ጥንቆላ

ሐ6. የክፋትና የአስማት ሰራተኞች

ሀ) ምዋርት (ጥንቆላ፣ አስማት፣ መናፍስት መጥራት) የአሕዛብ አገሮች አስማትን፣ ምዋርትንና የሙታን መንፈስ መሳብን ተለማምደዋል፡፡ – የኀጢአተኛ ባሕሪ ((አዳማዊ ባሕሪ) ተግባራት (ጥንቆላ) – ገላ 5፡19-21 – በልዓም ለምዋርቱ ዋጋን ተቀበለ – ዘኁ 22፡7 – ፍልስጤማዊያን ምዋርተኞች ነበራቸው – 1ሳሙ 6፡2 – የባቢሎን ንጉሥ ምዋርትን ተጠቅሟል – ሕዝ 21፡21-23 – ፈርኦን አስማተኞቹን አማክሮ ነበር – ዘፍ 41፡24 – የናቡከደነጾር አስማተኞች ሕልሙን ሊፈቱ አልቻሉም – ዳን 2፡2፤ 4፡7 – በርያስስ ወይም ኤልማስ ጠንቋይ ነበር – ሐዋ 13፡6-12 – የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት ሴት – ሐዋ 16፡16 – በኤፌሶን የጥንቆላ መጻሕፍት ተቃጠሉ – ሐዋ 19፡17-20 – የእርኩሷ ከተማ ባቢሎን አስማት – ራዕ 18፡23

የተከለከለና በእግዚአብሔር የሚያስቀጣ ነው – ማንኛውም አይነት አስማት ሥራ በእግዚአብሔር ዘንድ ፈፅሞ የተከለከለ ነው – ዘዳ 18፡9-13 – አስማትና ከሙታን መንፈስ ጋር ማውራት በእግዚአብሔር የተከለከለ ነው – ኢሳ 8፡19-20 – የምስራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮና ምዋርት በፍርድ ስር ሆንዋል – ኢሳ 2፡6 – እግዚአብሔር መተተኞችን አጠፋለሁ በማለት ዝቷል – ሚክ 5፡12 – በእግዚአብሔር አይን ሁሉም የጣኦት አምል አፀያፊ ነው – 2ነገ 17፡17 – እግዚአብሔር በመተተኞች ላይ ይፈርዳል – ሚኪ 3፡5 – አስማተኞች ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም አይገቡም – ራዕ 21፡8 – እግዚአብሔር መናፍስት ጠሪዎችን ይቃወማቸዋል – ዘሌ 20፡6 – ሳኦል የሳሙኤልን የሙት መንፈስ ፈለገ – 1ሳሙ 28፡11 – ሳኦል መናፍስት ጠሪን ስለጠየቀ ሞተ – 1ዜና 10፡13
32

– መተተኛ በሕይወት እንዲኖር አይፈቀድለትም ነበር – ዘጸ 22፡18 – ወደመናፍስት ጠሪዎና ጠንቋዮች መሄድ ያረክሳል – ዘሌ 19፡31

ለ) ሐሰተኛ ምልክቶችና ተአምራት – የሰይጣን አገልጋዮች አስደናቂ ምልክቶች ሊያደርጉ ይችላሉ – ራዕ 16፡14፤ 2ተሰ 2፡9-12፤ ማቴ 24፡24፤ ዘጸ 7፡11፣ 22 – በሕገወጥ መሪዎች ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 7፡22-23 – የመጨራሻው ዘመን ሐሰተኛ ምልክቶችና ድንቆች – ማቴ 24፡24 – ሁለተኛው አውሬ ድንቅና ታላላቅ ተአምራቶችን ያደርጋል – ራዕ 13፡13 – ስድስት የቁጣ ድንቆች – አጋንንት ድንቅን ያደርጋሉ – ራዕ 16፡13-14፤ 19-20

ሐ) እግዚአብሔር ከአስማት ሃይል በላይ ብርቱ ነው – የፈርኦን አስማተኞች ተአምራትን አደርገዋል – ዘጸ 7፡11 – አስማተኞቹ ከውሃ ውስጥ ጓጉንቸሮች እንዲወጡ አደረጉ – ዘጸ 8፡7 – ሳኦል የገለጋት በዓይንዶር ትገኝ የነበረች መናፍስት ጠሪ – 1ሳሙ 28፡7-9 – ጠንቋዮ ስምኦን – ሐዋ 8፡9-11 – ሐሰተኛ ነቢይና ጠንቋዩ በርያስስ ወይም ኤልማስ – ሐዋ 13፡6-8 – የጥንቆላ መንፈስ የነበረባት ሴት – ሐዋ 16፡16

1 thought on “ጥንቆላ”

  1. Pingback: ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት | Apostolic Servant of Lord

Leave a Reply

%d bloggers like this: