መላእክት – የእግዚአብሔር መልእክተኞች

ሀ) መላእክቶች ማን ናቸው?

መላእክት በመጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ጊዜ የተጠቀሱ ቢሆንም፣ የተጠቀሱበት አላማ እኛን ስለ መላእክት ለማስተማር ታስቦ አይደለም፡፡ በተጠቀሱባቸው ጥቅሶች ውስጥ የምንማረው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነትና አላማውን ለማስፈጸም እንደመሳሪያ ማገልገላቸውን ነው፡፡

“መልአክ” የሚለው ቃል ትርጉም በእብራይስጥም ሆነ በግሪክ ቋንቋ “መልእክተኛ” ማለት ነው፡፡

– ሊመለኩ አይገባቸውም – መሳ 13፡16-18፤ ቆላ 2፡18፤ ራዕ 19፡10፤ 22፡8-9

– ሁለት የመላእክት ክፍሎች አሉ፣ መልካምና ክፉ – ራዕ 12፡7

– ስለ ክፉ መላእክት ለማወቅ ሐ2 እና ክፍል ሐ5 ላይ የሚገኘውን የዲያቢሎስ ጥናት የሚለውን ይመልከቱ።

– መላእክት ከሚለው ስማቸው በተጨማሪ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስም ተሰይመዋል፡-

– ጠባቂዎች – ዳን 4፡13፣ 17፣ 23

– የሰማይ መላእክት – ማቴ 24፡36

– የሰማይ ሠራዊት – ሉቃስ 2፡13

– መናፍስት – ዘካ 6፡5፤ ዕብ 1፡4፣ 14

– የእግዚአብሔር ልጆች – ኢዮብ 1፡6፤ 2፡1፤ 38፡7

– ስልጣናት፣ ኀይላት፣ ዙፋናት፣ ገዦች፣ ባለ ስልጣናት – ቆላ 1፡16፤ ሮሜ 8፡38፤ 1ቆሮ 15፡24፤ ኤፌ 6፡12፤ ቆላ 2፡ 15

– መላእክት ከዚህ በታች በተጠቀሱ ስያሜዎች ተጠርተዋል

– ገብርኤል – ዳን 8፡16፤ 9፡21፤ ሉቃስ 1፡11-20፣ 26-38

– ሚካኤል – ዳን 10፡13፣ 21፤ 12፡1፤ ይሁዳ 9፤ ራዕ 12፡7

– ሰይጣን (ከተጨማሪ ሌሎች ስሞች ጋር) – ክፍል ሐ3 ይመልከቱ

– መንፈሳዊ አካላቱ የተለያዩ ማእረጋትና ቅደም ተከተሎች አሏቸው

– ሰማያዊ ፍጡራን – 2ጴጥ 2፡10-11

– ሱራፌል – ኢሳ 6፡2፣ 6 – ኪሩቤል – ዘፍ 3፡24፤ ዘጸ 25፡18፤ መዝ 18፡10፤ ሕዝ 10፡2-9

– ሰይጣን ኪሩብ ነበር – ሕዝ 28፡14-16

– የመላዕክት አለቃ – 1ተሰ 4፡16፤ ይሁዳ 9

– በእግዚአብሔር አብና ወልድ ተፈጥረዋል – ነሕ 9፡6፤ ቆላ 1፡16

– ከሰው መፈጠር በፊት ነበሩ – ኢዮብ 38፡1-7

– መንፈሳዊ አካላት ናቸው (ሥጋና ደም የላቸውም) – ኤፌ 6፡12፤ ዕብ 1፡14፤ መዝ 104፡4

– ነገር ግን አንድ አንድ ጊዜ በሰው መልክ ይገለጻሉ – ዘፍ 18፡2-33፤ 19፡1-22፤ መሳ 6፡11-22፤ ዮሐ 20፡1

– ሳናውቀው መላዕክትን ልናስተናግድ እንችላለን – ዕብ 13፡2

– በቁጥጥር በጣም ብዙ ናቸው – ዘዳ 33፡2፤ ዳን 7፡10፤ ማቴ 26፡53፤ ሉቃስ 2፡13፤ ዕብ 12፡22

– ብርቱዎች ናቸው – 2ነገ 19፡35፤ መዝ 103፡20፤ 2ተሰ 1፡7፤ 2ጴጥ 2፡11፤ ኢሳ 37፡36

– ጠቢቦች ናቸው ነገር ግን ሁሉን አዋቂዎች አይደሉም – 2ሳሙ 14፡20፤ ማቴ 24፡36፤ 1ጴጥ 1፡12

– ክርስቶስ ኢየሱስ ከመላእክት በእጅጉ ይበልጣል – ዕብ 1፡4-2፡15

ለ) የመልካም መላእክት ተግባራቸው ምንድን ነው?

