ሁለተኛው ዙር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ 12/01/2017 በይፋ ተጀምሯል !!!
ጠቃሚ መረጃዎች፡
ይህ ውድድር በኤፌሶን መልዕክት ላይ ያተኩራል።
ማንኛውም ሰው በጥያቄና መልስ ውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላል።
የውድድሩ ዋነኛ ግብ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ለመጥናት አንዳችን ሌላችንን ማበረታታት ቢሆንም በውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው አንድ ግለሰብ ከአዘጋጁ የተዘጋጀለትን ሽልማት ይቀበላል።
ውድድሩ እንደ ተሳታፊዎቹ ጥንካሬ 4 ሳምንትና ከዛ በላይ ሊፈጅ ይችላል።
ውድድሩ ከተጀመረ በኋላ ዘግይተው የሚቀላቀሉ ተሳታፊዎች በውድድሩ መሳተፍ ያሚችሉ ቢሆንም ያለፋቸው የውድድሩ ክፍል ውጤት ከቀሪው ክፍል ጋር አይደምርላቸውም። ይህም ውጤታቸውን አነስተኛ እንዲሆን ያደርገዋል። ስለዚህ ውድድሩን አለማቋረጥም ሆነ በተሰጠው የጊዜ ገዳብ ስርቶ መመልስ ለአሸናፊነት ከሚያበቁ ነገሮች መካከል መሆናቸው የታወቀ ይሁን።
እያንዳንዱን ጥያቄና መልስ ሰርቶ ለመላክ ቢያንስ የአንድ ሳምንት ጊዜ ይኖራል። ይህን የ2ኛ ዙር ክፍል 1 ጥያቄና መልስ ሰርቶ ለመላክ የተሰጠው የጊዜ ገደብ 12/08/2017 ነው።
በውድድሩ ላይ የሚኖርዎትን ማንኛውንም ጥያቄ በሚከተለው የ ኢ-ሜይል አድራሻ ቢልኩልን በተቻልን ፍጥነት ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል፣ tsegaewnet@gmail.com
የውድድሩን ጥያቄዎች በ ፌስ ቡክ ፔጅ (https://www.facebook.com/tesegaewnet/) ወይም በቫይበር ግሩፑ ስር ወይም በዚሁ ዌብ ሳይት ላይ ሊያገኙ ይችላሉ ( https://goo.gl/V343VR )። በቫይበር ግሩፕ ላይ ለመሳተፍ የስልክ ቁጥሬ ለሌላችሁ እነሆ (980) 318-2402።
ከመጀመሪያው ዙር በተለየ ሁኔታ በዚህ ውድድር ላይ በመጨረሻ ላይ ከሚገለጸው አሸናፊ ስም በቀር የማንም ተወዳዳሪ ስም በይፋ አይገለጽም። የተሳታፊዎች ስምም ሆነ የ ኢ-ሜይል አድራሻ በሚስጥር የሚጠበቅ ይሆናል። ስለዚህ በጥያቄና መልሱ ላይ ትክክለኛ ስምዎን መግለጽ ካልፈለጉ የብእር ስምዎን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ነገር ግን አንዴ ይህን ስም መጠቀም ከጀመሩ በኋላ መቀየር አይፈቀድም። የኢ-ሜይል አድራሻዎ ግን ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ። የውድድሩን ጥያቄዎች ከዚህ በታች ያገኛሉ።
መልካም የውድድርና ቃሉን የማጥናት ጊዜ ይሁንልን።