ከፍተኛ አማካይ ወጤት የተመዘገበበት የመጀመሪያው ክፍል 2ኛ ዙር ውጤት

ከፍተኛ አማካይ ወጤት የተመዘገበበት የመጀመሪያው ክፍል 2ኛ ዙር ውጤት ዛሬ ለተሳታፊዎች ሁሉ በኢ-ሜይላቸው እንዲደርሳቸው ሆኗል። የውድድሩ ተሳታፊዎች አማካይ ውጤት (Average) 18.72 / 20 points፣ ሲሆን የመጨረሻው ዝቅተኛ ውጤት ደግሞ 15 ሆኖ ተመዝግቧል። 45% ያሚያክሉቱ ተሳታፊዎች ጥያቄዎቹን ሙሉ በሙሉ በትክክል መመለስ ችለዋል። በቀጣዩ ውድድር ላይ በመጀመሪያው ክፍል ላይ የተሳተፋችሁም ይሁን ክፍሉ ያመለጣችሁ ሁሉ አስቀድሞ በተገለጸው በውድድሩ መመሪያዎች መሰረት መሳተፍ ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቹ ሲለቀቁ እንዳያመልጥዎ ወይም ዘግይቶ እንዳይደርስዎ ይረዳዎ ዘንድ የሚከተለው ድረ-ገጽ (website) (https://ethiopiansite.com/) ላይ በመሄድ እና የኢ-ሜይል አድራሻዎን ከድረ-ገጹ የፊት ገጽ ግርጌ ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ሳጥን ውስጥ በማስገባትና “ድረ-ገጹን ይከታተሉ” የሚለውን ሰማያዊ ቁልፍ በመጫን የድረ-ገጹ ተከታታይ (follower) እንዲሆኑ በአክብሮት እጋብዛለሁ። ይህን ሲያደርጉ፣ የውድድር ጥያቄዎቹና ሌሎች አዳዲስ ጽሁፎች በድረ-ገጹ ላይ በሚለቀቁበት ጊዜ ሁሉ በኢ-ሜል አድራሻዎ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል።

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

Leave a Reply

%d bloggers like this: