Site icon

ፀሎት፣ ለእግዚአብሔር ማሳሰብ

እግዚአብሔር የማያውቀውን ነገር ልንነግረው አንችልም፡፡ ስንፀልይ የምንናደርገው ነገር ቢኖር እርሱ አስቀድሞ የሚያውቀውን ነገር በአንደበታችን ወይም በራሳችን ቃል ለእርሱ መልሶ መናገር ነው፡፡

ይህ ጉዳይ እንድንፀልይ የሚያበረታታን እንጂ ፀሎትን አላስፈላጊ የሚያደርገው አይደለም፡፡ ስለ እኛ እና ስላለንበት ሁኔታ በሚገባ ከሚያውቅ ሰው ጋር ያው የሚያውቀውን ጉዳይ ስናወራ እረፍት ይሰማናል፡፡ የእግዚአብሔር ምላሽ በሰጠነው መረጃ ላይ ሳይሆን እርሱ ስለእኛ ሁኔታ በሚያውቀው ፍፁም እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተደላድለን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ በእኛ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ስለሚችሉ ያለፉ፣ የአሁኑ እና የወደፊቱ ሁኔታዎቻችንን ጠንቅቆ ያውቃልና፡፡

ኢየሱስ በማቴ. 6፡8 ላይ እንዳለው አባታችን ሁሉን ያውቃል፡፡ እርሱ ሃሳቦቻችንንና ፍላጎቶቻችንን ያውቃል፡፡ መንገዶቻችንን ጠንቅቆ ይረዳቸዋል (መዝ. 139፡3)፡፡ የልባችንን ጭንቀትና ስቃይ ያውቃል፤ የማያቋርጥ ተስፋ መቁረጥ የሚያደርስብንን የስሜት ጉዳትም ይገነዘባል፤ በውስጣችን ያሉ ሁለቱ ተቃራኒ ተፈጥሮዎች በነፍሳችን ላይ የሚያደርጉት ጦርነትም ከእርሱ የተሸሸገ አይደለም፡፡

እንዲህ ከሆነ፣ ካሉብን ችግሮችና ተቃውሞዎች እንዴት እና በየትኛው ሰዓት መውጣት እንዳለብን ለማወቅ እግዚአብሔር ላይ የመታመን አስፈላጊነት አይታያችሁም? ሕይወታችን ሊታነፅ የሚችልበትን የተሻለ መንገድ እኛ ለእግዚአብሔር ልንጠቁም የምንችል ይመስላችኋል? በፍፁም፤ እግዚአብሔርን ምንም ነገር ልናስተምረው አንችልም፡፡ እርሱ ብቻውን እኛን ወደ ክብር የሚያደርሰውን ጎዳና ያውቃል፡፡ ካሉት መንገዶች ሁሉ፣ ለማንነታችን እና በእኛ ውስጥ እርሱ ላስቀመጠው ነገር የሚስማማውን ልዩ መንገድ መርጦልናል፡፡

እግዚአብሔርን እውቀት ልናስገበየው አንችልም፡፡ ልናፈቅረውና ልንደላደልበት ግን እንችላለን፡፡ እርሱ ከኛ የሚጠይቀው ይህንን አንድ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመነሻው የመጨረሻውን ያውቃል፤ ስለዚህ በመካከል በሚፈጠሩ ነገሮች ሁሉ ላይ  በእርሱ ልንታመን እንችላለን፡፡ Our Daily Bread (መስከረም 19, 2004 እ.ኤ.አ.)

ፀሎት – ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር

ፀሎት – በ ‹‹ስውር ስፍራ›› የሚደረግ ጦርነት

Exit mobile version