– እግዚአብሔርን ማምለክና ማመስገን – ዕብ 1፡6፤ ራዕ 5፡11-12

– የሙሴ ሕግ በመላእክት በኩል ተሰጠ – መዝ 68፡17፤ ገላ 3፡19፤ ሐዋ 7፡53

– ለኢየሱስ ይታዘዛሉ – ኤፌ 1፡20-22፤ ቆላ 2፡10፤ 1ጴጥ 3፡22

– መዳንን የሚወርሱትን ያገለግላሉ – ዕን 1፡7፣ 14

– እርዳታቸው የሚገኘው ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ነው – ማቴ 26፡53፤ ሐዋ 12፡5-7

– የእግዚአብሔርን ፍርድ ያስፈፅማሉ – 2ሳሙ 24፡16፤ 2ነገ 19፡35፤ መዝ 35፡5-6፤ ሐዋ 12፡23፤ ራዕ 16፡1

– በመጨረሻው ዘመን መከሩን የሚሰበስቡ (አጫጆች) ናቸው – ማቴ 13፡39-41፣ 49-50፤ 24፡31

– ሕፃናትን ይጠብቃሉ – ማቴ 18፡10

– የእግዚአብሔርን ሕዝብ ይጠብቃሉ – ዳን 6፡22፤ መዝ 34፡7፤ 91፡11

– ከኢየሱስ ዳግም ምፅአት ጋር አብረው ይገለጣሉ – ማቴ 16፡27፤ 25፡31፤ ማር 8፡38፤ 1ተሰ 4፡16፤ 2ተሰ 1፡7

– በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ታላላቅ ትዕይንቶችን አብስረዋል

ፅንሱን – ሉቃስ 1፡31 ትንሳኤውን – ሉቃስ 24፡23

ዳግም ምፅአቱን – ሐዋ 1፡11

ልደቱን – ሉቃስ 2፡10-12

እርገቱን – ሐዋ 1፡11

ሐ) መላእክት በርካታ ሰዎችን አገልግለዋል

– አጋር፣ ሳራን ተለይታ ስትሄድ – ዘፍ 16፡7-13

– ሎጥ፣ ሰዶም ከመጥፋቷ በፊት – ዘፍ 19፡1-22

– አጋርና እስማኤል – ዘፍ 21፡17-19

– አብርሃም፣ ከይስሃቅ ጋር በተራራ በነበረ ጊዜ – ዘፍ 22፡11-18

– ያዕቆብ፣ የመሰላል ራዕይ ባየ ጊዜ – ዘፍ 28፡12

– የላባን በጎች በተመለከተ ባየው ራዕይ ውስጥ – ዘፍ 31፡11

– ኤሳውን ለመገናኘት ከላባ በሄደ ጊዜ – ዘፍ 32፡1

– ሙሴ፣ በሚነደው ቁጥቋጦ ስፍራ – ዘጸ 3፡2

– እስራኤል፣ በደመናው አምድ – ዘጸ 14፡19-20

– እስራኤልን በመምራት – ዘጻ 23፡20-23፤ ዘኁ 20፡16

– በልአምና አህያው – ዘኁ 22፤ 22-35

– ኢያሱና እስራኤል – መሳ 2፡1-5

– ጌዲዮን፣ እስራኤልን እንዲመራ ሲመረጥ – መሳ 6፡11-22

– የሶምሶን ቤተሰቦች – መሳ 13፡2-23

– ዳዊት ሕዝቡን ሲቆጥር – 2ሳሙ 24፡15-17፤ 1ዜና 21፡16-30

– ኤልያስን ለማጠንከር – 1ነገ 19፡5-8

– አሦራዊያንን ለመግደል – 2ነገ 19፡35፤ 2ዜና 32፡21፤ ኢሳ 37፡36

– ሲድራቅ፣ ሚሳቅና፣ አብድናጎ በእሳት ውስጥ – ዳን 3፤ 25-28

– ዳንኤል፣ አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ – ዳን 6፤ 22

– መልአኩ ገብርኤል ስለመጪው ዘመን ለማሳየት – ዳን 8፡16፤ 9፡21

– ዘካሪያስ በመላእክት በርካታ ነገር አየ – ዘካ 1፡9፤ 4፡1-6

– ዮሴፍ፣ የማርያም እጮኛ – ማቴ 1፡20-21 – ወደ ግብጽ እንዲሄድና እንዲመለስ – ማቴ 2፤ 13፤ 2፡19

– ኢየሱስ፣ መላአክ አገለገለው – ማቴ 4፡11፤ ማር 1፤ 13

– ሕጻናት መላእክት አሏቸው – ማቴ 18፡10

– ሴቶች፣ በኢየሱስ መቃብር – ማቴ 28፤ 2-8፤ ዮሐ 20፡11-13

– ዘካሪያስ ገብርኤልን በመቅደሱ ተመለከተ – ሉቃስ 1፡11-19

– ማርያም፣ የኢየሱ እናት ገብርኤልን ተመለከተች – ሉቃስ 1፡26-38

– እረኞች፣ በኢየሱስ ልደት ወቅት – ሉቃስ 2፡8-16

– ኢየሱስ፣ በደብረዘይት ተራራ ሲያለቅስና ሲጸልይ – ሉቃስ 22፡43

– ለበሽተኞች፣ ውኃ ማናወጥ – ዮሐ 5፤ 4

– ሐዋሪያትን ከእስራት ለማስፈታት – ሐዋ 5፡19-20

– ፊሊጶስ ለኢትዮጵያዊው እንዲመሰክር – ሐዋ 8፡26

– ቆርነሊዎስ ጴጥሮስን እንዲጠራ – ሐዋ 10፡3-8

– ጴጥሮስ ከሄሮድስ እስር ቤት እንዲያመልጥ – ሐዋ 12፡6-11

– ሄሮድስን መቶ ለመግደል – ሐዋ 12፡21-23

– ጳውሎስ፣ መርከቡ ከመሰበሩ በፊት – ሐዋ 27፡23-24

– ዮሐንስ፣ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ – የራዕይ መጽሐፍ

Leave a Reply

%d bloggers like this: