ሀ) መከራዎች
– እዚህ ላይ የምናነሳቸው መከራዎችን ፈተናዎች በኀጢአታችን ምክንያት በሕይወታችን ላይ የሚመጡትን መከራዎች ሳይሆን በጽድቅ ሕይወታችን ምክንያት ልንታገሳቸው የሚገቡትን የመከራ አይነቶች ነው፡፡
– ኢዮብ የሰይጣንን ውጊያ ተቋቋመ – የኢዮብ መጽሐፍ
– የብሉይ ኪዳን አማኞች ሃይለኛ መከራዎችን አሳልፈዋል – ዕብ 11፡36-40
– በርካታ የዚህ ዘመን አማኞችም መከራን ይቀበላሉ
– መከራ ሊያጠራን ይመጣል – ያዕ 1፡2-5፤ 1ጴጥ 1፡6-7
– የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ነን – 1ጴጥ 4፡12-16
– እግዚአብሔር ጻድቃንን ከመከራቸው ሊያድናቸው ይችላል – 2ጴጥ 2፡7-9
ለ) ፈተናዎች
ፈተናዎች ኃጢአት አይደሉም ነገር ግን ሰይጣን ኀጢአት እንድናደርግ ፈተናዎችን ይጠቀማል፡፡ ኀጢአት እንድናደርግ የሚቀርቡልንን ፈተናዎች ጸንተን ልንቃወማቸው ይገባል፡፡
– እግዚአብሔር ኀጢአትን እንድናደርግ አይፈትነንም – ያዕ 1፡13-15
– እግዚአብሔር ከፈተና የምናመልጥበትን መውጫ ያሳየናል – 1ቆሮ 10፡13፤ 2ጴጥ 2፡9
– ሰይጣን ዋነኛው ፈታኝ ነው
– ሰይጣን ሔዋንን በኤደን ፈተናት – ዘፍ 3፡1-7
– ሰይጣን ንጉሥ ዳዊትን ፈተነው – 1ዜና 21፡1-30
– ሰይጣን እኛን ይፈትናል – 2ቆሮ 2፡10-11፤ 11፡3፤ 1ተሰ 3፡5
– አለም ፈተናን ያቀርባል – 1ዮሐ 3፡15-17፤ ማቴ 13፡22፤ ሉቃስ 8፡13
– ብልጥግናን መውደድ አደገኛ ወጥመድ ነው – 1ጢሞ 6፡9-11
– አካን የባቡሎንን ብልጥግና ለራሱ ወሰደ – ኢያሱ 7፡1-26
– ሎጥ በሶዶም ዙሪያ ያለውን አካባቢ ተመኘ – ዘፍ 13፡10-13
– ንጉሥ ሳኦል የአማሌቃውያንን ምርጥ ከብቶች አስቀረ – 1ሳሙ 15፡20-26
– የኤልሳዕ ሎሌ ግያዝ ወርቅና ልብስን ለራሱ አስቀረ – 2ነገ 5፡20-27
– የገዛ ክፉ ምኞቶቻችን ያጠምዱናል – ያዕ 1፡14
– ምኞት ኀጢአትን ይወልዳል – ያዕ 1፡15
– ኀጢአት ካደገች በኃላ ሞትን ትወልዳለች – ያዕ 1፤ 15
– ኤሳው ስለምግብ ብኩርናውን ሸጠ – ዘፍ 25፡29-33
– ለሴቶች ያለው ከፍተኛ ምኞት፣ ንጉሥ ሰለሞንን ችግር ውስጥ ጣለው – 1ነገ 11፡1-4
– ኢየሱስ እንደ እኛ በሁሉ ነገር ተፈተነ – ዕብ 4፡15
– ኢየሱስ በዲያብሎስ ተፈተነ – ማቴ 4፡1፤ ማር 1፡3፤ ሉቃስ 4፡2
– በሰውነቱ – የሰውነቱን ፍላጎት እዲያረካ – ማቴ 4፡2፡4
– በነፍሱ – ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን የተለየ ግንኙነት እንዲያሳይ – ማቴ 4፡5-7
– በመንፈሱ – ሰይጣንን በማምለክ ሃይልን እንዲቀበል – ማቴ 4፡8-10
– ከፈተና ለመራቅ መጸለይ አለብን – ማቴ 6፡13፤ ሉቃስ 11፡4
– በኀጢአት ውስጥ ገብተው ያሉትን በምትረዱበት ወቅት እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ – ገላ 6፤ 1
– ፈተናዎችን መቋቋም አለብን – ምሳሌ 1፤ 10፤ ሮሜ 6፡13፤ ኤፌ 6፡13
– ኤልሳዕ ንዕማንን ከፈወሰ በኋላ ገንዘብ አልተቀበለም – 2ነገ 5፤ 16
– ጴጥሮስ የእግዚአብሔርን (የመንፈስ) ስጦታ በገንዘብ አልሸጠም – ሐዋ 8፡20
– ኢዮብ የባለቤቱን ክፉ ምክር ተቋቋመ – ኢዮብ 2፡9-10
– ሬካባዊያን ወይን ከመጠጣት እንቢ አሉ – ኤር 35፡5-6
– ዳንኤልና ጓደኞቹ የንጉሡን ምግብ አንመገብም አሉ – ዳን 1፡8