባል – ሮሜ 4፡20
– ለመበርታትና ለመበዝበዝ – ዳን 11፡32
ቸ) እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው – 1ዮሐ 5፡20
– ከዘላለም እስከዘላለም – መዝ 90፡1-2
– መጀመሪያና መጨረሻ – ራዕ 22፡13
– ያለ፣ የነበረና፣ የሚመጣው – ራዕ 1፡8
– ከእርሱ በፊትና በኃላ ምንም የለም – ኢሳ 43፡10
– ዘላለማዊ ሕይወቱን መካፈል እንችላለን – ዮሐ 3፡15-16፤ ሮሜ 6፡23፤ 1ዮሐ 5፡11-13
– የሰጠነውን አደራ ይጠብቃል – 2ጢሞ 1፡12
ነ) እግዚአብሔር አይለወጥም – ሚል 3፡6
– ስለዚህ የፍቅር ስጦታው ሊታመን ይችላል፡፡
– ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትና፣ ዛሬ፣ ወደፊት ያው ነው – ዕብ 13፡8
– በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ የለም – ዕብ 1፡17
– እርሱን ለመምሰል መለወጥ አለብን – 1ዮሐ 3፡2፤ 1ቆሮ 15፡51-53