ሰይጣን – አጋንንት

ሀ) መግቢያ

– የተወሰኑ መላእክት በእግዚአብሔር ተጥለዋል – 2ጴጥ 2፡4፤ ይሁዳ 6

– ርኩሳን መናፍስት በሰዎች ውስጥ ሊያድሩ ይችላሉ – ማቴ 12፡43፤ ማር 1፡26፤ 5፡9፤ 7፡24-30፤ 9፡14-27፤ 16፡19

– የማያምኑ ሰዎች እርኩሳን መናፍስትን ለማስወጣት ቢሞክሩ ያለው አደጋ – ሐዋ 19፡12-16

– አጋንንት አታላይ መናፍስት በመባል ተጠርተዋል – 1ጢሞ 4፡1

– አጋንንት የሚሉትን ፈፅመው አይመኑ፣ ውሸተኞች ናቸውና – ዮሐ 8፡44

– ከአጋንንት ጋር አያውሩ – አስወጧቸው እንጂ – ማር 16፡15-18

– አጋንንት እግዚአብሔር እንዳለ ያምናሉ – ያዕ 2፡19

– ተአምራትና ማድረግ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22

ለ) አማኞች በአጋንንት ላይ ስልጣን አላቸው

– በእኛ ውስጥ ያለው ኢየሱስ በአለም ካለው ሰይጣን ይበልጣል – 1ዮሐ 4፡4

– አጋንንት ያለፈቃድ በአሳማዎቹ ውስጥ አልገቡም – ማቴ 8፡30-32

– ሐዋሪያት በአጋንት ላይ ስልጣን ተሰጣቸው – ሉቃስ 9፡1

– ሰባ የሚሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች አጋንንትን እንዲያወጡ ተላኩ – ሉቃስ 10፡1፣ 17

