ግለሰብ ተኮር የደቀ መዝሙር ማሰልጠኛ ማንዋል

የኢየሱስን ፍቅር ተረድተህ፣ ከዛም በእርሱ ሞትና ትንሳኤ በማመን ከዳንክ በኋላ ሕይወትህን በገዛ ፈቃድህ እንድትመራ የእግዚአብሔር ሃሳብ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ “…በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” ይላል። ኢየሱስን ጌታ ብለሃል እና ከእንግዲህ የራስህ ጌታ አይደለህም። ከኃጢአት ባርነት ነፃ ወጥተህ የክርስቶስ ባሪያ ሆነሃል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ “ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ”።  ለራስህ ፍላጎት ሞተህ የእርሱን ፍላጎት በምድር ላይ ለመኖር ሕያው ሆነሃል። ኢየሱስን በሕይወትህ ላይ ጌታ እንዲሆን ስትሾም፣ የሕይወት ዘመን የክርስቶስ ተከታይ/ደቀ መዝሙር ለመሆን ቃል ገብተሃል። “ደቀ መዝሙሩ ለመሆን ምን ልማር?”፣ “እንዴት ልሰልጥን?”፣ “ምን ላድርግ?” ወዘተ፣ የሚል ጥያቄ ውስጥህ ከመጣ፣ ስጋት አይግባህ። በዚህ ድረ-ገጽ ውስጥ እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችህን የሚመልሱ የማሰልጠኛ ማኑዋሎች ተዘጋጅተውልሃል። ከዚሀ በታች ያሉትን ሊንኮች መመጫን ጥናትህን እንድትቀጥል በአክብሮት እንጋብዝሃለን።

ግለሰብ ተኮር የደቀመዝሙር ማሰልጠኛ ማንዋል- መግቢያ

1ግለሰብ ተኮር የደቀመዝሙር ማሰልጠኛ ማንዋል- የእድገት ደረጃ 1

2ግለሰብ ተኮር የደቀመዝሙር ማሰልጠኛ ማንዋል- የእድገት ደረጃ 2

3ግለሰብ ተኮር የደቀመዝሙር ማሰልጠኛ ማንዋል- የእድገት ደረጃ 3

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading