ሀ) ሃጢአት ማለት ምን ማለት ነው?
የሚከተሉት ንዑስ ርዕሶች ኀጢአትን ይበይናሉ፡፡ ኀጢአት በእግዚአብሔር ማመጽ ማለት ነው፡፡ ሁሉ ኃጢአትን ስለሠሩ (ሮሜ 3፡23)፣ ከእግዚአብሔር ፍቅር በመለየት ሁሉም ከአግዚአብሔር ጋር ጠላቶች ሆነዋል – ዘዳ 9፡7-8፤ ኢያሱ 1፡18፤ ኢሳ 59፡2
– የመጀመሪያው ኀጢአት ግንኙነታችንን አበላሸ – ዘፍ 3፡1-24
– ጣኦትን ማምለክ ኃጢአት ነው – ዘጸ 32፡31፤ 1ነገ 12፡28-30፤ ኢሳ 31፡7፤ ኤር 17፡3፤ 32፡3፤ 32፡35፤ ሕዝ 23፡49፤ ሆሴዕ 13፡2
– ለሃሰተኛ አማልክት ዕጣን ማጠን ኃጢአት ነው- ኤር 44፡23
– ጥንቆላ ኃጢአት ነው- 1ሳሙ 15፡23
– ሕግን መተላለፍ ኃጢአት ነው – ዘሌ 16፡16፤ ነህ 1፡6-7፤ 1ዮሐ 3፡4
– ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት አለመታዘዝ ኃጢአት ነው – ዘጸ 9፡27፣ 34፤ 10፡16-17፤ ዘሌ 5፡17
– ኀጢአት ባለማስተዋል (ሳያውቁ) ሊሰራ ይችላል – ዘሌ 4፡2፣ 13፣ 22፣ 27፤ 5፡15፣ 17
– ኀጢአት በድብቅ ሊሰራ ይችላል – መዝ 90፡8፤ ምሳሌ 28፡13
– ዐመጽ ሁሉ ኃጢአት ነው- 1ዮሐ 5፡17
– ወሲባዊ ኢ-ሞራላዊነት ኃጢአት ነው፣ ትዳርና ቤተሰብ የሚለውን ርዕሰ ጉዳዩ ይመልከቱ – ክፍል ሰ9.
– ግብረ ሰዶማዊነት ኃጢአት ነው – ዘፍ 9፡22፤ 18፡20፤ 19፡5-9፤ ዘሌ 18፡22፤ ሮሜ 1፡24-27፤ 1ቆሮ 6፡9
– ከእንስሳት ጋር ወሲብ መፈጸም ኃጢአት ነው – ዘሌ 18፡23
– ከዘመድ ጋር ወሲብ መፈጸም – ዘፍ 19፡33-39፤ ዘሌ 18፡6-20
– በዘመድ መካከል በተደረገ ግንኙነት የተገኘ ዘር ኀጢአት ነው (ሞአብና አሞን) – ዘዳ 23፡3፤ መሳ 10፡6፤ 1ነገ 11፡4፣ 7፤ 2ነገ 21፡
– ምንዝርና ኃጢአት ነው – ማቴ 5፡32፤ ሐዋ 15፡20-29፤ 1ቆሮ 5፡1፣ 11፤ 10፡8
– ጣኦት ማምለክ ኃጢአት ነው – ዘፍ 20፡7-9፤ 39፡7-10፤ 1ቆሮ 6፡9፤ 7፡2፤ ገላ 5፡19
– መልካምን ነገር ማድረግ እንዳለብን እያወቅን አለማድረግ ኃጢአት ነው – ዘሌ 5፡1፤ ያዕ 4፡17 (ባለማድረግ የሚሠራ ኀጢአት)
– የስንፍና አሳብ ኃጢአት ነው – ምሳሌ 24፡9
– ከንቱ ንግግር ወይም የቃል ብዛት ኃጢአት ነው – ምሳሌ 10፡19
– ንቀት፣ ትዕቢት ኃጢአት ነው – ምሳሌ 14፡21፤ 21፡4
– አለማመን እና ያለእምነት የሚደረግ እርምጃ (ድርጊት) ኃጢአት ነው – ሮሜ 14፡23፤ ዕብ12፡16፤ ራዕ 2፡14፣ 20፤ 9፡21
ለ) ኀጢአት በሚከተሉት መንገዶች ተገልጿል
– በአዳም አማካኝነት ወደ አለም ገባ – ዘፍ 3፡1,24፤ ኢሳ 43፡27፤ ሮሜ 5፡12
– የዲያብሎስ ነው – 1ዮሐ 3፡8፤ ዮሐ 8፡44
– የጨለማ ሥራ ነው – ኤፌ 5፡11-14
– ለማጥቃት በበር ቆሞ ያደባል – ዘፍ 4፡7
– ከልብ ይመነጫል – ማቴ 15፡19-20
– የምኞት ውጤት ነው – ያዕ 1፡15
– በዘር በኩል ይመጣል – ዘጸ 20፡5፤ መዝ 37፡28፤ ምሳሌ 14፡11
– የሰው ልጆች መከራና ጭንቀት ምክንያት ነው – ኢዮብ 15፡20፤ ምሳሌ 13፡15፤ ሮሜ 2፡9ማመካኛ የለውም – ሮሜ 1፡20፤ 2፡1፤ ዮሐ 15፡22
ሐ) ኀጢአት ያደረገ ወይም ያለበት ማነው?
– ኀጢአትን ያላደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው – 2ቆሮ 5፡21፤ ዕብ 4፡15፤ ዕብ 7፡26፤ 1ዮሐ 3፡5
– ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የሰው ልጅ ከኀጢአት በታች እንደሆኑ ይናገራሉ – ገላ 3፡22፤ መዝ 53፡3 ፤ ኢሳ 53፡6
– ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋል – 1ዮሐ 1፡8፤ 1ነገ 8፡46፤ ሮሜ 3፡23
– በዘር ሁላችን ኀጢአተኞች ነን – ኢዮብ 15፡14፤ ኢዮብ 25፡4፤ መዝ 51፡5፤ ሮሜ 5፡12-19፤ 1ቆሮ 15፡21-22
– ሴት የኀጢአተኛው አዳም አምሳል ነበር – ዘፍ 5፤ 3
– በሁለንተናችን ኀጢአትን ሰርተናል
– በተግባራችን (በአካላችን /በሰውነታችን) – ገላ 5፡17-21
– በዝንባሌዎቻችን (በነፍሳችን) – ማቴ 5፡21-22፤ ያዕ 2፡8-9
– በኀጢአት ሁኔታ ውስጥ ነን (በመንፈሳችን) – ዮሐ 16፡8-9
– ስለዚህ ሁሉ ኀጢአተኛ ነው – ሮሜ 3፡23
መ) የኀጢአት ውጤት
– ከእግዚአብሔር ይለያል – ዘፍ 3፡23፣ 24፤ ኢሳ 59፡2
– ኀጢአተኞችን ከመንግስተ ሰማይ ይለያቸዋል – 1ቆሮ 6፡9፤ ገላ 5፡19-21፤ ኤፌ 5፡5-7፤ ራዕ 21፡27
– ሞትን ያመጣል – ዘፍ 3፡2-3፤ 19፤ ያዕ 1፡15፤ ሮሜ 6፡23፤ ሕዝ 18፡4
– የእግዚብሔርን ቁጣ ያመጣል – ዘጻ25፡16፤ ምሳሌ 6፡16-19፤ 1ነገ 16፡2
– የእግዚአብሔርን እርግማን ያመጣል
– ምድር በኀጢአት ምክንያት ተረገመች – ዘፍ 3፡17-18
– ድካምና ላብ የኀጢአት ውጤቶች ናቸው – ዘፍ 3፡16፣ 17፣ 19፤ ኢዮብ 14፡1
– በምጥ ጊዜ ሕመም የኀጢአት ውጤት ነው – ዘፍ 3፡16
– ፍጥረት በእስራት ውስጥ – ሮሜ 8፡21-22
– አደጋ ያስከትላል
– ድርቅ – ኤር 5፡24፤ 2ዜና 6፡26-28፤
– ጦርነት – 2ዜና 6፡36-39
– በሽታ – መዝ 38፡3
– አገራዊ ችግር – ምሳሌ 14፡34፤ ኤር 8፡14-16፤ 2ዜና 25፡4
– የእግዚአብሔርን ፍርድ ያመጣል
– የአሁን ጊዜ – ኢሳ 13፡11፤ አሞፅ 3፡2፤ ኤር 5፡25፤ ሉቃስ 12፡47፤ ሮሜ 2፡8-9
– የሚመጣ ጊዜ ቅጣት – ማቴ 18፡18፤ ማር 3፡29፤ ሉቃስ 3፡17፤ 2ተሰ 1፡9፤ 2ጴጥ 2፡9፤ ራዕ 14፡11፤ ራዕ 20፡15
ሠ) ለኀጢአት ችግር እግዚአብሔር ያዘጋጀው መፍትሄ
– ወንጌል የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ረ3 ፣ ረ4 ፣ ረ5
– ድነት የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ሠ2
– ሞትና የመጨረሻው ዘመን የሚለውን ርዕስ ይመልከቱ – ክፍል ሸ
Pingback: ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት | Apostolic Servant of Lord