– ደቀ መዛሙርት ሁሉ አጋንንትን እንዲያወጡ ሥልጣን ተሰጣቸው – ማቴ 10፡1፤ ማር 16፡17

– ክፉ መናፍስት ለማውጣት የተሰጠ ተስፋ – ሉቃስ 10፡18-20

– ጳውሎስ የጥንቆላ መንፈስን አስወጣ – ሐዋ 16፡16

– አጋንንት በእምነት ቃል እና በሥልጣን ይወጣሉ – ሉቃስ 4፡32-36

ሐ) ሰይጣን – ስያሜዎቹና ታሪኩ

1) የሰይጣን ስያሜዎች፣ በሕሪያቶቹን ይገልጣሉ

– ሉሲፈር (የብርሃን መልአክ) በሰማይ ሳለ የሚጠራበት ስሙ – ኢሳ 14፡12

– ሰይጣን (ተቃዋሚ) – ማቴ 4፡10፤ 1ዜና 21፡1፤ ኢዮብ 1፡6፤ ዘካ 3፤ 1

– እባብ፣ የጥንቱ እባብ – ዘፍ 3፡1፣ 4፤ ራዕ 12፡9

– ዘንዶ፣ እባብ፣ ዲያብሎስ፣ ሰይጣን – ራዕ 12፡9፤ 20፡2

– ዲያብሎስ (ሃሰተኛ ከሳሽ) – ማቴ 4፡1፣ 5፣ 8፤ ኤፌ 6፡11-12፤ ራዕ 12፡9

– ፈታኝ – ማቴ 4፡3፤ 1ተሰ 3፡5

– ብዔልዜቡል (የእበት አምላክ) – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22

– የአጋንንት ወይም የዲያብሎስ አለቃ – ማቴ 12፡24፤ ማር 3፡22 – ክፉው – ማቴ 13፡19

– የዚህ አለም ገዢ – ዮሐ 13፡31፣ 14፡30፤ 16፡11

– ነፍሰ ገዳይ፣ ሃሰተኛ – ዮሐ 8፡44

– የዚህ አለም አምላክ – 2ቆሮ 4፡4፤ ዮሐ 12፡31፤ 14፤ 30፤ 16፡11

– ቤልሆር (ምናምንቴነት) – 2ቆሮ 6፡15

– በአየር ላይ ያሉ መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2

– ባላንጣ፣ ዲያብሎስ (ጠላት) – 1ጴጥ 5፡8

– አታላይ – ራዕ 12፡9

– የወንድሞች ከሳሽ – ራዕ 12፡10

– ከዚህ በታች ያሉ ስሞችም ለሰይጣን የተሰጡ ስያሜዎች ሳሆኑ አይቀሩም

– የጥልቁ ጉድጓድ መልአክ – ራዕ 9፡11

– አጶልዮን፣ አብዶን (አጥፊ) – ራዕ 9፡11

2) ሰይጣን ከሚከተሉት ጋር ተነጻጽሯል

– እባብ – ዘፍ 3፡1፤ ራዕ 12፡9፤ 20፡2

– አዳኝ ወፎች (fowler) – መዝ 91፡3

– እንክርዳድ ዘሪ – ማቴ 13፡25

– ተኩላ – ዮሐ 10፡12

– የሚያገሳ አንበሳ – 1ጴጥ 5፡8

3) ስለ ሰይጣን አጠቃላይ ታሪክ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሰለሰይጣን በርካታ ትምህርቶች አሉ፡፡

– ፍጡር ነው – ሕዝ 28፡13

– በሰማይ ሳለ “ሉሲፈር” በመባል ይጠራ ነበር – ኢሳ 14፡12

– በእግዚአብሔር፣ ጠባቂ ኪሩብ ተብሎ ተቀብቶ ነበር – ሕዝ 28፡14

– በተቀደሰው በእግዚአብሔር ተራራ – ሕዝ 28፡14

– የፍፅምና ተምሳሌት (የጥበብና የውበት) ነበረ – ሕዝ 18፡12፣ 15

– በእግዚአብሔር ገነት፣ በዔደን ነበር – ሕዝ 18፡13

– በመጀመሪያ በሰማይ ነበር ከዛ ተባረረ – ሉቃስ 10፡18

– በእግዚአብሔር ላይ አመጸ – 1ዮሐ 3፡8

– በደል በእርሱ ተገኘ – ሕዝ 28፡15

– በውበቱ ምክንያት በመኩራት – ሕዝ 28፡17

– የሰይጣን መውደቅ ምክንያቶች

– ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡13

– ዙፋኔንም ከእግዚአብሔ ከዋክብት በላይ ከፍ አደርጋለሁ – ኢሳ 14፡13

– … በተራራ ላይ እቀመጣለሁ – ኢሳ 14፤ 13

– ከደመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ – ኢሳ 14፡14

– በልዑል እመሰላለሁ – ኢሳ 14፡14

– የክፉ መናፍስት አለቃ፣ ክፉ መላእክት፣ አጋንንት – ማቴ 12፡24-28

– አንዳንድ ሰዎች ሰይጣን፣ አዳም ከመፈጠሩ በፊት፣ በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ባለቤት ለመሆን እንደፈለገ ያምናሉ፡፡

– ሰይጣን አለም የእርሱ እንደሆነች ተናግሯል – ማቴ 4፡8-9

– አዳም ምድርን እንዲያስተዳድር በእግዚአብሔር ተሰጥቶት ነበር – ዘፍ 1፤ 28

– ሔዋንን በዔደን ገነት አሳታት – ዘፍ 3፡1-7

– በእግዚአብሔር ተረገመ – ዘፍ 3፡14 – የሰው ልጅ ጠላት ነው – ዘፍ 3፤ 15

– በኢዮብ ዘመን፣ ሰይጣን ወደ እግዚአብሔር ይቀርብ ነበር – ኢዮብ 1፡6

– አሁንም ድረስ የወንድሞች ከሳሽ በመባል ይጠራል – ራዕ 12፡10

– ኢየሱስን ባይሳካለትም ፈተነው – ማቴ 4፡3፣ 4

– የብርሃን መልአክ መስሎ ሊቀርብ ይችላል – 2ቆሮ 11፡14

መ) የሰይጣንና የመላእክቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ

– ቅዱሳን በመላእክት ላይ ይፈርዳሉ – 1ቆሮ 6፡3

– ሰይጣን በእግዚአብሔር ስልጣኑ ይነጠቃል – ዘፍ 3፡15፤ ራዕ 20፡10

– ሰይጣን ከሰማይ ሲወድቅ ኢየሱስ መመልከቱን ተናገረ – ሉቃስ 10፡18

– በአየር ላይ ላሉት መንፈሳዊያን ኀይላት ገዢ – ኤፌ 2፡2

– ሰይጣን ከእግዚአብሔር ተራራ ተጥሏል – ሕዝ 28፡16 – በምድር ላይ ተጥሏል – ሕዝ 28፡17፤ ራዕ 12፡10-13

– ለአንድ ሺ አመት በሰንሰለት ይታሰራል – ራዕ 20፡1-3

– ሰይጣን በእሳት ባሕር ይጣላል – ማቴ 25፡41፤ ሕዝ 28፡18፤ ራዕ 20፡10

– የመዳን ተስፋ የላቸውም – ይሁዳ 6፤ 2ጴጥ 2፡4፤ ማቴ 25፡41

– የዘላለም እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል – ማቴ 25፡41

ሠ) ሰይጣን – ሥልጣንና ግብሩ

1) አካል አለው፣ የሆነ ሃይል ወይም ተጽእኖ ፈጣሪ አይደለም

– ኢየሱስን በፈተነው ወቅት ከኢየሱስ ጋር ምልልስ አድርጓል – ማቴ 4፡1-11

– ይናገራል – ዘፍ 3፡1፤ ማቴ 4፡3

– ኢየሱስ ነፍሰ ገዳዩ፣ ውሸታም ብሎ ጠርቶታል – ዮሐ 8፡44

– ተንኮለኛ ነው፣ ራሱን መለዋወጥ ይችላል – 2ቆሮ 11፡3፣ 14

– ከእግዚአብሔር ጋር ምልልስ አድርጓል – ኢዮብ 1፡6-12፤ 2፡1-6

– ይራመዳል፣ ያገሳል – 1ጴጥ 1፡8

– ሊታሰር ይችላል – ራዕ 20፡1-3

2) የሰይጣንና የወደቁ መላእክቶቹ ስልጣንና ግብር

– ጻድቃንን መቃወምና ማሰቃየት – ኢዮብ 1፡12-19፤ 2፡5-7፤ ዘካ 3፡1

– በበሽታ – ሉቃስ 13፡16፤ ማቴ 17፡15-16

– በአጋንንት – ማር 5፡15፤ 6፡13፤ 16፡19

– ሰዎችን ለማጥፋት መሞከር

– በፈተናዎች – 1ዜና 21፡1፤ 1ተሰ 3፡5

ሔዋን – ዘፍ 3፡1-7

ዳዊት – 1ዜና 21፡1

ይሁዳ – ሉቃስ 22፡1-6

ኢዮብ – ኢዮብ 1፡6-12

ክርስቶስ – ማቴ 4፡1-11

ሃናንያና ሰጲራ – ሐዋ 5፡1-11

– በውሸት – ዮሐ 8፡44

– በሞት ላይ ኀይል አለው – ዕብ 2፡14-15

– ወንጌል ለማጥፋት ይጥራል – ማቴ 13፡19፤ 2ቆሮ 4፡4

– የእግዚአብሔርን ሥራና ሠራተኞቹን መቃወም – ዘካ 3፡1፤ 1ተሰ 2፡18፤ ዳን 10፡19-14

– ቅዱሳት መጻሕፍትን ማጣመም – ማቴ 4፡6 እና መዝ 91፡11-12

– ምልክቶችና ድንቆችን ማድረግ ይችላል – 2ተሰ 2፡8-9፤ ራዕ 13፡11-15

– የአጋንንት ጥናት (ሥነ-አጋንንት በተጨማሪ ይመልከቱ – ክፍል ሐ5)

3) የሰይጣን ኀይልና የስልጣን ገደብ

– ኢየሱስ የሰይጣንን ሥራ ለማፍረስ መጣ – ዕብ 2፡14፤ 1ዮሐ 3፡8

– ኢየሱስን የፈተነበት ወጥመድ አልተሳካም – ሉቃስ 4፡13

– ሰይጣን በኢየሱስ ላይ ምንም ኀይል የለውም – ዮሐ 14፡30

– ኢየሱስ ርኩሳን መናፍስትን አስወጥቷል – ሉቃስ 11፡20፤ 13፡32

– ደቀ መዛሙርት አጋንንትን ያወጡ ዘንድ ኀይል ተሞልተው ነበር – ማቴ 10፡1፤ ማር 16፡17

– በእኛ ያለው ኢየሱስ በአለም ካለው ሰይጣን ይበልጣል – 1ዮሐ 4፡4

– ኢዮብን ለመፈተን የእግዚአብሔር ፈቃድ ማግኘት ነበረበት – ኢዮብ 1፡9-12

– የሰይጣን አጋንንቶች፣ አሳማ ውስጥ ለመግባት ፈቃድ ማግኘት ነበረባቸው – ማቴ 8፡30-32

– ስልጣኑ በመስቀሉ አማካኝነት ተገፏል – ቆላ 2፡15

4) ሰይጣንን በተመለከተ የቅዱሳን ሚና

– መላዕክትን ማምለክ አይገባቸውም – መሳ 13፡16-18፤ ቆላ 2፡18፤ ራዕ 19፡10፤ 22፡8-9

– ሰይጣንና መላዕክቱ መመለክ ይሻሉ – ማቴ 4፡8-10

– ሰይጣንን ተቃወሙት ከእናንተ ይሸሻል – ያዕ 4፡7፤ 1ጴጥ 5፡9

– ሰይጣንን ለመቃወም እቃ ጦርን ሁሉ ልበሱ – ኤፌ 6፡11-16

– እግዚአብሔር በፈቀደለት መጠን ቅዱሳን በሰይጣን መከራ ይደርስባቸዋል – ኢዮብ 1፡12፤ 2፡4-7፤ 2ቆሮ 12፡7-9

– ሊነቁ ይገባቸዋል – 2ቆሮ 2፡11

– ሰይጣንን ማሸነፍ አለባቸው – 1ዮሐ 2፡13፤ ራዕ 12፡10-11

– በኢየሱስ ደም

– በእግዚአብሔር ቃል

– እስከ ሞት ድረስ ለፍሳችንን ባለመውደድ

– ሰይጣንን የማሸነፍ ተሰፋ ተሰጥቶናል – ሮሜ 16፡20

– ርኩሳን መናፍስትን የማዘዝ ኀይል አለን – ሉቃስ 10፡18-20

– የእግዚአብሔር ቃል፣ ሰይጣንን ለማሸነፍ የመጀመሪያ መሣሪያችን ነው – ሉቃስ 4፡8፣ 10፣ 12

ረ. አጋንንትና ሥነ-አጋንንት

ስለ አጋንንት ያለንን አስተሳሰብ በጥንቃቄ ልናጤነው ይገባናል፡፡ ስለ አጋንንት አለሙ የሚያምናቸው በርካታዎቹ እውቀቶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደሉም፡፡ 1ዮሐ 4፡1 በሐሰተኛ ነቢያትና በክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ የተሰራጩ በርካታ ሃሰተኛ ትምህርቶች እንዳሉ ይነግረናል፡፡

1) አጋንንት ምንድን ናቸው?

– ‹‹ርኩስ መናፍስት›› እና ‹‹ዲያብሎስ›› ተብለው ተጠርተዋል – ማቴ 4፡24፤ 7፡22፤ ማር 9፡25

– መናፍስት ሥጋና አጥንት የላቸውም – ሉቃስ 24፡39

– የሙታን መንፈሶች አይደሉም – ሉቃስ 16፡27-31

– ሃብታሙ ሰው ወደምድር መመለስ አልቻለም

– በርካታ ክርስቲያኖች አጋንንት የወደቁት መልአኮች እንደሆኑ ያምናሉ

– የወደቁት መላእክቶች በአሁኑ ሰአት በእግዚአብሔር ታስረዋል – ይሁዳ 6፤ 2ጴጥ 2፡4

– የዲያብሎሶች አለቃ ብኤልዚቡል ይባላል – ማር 3፡22

– ከሰይጣን መጠሪያ ስሞች አንዱ እንደሆነ ይታመናል

– አጋንንት እግዚአብሔር እንዳለ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል – ያዕ 2፡19

– ደቀ መዛሙርት መናፍስትን ፈርተው ነበር – ማቴ 14፡26፤ ሉቃስ 24፡37

– ይህ የሆነው በመንፈስ ቅዱስ ከመሞላታቸው በፊት ነበር

– አጋንንት ሰዎችን ለማሳት ተአምራትን መሥራት ይችላሉ – ራዕ 16፡1

2) ሰዎች እንዴት ባለ ሁኔታ ከአጋንንት ጋር ሕብረት ይፈጥራሉ?

– ብዙ ጊዜ የማያምኑ ሰዎች መስዋእት ያቀርቡላቸዋል – 1ቆሮ 10፡20-21፤ ዘዳ 32፡17

– አጋንንት፣ ሰዎችን በኀጢአት የሚፈትኑ አታላይ መናፍስቶች ናቸው – 1ጢሞ 4፡1

– በመጨረሻው ዘመን የአጋንንት የክፋት ተግባራቸው ይባባሳል

– ሰዎች የአጋንትን ዶክትሪን ሊያስተምሩ ይችላሉ – 1ጢሞ 4፡1-5

– መጋባትን መከልከል እና የተወሰኑ ምግቦችን ብቻ መመገብ

– ሰዎች በአጋንንት ቁጥጥር ስር ሊገቡ ወይም አጋንንት በውስጣቸው ሊያድሩ ይችላሉ

– ከታች ባለው ጥቅስ ውስጥ ይመልከቱ – አጋንንት በእንስሳዎችም ውስጥ ሊያድሩ ይችላሉ – ማቴ 8፡30-32

3) ሰዎች እንዴት አጋንንት ይገቡባቸዋል?

– ሰዎች ጣኦታትን በማምለክና በሥጋ ስራቸው አማካኝነት በአጋንንት ሊያዙ ይችላሉ፡፡ 1ቆሮ 10፡20፣ 21፤ ገላ 5፡19-21 (ያስተውሉ፡- ጣኦትን ማምለክና ሴሰኝነት ይዛመዳሉ፣ አብረው የሚሄዱ ነገሮች ናቸው፡፡

– በኀጢአት ልማድ ውስጥ ያሉ ሰዎች አጋንንት ሊያድሩባቸው ይችላሉ – ዮሐ 5፡14

– ሃሰተኛ ሃይማኖቶች ሰዎችን በማሳት ለአጋንንት ሃይል እንዲጋለጡ ሊያደርጓቸው ይችላሉ፡፡

– ሰይጣን አሳችና ፈታኝ ነው – ራዕ 12፡9፤ 1ተሰ 3፡5

– ይቅር አለማለት አሰቃዮችን (አጋንንትን) ሊጋብዝ ይችላል – ማቴ 18፡34፣ 35

– ጌታ ወደማይታዘዙት አጋንንትን ሊልክባቸው ይችላል – ንጉሥ ሳኦልን ያሰቃዩት ዘንድ – 1ሳሙ 16፡14-16

– በሐሰተኛ ነቢያት አፍ ውስጥ ሃሰትን ይናገሩ ዘንድ – 1ነገ 22፡23፤ 1ዮሐ 4፡1

– ክፉ መናፍስት ባዶ ወደ ሆነ ሰው ሕይወት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ – ማቴ 12፡44-45

– ነፃ የወጣ ሰው ባዶ ነው – ማቴ 12፡44

– ባዶ በሆነ ሕይወት ውስጥ ከቀድሞ የበዛ ክፉ መናፍስት ሊገቡ ይችላሉ – ማቴ 12፡45

ማስታወሻ – ይህ ሃሳብ ከማያምኑ ሰውች ውስጥ አጋንንት ለማውጣት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

– በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ይጠበቅብናል – ሐዋ 2፡4፤ ኤፌ 5፡18

– አማኞች እግዚአብሔርን በመጠየቅ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበሉ ይችላሉ – ሉቃስ 11፡13

– ሰው ሰይጣንን በመጠየቅ ርኩስ መንፈስን ሊቀበል ይችላል

– የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ስሕተት ነው፡-

– ከርኩሳን መናፍስት ጋር ግንኙነት መፍጠር – 2ዜና 33፡6፤ 1ቆሮ 10፡20-21

– ዲያብሎስን ማምለክ – ራዕ 9፡20

– መላእክትን ማምለክ – ቆላ 2፡18

4) ብሉይ ኪዳንና አጋንንቶች

– በብሉይ ኪዳን አጋንንት ሲወጡ የሚያሳይ ማስረጃ የለም

– ኢየሱስ ‹‹ኃይለኛውን ሰው›› (ሰይጣንን) ሳያስሩ ንብረቱን መዝረፍ አይቻልም አለ – ማር 3፡27

– ኃይለኛው ሰው (ሰይጣን) ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት አልታሰረም፡፡ ይህ ለማድረግ ጭምር ነበር ኢየሱስ የመጣው – 1ዮሐ 3፡8

– አጋንንትን ማውጣት የእግዚአብሔር መንግስት መምጣት ምልክት ነው – ማቴ12፡28 ፤ ሉቃስ 11፡20

5) በአጋንንት የተያዙ ሰዎች ምን ይመስላሉ?

– ብርቱ ሃይል ሊኖራቸው ይችላል – ማቴ 8፡28፤ ማር 5፡3-4፤ ሉቃስ 8፡29፤ ሐዋ 19፡15-16

– ሰውየው ራሱን ሊጎዳ ይችላል – ማቴ 17፡15፤ ማር 5፡5

– ሊታመምና ሊጎዳ ይችላል – ማር 9፡20

– አረፋ ሊደፍቅ ይችላል – ማር 9፡20

– እንደ መምህራን በቤተ ክርስቲያን ሊቀርቡ ይችላሉ – 1ጢሞ 4፡1-5

– ንጉሥ ሳኦል በክፉ መንፈስ በተሰቃየ ጊዜ ትንቢት ተናገረ – 1ሳሙ 18፡10

– አጋንንት በያዙት ሰው አፍ ሊናገሩ ይቻላሉ – ማቴ 8፡29-31፤ ማር 1፡24

– አጋንንት ስለ ኢየሱስ ሊናገሩ ይችላሉ – ማር 1፡24፤ ሐዋ 16፡16፣ 17

– ኢየሱስ ብዙ እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም – ማር 1፡34

– የዲያብሎስን አሳች ቃላት እንዳናደምጥ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

– ባልተለመዱ ስፍራዎች ሊኖሩ ይችላል (በምድረ በዳ፣ በመቃብር ሥፍራ) – ሉቃስ 8፡27

– እርቃናቸው ሊሄዱ ይችላሉ – ሉቃስ 8፡27

– በሥጋ በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ

– ድዳነት – ማር 9፡17

– እውርነትና ድዳነት – ማቴ 12፡22

– ማንዘፍዘፍ (ማንፈራገጥ) – ማር 1፡26፤ 9፡20፤ ሉቃስ 9፡39

– ድንቁርናና ድዳነት – ማር 9፡25

– ሽባነትና አንካሳነት – ሐዋ 8፡7

– የጣኦታት አምላኪዎች ሊሆኑ ይችላሉ – ዘሌ 17፡7፤ ዘዳ 32፡17፤ ራዕ 9፡20

– ጠንቋዮች ሊሆኑ ይችላሉ – ዘሌ 21፡27፤ ሐዋ 16፡16

– በመተትና አስማት ሥራ ሊሳተፉ ይችላሉ – ኢሳ 47፡9-13፤ ሐዋ 19፡18-19

– የሙታን መንፈሶችን ሊጠሩ ይችላሉ – 1ሳሙ 28፡11-14

6) አማኞች እንዴት ባለ ሁኔታ አጋንንትን ያስወጣሉ?

– መጽሐፍ ቅዱስ አጋንንት የሚወጡበትን መመሪያ (ቀመር) አይሰጥም፡፡

– ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ስልጣንን ሰጣቸው – ማር 16፡17

– ለ12ቱ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ጭምር – ዮሐ 17፡20-23

– ኢየሱስ እንዲወጡ አዘዛቸው – ማር 1፡25፤ 9፡25

– በእግዚአብሔር መንፈስ /በእግዚአብሔር ጣት – ማቴ 12፡28፤ ሉቃስ 11፡20

– ኢየሱስ አጋንንት እንዲያወሩ አልፈቀደላቸውም – ማር 1፡34፤ ሉቃስ 4፡41

– ኢየሱስ ስልጣንን ለደቀ መዛሙርቱ ሊሰጥ ችሎ ነበር – ማቴ 10፡1

– ውጤታማ ለመሆን ደቀ መዛሙርት እምነት ያስፈልጋቸው ነበር – ማቴ 17፡19-20

– ደቀ መዛሙርት አጋንንትን በኢየሱስ ስም አዘዟቸው – ማር 16፡17

– ጾምና ጸሎት ሊያስፈልግ ይችላል – ማር 9፡29

– ፈውሱን በሚጠይቀው ሰው ዘንድ እምነት ያስፈልጋል – ማር 6፡5-6፤ 9፡23-24

– አንዳንድ ጊዜ ግን ይህ እምነት አስፈላጊ አይሆንም – ሐዋ 16፡16-19

– በጳውሎስ መሐረብና ሰውነቱን በነካ ጨርቅ አጋንንት ይወጡ ነበር – ሐዋ 19፡11-12

– የማያምኑ ሰዎች አጋንንትን ለማውጣት በሞከሩ ጊዜ ተጎድተው ነበር – ሐዋ 19፡13-16

– የኢየሱስን ስም ተጠቀሙ – ሐዋ 19፡13

– ኢየሱስን ግን አያቁትም ነበር – ሐዋ 19፡13

– አጋንትን ከማያምን ሰው ማውጣት

– በሰውየው ላይ የከፋ ችግር ሊያመጣበት ይችላል – ማቴ 12፡44-45

7) አጋንንት በሽታ ሊያመጡ ይችላሉን?

– አጋንንት አካላዊ በሽታ ሊያመጡ ይችላሉ – ከላይ በ ‘ሠ’ ስር የቀረበውን ይመልከቱ

– መጽሐፍ ቅዱስ መፈወስንና አጋንት ማስወጣት ለይቶ ያቀርባል – ማቴ 4፡24፤ 10፡8፤ ማር 1፡32፤ 3፡15፤ ሉቃስ 9፡1-2፤ 13፡ 32 – ከአጋንንት ጋር ያልተያያዙ አካላዊ ፈውሶች

– የሚጥል በሽታና ሽባነት – ማቴ 4፡24

– የመቶ አለቃው ባርያ – ማቴ 8፡5-13

– ሁለት አይነ ስውራን – ማቴ 9፡27-30

– ለምጽ – ማቴ 8፡3

– ደም ሲፈሳት የነበረች ሴት – ማቴ 9፡19-20

– እጁ የሰለለበት – ማቴ 12፡9-14

7. የክፋትና የአስማት ሰራተኞች

ሀ) ምዋርት (ጥንቆላ፣ አስማት፣ መናፍስት መጥራት)

የአሕዛብ አገሮች አስማትን፣ ምዋርትንና የሙታን መንፈስ መሳብን ተለማምደዋል፡፡

– የኀጢአተኛ ባሕሪ ((አዳማዊ ባሕሪ) ተግባራት (ጥንቆላ) – ገላ 5፡19-21

– በልዓም ለምዋርቱ ዋጋን ተቀበለ – ዘኁ 22፡7

– ፍልስጤማዊያን ምዋርተኞች ነበራቸው – 1ሳሙ 6፡2

– የባቢሎን ንጉሥ ምዋርትን ተጠቅሟል – ሕዝ 21፡21-23

– ፈርኦን አስማተኞቹን አማክሮ ነበር – ዘፍ 41፡24

– የናቡከደነጾር አስማተኞች ሕልሙን ሊፈቱ አልቻሉም – ዳን 2፡2፤ 4፡7

– በርያስስ ወይም ኤልማስ ጠንቋይ ነበር – ሐዋ 13፡6-12

– የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት ሴት – ሐዋ 16፡16

– በኤፌሶን የጥንቆላ መጻሕፍት ተቃጠሉ – ሐዋ 19፡17-20

– የእርኩሷ ከተማ ባቢሎን አስማት – ራዕ 18፡23

የተከለከለና በእግዚአብሔር የሚያስቀጣ ነው

– ማንኛውም አይነት አስማት ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው – ዘዳ 18፡9-13

– አስማትና ከሙታን መንፈስ ጋር ማውራት በእግዚአብሔር የተከለከለ ነው – ኢሳ 8፡19-20

– የምስራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮና ምዋርት በፍርድ ስር ሆንዋል – ኢሳ 2፡6

– እግዚአብሔር መተተኞችን አጠፋለሁ በማለት ዝቷል – ሚክ 5፡12

– በእግዚአብሔር አይን ሁሉም የጣኦት አምል አፀያፊ ነው – 2ነገ 17፡17

– እግዚአብሔር በመተተኞች ላይ ይፈርዳል – ሚኪ 3፡5

– አስማተኞች ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም አይገቡም – ራዕ 21፡8

– እግዚአብሔር መናፍስት ጠሪዎችን ይቃወማቸዋል – ዘሌ 20፡6

– ሳኦል የሳሙኤልን የሙት መንፈስ ፈለገ – 1ሳሙ 28፡11

– ሳኦል መናፍስት ጠሪን ስለጠየቀ ሞተ – 1ዜና 10፡13

– መተተኛ በሕይወት እንዲኖር አይፈቀድለትም ነበር – ዘጸ 22፡18

– ወደመናፍስት ጠሪዎና ጠንቋዮች መሄድ ያረክሳል – ዘሌ 19፡31

ለ) ሐሰተኛ ምልክቶችና ተአምራት

– የሰይጣን አገልጋዮች አስደናቂ ምልክቶች ሊያደርጉ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22

– በሕገወጥ መሪዎች ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 7፡22-23

– የመጨራሻው ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 24፡24

– ሁለተኛው አውሬ ድንቅና ታላላቅ ተአምራቶችን ያደርጋል – ራዕ 13፡13

– ስድስት የቁጣ ድንቆች – አጋንንት ድንቅን ያደርጋሉ – ራዕ 16፡13-14፤ 19-20

ሐ) እግዚአብሔር ከአስማት ሃይል በላይ ብርቱ ነው

– የፈርኦን አስማተኞች ተአምራትን አደርገዋል – ዘጸ 7፡11

– አስማተኞቹ ከውሃ ውስጥ ጓጉንቸሮች እንዲወጡ አደረጉ – ዘጸ 8፡7

– ሳኦል የገለጋት በዓይንዶር ትገኝ የነበረች መናፍስት ጠሪ – 1ሳሙ 28፡7-9

– ጠንቋዮ ስምኦን – ሐዋ 8፡9-11

– ሐሰተኛ ነቢይና ጠንቋዩ በርያስስ ወይም ኤልማስ – ሐዋ 13፡6-8

– የጥንቆላ መንፈስ የነበረባት ሴት – ሐዋ 16፡16

1 thought on “ሰይጣን – አጋንንት”

  1. Pingback: ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት | Apostolic Servant of Lord

Leave a Reply

%d bloggers like this: