የተዋጀ ሰውና የእግዚአብሔር መንግስት

ሀ) የሰው ዘር በሙሉ ወደእግዚአብሔር መንግስት እንዲገባ ተጋብዟል

– እግዚአብሔር የአለም ሕዝብ ሁሉ አምላክ መሆኑ – ዘኅ16፡22፤ 27፡16

– እስራኤላዊ ያልሆኑ ሕዝቦች በኢየሱስ ደም ወደዚህ መንግስት መጠራታቸው – ኤፌ 2፡11-22

– በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መውረድ – ኢዩ 2፡28፤ ሐዋ 2፡17

– መንግስተ ሰማይ ከው ዘር ሁሉ የተዋጁ ሰዎች መኖሪያ መሆኗ – ሮሜ 5፡9

– የሰው ዘር በሙሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘታቸው – ሐዋ 10፡34-35

– የኢያሪኮዋ ረዓብ – ኢያሱ 2፡1፤ 6፡17፤ ዕን 11፡31፤ ያዕ 2፡25

– ሞአባዊቷ ሩት – የሩት መጽሐፍ

– ሳማሪያዊቷ ሴት – ዮሐ 4፡7-42

– ሲሮፊኒቃዊቷ ሴት – ማር 7፡24-30

– የጴጥሮስ ራዕይ – ሐዋ 10፡9-16

– ሶሪያዊው ንዕማን – 2ነገ 5፡15-19

– ሮማዊው መቶ አለቃ – ማቴ 8፡5-13

– ሮማዊው ቆርነሊዎስ – ሐዋ 10፡17-48

ለ) በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መካተት

– በክርስቶስ በአይሁድና በግሪክ፣ በባሪያና በነጻ ሰው፣ በወንድና በሴት መካከል ምንም ልዩነት የለም – ገላ 3፡28

– ባለጠጎችና ድሆች – ያዕ 2፡4-5

–  አረጋውያን – ዘሌ 19፡32

– ሕፃናት – ማቴ 18፡3፤ 19፡14፤ ሐዋ 2፡39

– ያገቡ ወይም ያላገቡ – 1ቆሮ 7

ሐ) ወደ እግዚአብሔር መንግስት የመግባት ቅድመ ሁኔታዎች

– ትህትና/እንደ ልጅ መሆን – ማቴ 18፡3

– መንፈሳዊ ጥማት – ማቴ 5፡6

– ዳግም መወለድ – ዮሐ 3፡3-5

– ለክርስቶ ፍጹም መሰጠት – ሉቃስ 9፡62

– እምነትና ፍቅር – ያዕ 2፡5

– በፈተና መጽናት – ሐዋ 14፡22፤ 2ተሰ 1፡5

መ) የመንግስቱ ባሕሪ

– ዘላለማዊ – ዳን 2፡44፤ ሉቃስ 1፡33

– የምትሰፋ – ማቴ 13፡31-32

– ሃይለኛ – ማር 9፡1፤ 2ቆሮ 10፡4

– በአሁኑ ጊዜ ያለች – ማቴ 12፡28፤ ሉቃስ 17፡21፤ 12፡32

– በክብር የተሞላች – 1ተሰ 2፡12

– የማትናወጥ – ዕብ 12፡28

– ከዚህ አለም ያልሆነች – ዮሐ 18፡36

– ለሁሉ ወገን የተፈቀደች – ዕብ 5፡9፣ 10፤ ዳን 7፡14

– ስልጣን ያላት – ማቴ 16፡19

– የተደበቀች/የማትታይ – ማቴ 13፡33፤ ቆላ 1፡15፣ 16

– ያለማቋረጥ የምታድግ – ኢሳ 9፡6፣ 7፤ ማቴ 13፡33

– የመላዕክት ሰራዊትን የምታጠቃልል – ዕብ 12፡22፤ ራዕ 5፡11

– በጽድቅ፣ ሰላምና ደስታ የምትታወቅ – ሮሜ 14፡17

– የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚደረግባት ሥፍራ – ማቴ 6፡10

ሠ) መንግስቱ በብሉይ ኪዳን

– የአብርሃም ዘር ታላቅ ሕዝብ መሆኑ – ዘፍ 12፡2

– የአብርሃም ስም የአሕዛብ ሁሉ አባት ተብሎ መለወጡ – ዘፍ 17፡4፣ 5

– እስራኤል ለመንግስትነት መመረጧ – ዘጸ 19፡5፣ 6

– ጌዴዎን ይህን መንግስት ማወቁ – መሳ 8፡23

– እስራኤል መንግስቱን መቃወሟ – 1ሳሙ 8፡7

– አስቴር በእዚህ መንግስት ስር መምጣቷ – አስ 4፡14

– የዳዊት ዘር ይህን መንግስት እንዲወርስ ቃል ተሰጠው – 2ሳሙ 7፡13

– ኢሳይያስ፣ ንጉሡ በመንግስቱ ላይ ሲከብር ማየቱ – 1ሳሙ 6፡2-6

– ዳንኤል ስለመጻኢው መንግስት መተንበዩ – ዳን 2፡44፤ 7፡14

ረ) የእግዚአብሔር መንግስት ሌሎች ስሞች

– መንግስተ ሰማይ (የሰማይ መንግስት) – ማቴ 13፡11

– የክርስቶስ መንግስት – ሉቃስ 22፡30፤ 2ጴጥ 1፡11፤ ኤፌ 5፡5

– የአባታቸው መንግስት – ማቴ 13፡43፤ 26፡29

– የብርሃን መንግስት – 1ጴጥ 2፡9፤ ቆላ 1፡13

– (ቅድስት) ከተማ – መዝ 48፤ ዕብ 11፡16

– (አዲሲቱ) ኢየሩሳሌም – ዕብ 12፡22፤ ሚክ 4፡2፤ ራዕ 21፡2

ሰ) ሌሎች ‹‹መንግስታት›› ማለትም የሰይጣን መንግስት

– የሰይጣን መንግስት – ማቴ 12፡26

– የዚህ አለም መንግስታት – ማቴ 4፡8፤ ራዕ 11፡15፤ ዮሐ 14፡30

– የጨለማ መንግስት – ቆላ 1፡13፤ ራዕ 16፡10 – ባቢሎን – ዳን 4፡29፤ ራዕ 18፡2 –

ኀጢአተኛ መንግስት – አሞፅ 9፡8

– የአሕዛብ መንግስት – ሐጌ 2፡22

ሸ) ክርስቶስና የእግዚአብሔር መንግስት

– ክርስቶስ የመንግስቱ ንጉሥ ሆነ ይነግሳል – 1ጢሞ 6፡15፣ 16

– የኢየሱስ መምጣት የመንግስቱን መመረቅ አብስሯል – ማቴ 4፡17

– ኢየሱስ ብዙውን ጊዜ ስለመንግስቱ ሰብኳል – ማቴ 13

– በአጋንንት ላይ የተገኘው ስልጣን የመንግስቱ መምጣት አብነት ተደርጎ ተወስዷል – ማቴ 12፡28

– የኢየሱስ በምድር ላይ መምጣት መንግስቲቱን አምጥቷታል – ሉቃስ 17፡21

– የኢየሱስ ዳግም ምጽአት የመንግስቲቱን በሙላት መምጣት ያበስራል – ራዕ 11፡15

ቀ) የመንግስቱ ሰዎች

– አገልጋዮች – ማቴ 13፡27፤ 25፡14-46፤ ራዕ 7፡15

– መጻተኞችና እንግዶች – ዕብ 11፡13፤ 1ጴጥ 2፡11

– ልጆች – ማቴ 18፡1-4

– መንፈሳዊ ካህናት – ዘጻ 19፡6፤ 1ጴጥ 2፡9፤ ራዕ 5፡10

በ) የመንግስቱ መርህዎች

ያስተውሉ፡- የመንግስቲቱ በርካታ መርህዎች በምሳሌዎች ቀርበዎል። እነዚህ መርህዎች በእግዚአብሔር እና በአለም መንግስታት መካከል ያለውን የሰፋ የመርህ ልዩነት እንድናይ ይረዱናል፡፡ በሰው ቋንቋ ለመግለጥ እጅግ አዳጋች የሆኑትን እነዚህን እውነታዎች ኢየሱስ በምሳሌ አቅርቦልናል፡፡ ለሚጠፉት እነዚህ ነገሮች ሞኝነት (1ቆሮ 1፡18) ሲሆኑ ሊመረመሩ የሚችሉትም በመንፈስ ብቻ ነው (1ቆሮ 2፡9-13)፡፡

– ከሚቀበል የሚሰጥ ብፁዕ ነው – ሐዋ 20፡35

– የመኖር መንገድ መሞት ነው – ዮሐ 12፡24፣ 25፤ ማቴ 10፡39

– የክብር መንገድ በስቃይ ውስጥ ነው – ሮሜ 8፡17፤ 1ጴጥ 5፡10

– ብርታት በድካም ውስጥ ይገኛል – ዕብ 11፡34፤ 2ቆሮ 12፡9

– የዎሆች ይከብራሉ – 1ጴጥ 5፡5፣ 6፤ ማቴ 5፡5

– የሚሰደዱ ይባረካሉ – ማቴ 5፡11፣ 12

– የተናቁ ይከብራሉ – ኢሳ 53፡3፤ 1ቆሮ 12፡23

– ድሆች ባለጠጎች ናቸው – ሉቃስ 6፡20፤ 2ቆሮ 6፡10፤ 8፡9

– ባሮች ነጻ ናቸው – ሮሜ 6፡18፤ ፊሊ 1፡1

– ሞኝ ጥበበኛ ነው – 1ቆሮ 1፡26፤ 3፡18

– እጅግ በጣም ጥገኛ የሆኑ እጅግ በጣም የበሰሉ ናቸው – ዮሐ 21፡18

– እግዚአብሔር ምናምንቴውንና ከንቱን ነገር ይጠቀማል – ዕን 11፡38፤ ዘጸ 4፡10፤ መሳ 6፡1

Leave a Reply

%d bloggers like this: