መስከረም 1፣ 2011ዓ.ም የሚጀመርና ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የሚዘልቅ  የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

በኢትዮጵያውያን አዲስ አመት ከመስከረም 1፣ 2011ዓ.ም ጀምሮ አመቱን ሙሉ ሊደረግ በታሰበው መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከዳር በጥልቀት የማጥናት መንፈሳዊ ማእድ ላይ ይታደሙ (ማቴ 4:4)፡፡

ወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት፣ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ መጽሐፍ ድረስ የሚዘልቅና መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጥንቶ ለመጨረስ የሚረዳ ማጥኛ አዘጋጅቶ አጠናቋል፡ በየአመቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከዳር እስከዳር የማንበብ ቁርጠኛ ውሳኔ አድርገው ከሆነ በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስዎን በጥንቃቄ ማንበብዎን የሚመዝኑ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ከመካተታቸው ጎን ለጎን በበርካቶች ዘንድ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎችም ይቀርባሉ፡፡  የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ጥያቄዎቹ እና አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎቹ ከመስከረም 1፣ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት ዌብ ሳይት እና የፌስ ቡክ ፔጅ ላይ በየዕለቱ የሚለቀቁ ይሆናል፡፡

እያንዳንዱ ጥያቄ ሁለት እና ከዛ በላይ አማራጭ ያለው ሲሆን ከአጥኚው የሚጠበቀው፣ መልስ ብሎ ያሰበው አማራጭ ላይ ክሊክ (click) ማድረግ ብቻ ይሆናል፡፡ ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት፣ መመሪያውን በጥንቃቄ ማንበብዎን እና በጥያቄዎቹ የፊት ገጽ ላይ የሚጠየቁትን ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻዎን መሙላትዎን አይዘንጉ። ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻ እንዲሞሉ የተጠየቁበት ምክንያት ውጤትዎ የሚላከው በዚሁ አድራሻ ስለሆነ ነው፡፡ ጥያቄዎቹን ሰርተው ሲያበቁ “submit” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። አንዳንድ ጊዜ “Google” ጥያቄዎቹን የሰራው ኮምፒውተር ወይም ሰው መሆኑን ለማጣራት የሴኪውሪቲ ጥያቄዎችን ሊጠይቆት ይችላል። “Submit” የሚለውን ቁልፍ ከተጫኑ በኋላ በሚከፈትሎት አዲስ ፔጅ ላይ “view your score” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤትዎን እና የተሳሳቱትን ጥያቄ ግብረ መልስ (feedback) ማየት ይችላሉ። ጥያቄዎቹን በድጋሚ ለመስራት የሚሹ ከሆነ ደግሞ “Submit another response” የሚለውን ሊንክ ይጫኑ፡፡

የጥናት ጥያቄዎቹና አጫጭር ትምሕርታዊ ጽሁፎቹ በድረ ገጹ ላይ በሚጫኑበት ጊዜ እንዳያመልጥዎ ወይም ዘግይቶ እንዳይደርስዎ ይረዳዎ ዘንድ የድረ-ገጹ ሆም ፔጅ (https://ethiopiansite.com/)  ላይ በመሄድ እና የኢ-ሜይል አድራሻዎን ከድረ-ገጹ የፊት ገጽ ግርጌ ላይ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው ሳጥን ውስጥ በማስገባትና “ድረ-ገጹን ይከታተሉ” የሚለውን ቁልፍ በመጫን የድረ-ገጹ ተከታታይ (follower) እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። ይህን ሲያደርጉ፣ ጥያቄዎቹና ሌሎች አዳዲስ ጽሁፎች በድረ-ገጹ ላይ በሚጫኑበት ጊዜ ሁሉ በኢ-ሜል አድራሻዎ የማስታወሻ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል።

የሚያነሱት ሃሳብና ጥያቄ ካለ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይላኩልን፤ በተቻለ ፍጥነት ለማስተናገድ ቃል እንገባለን። tsegaewnet@gmail.com

የወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት አዘጋጅ

1 thought on “መስከረም 1፣ 2011ዓ.ም የሚጀመርና ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ የሚዘልቅ  የአንድ ዓመት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት”

  1. Rahel Yeshitila

    የእግዚአብሄር ፀጋ ስለበዛላችሁ : ስሙ ይባረክ:: በጣም ደስ ይላል:: ለእያንዳንዱ chapter summery የሚሆን ነገር ብትጽፉልን መልካም ነው ብዬ አምናለሁ:: ቃሉ ለማን እንደተፃፈና እኛ ምንድነው ከዛ የምንማረው: የሚለውን ማወቅ አስፈላጊ መስሎ ስለታየኝ ነው :: ተባረኩ ::

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading