የሚያንገጫግጭ መንገድ

ሰዎች፣ ሕይወት አስቸጋሪ እንደሆነች ሲነግሩኝ ሁልጊዜ የምመልሰው ‹‹በእርግጥ አስቸጋሪ ናት፡፡›› በማለት ነው፡፡ ልሰጥ ከምችላቸው ምላሾች በላይ ይህ መልስ ያረካኛል፡፡ ፀሐፊ ቻርለስ ዊሊያምስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፣ ‹‹አለም በሁሉም ረገድ ስቃይ አለባት፤ ይህን ስቃይ መውደድ ይኖርብናል የሚለውን ሃሳብ መስማት ደግሞ ሊሸከሙት የማይችሉት ዜና ነው፡፡››

እግዚአብሔር እኛን ይዞን የሚጓዝበት መንገድ ብዙውን ጊዜ እኛ ለራሳችን ካየነው ጥሩ መንገድ አንጻር በተቃራኒው ሊመስል ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንዴ እየተጓዝንበት ያለንበት የእግዚአብሔር መንገድ ትክክለኛ ያልሆነ ይመስለናል፡፡ ለዚህ ነው ብዙዎቻችን፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ ብሆን ኖሮ፣ የእግዚአብሔር መልካምነት፣ ሁል ጊዜ ከችግር ነፃ በሆነ የሕይወት ጎዳና ይመራኝ ነበር ብለን የምናስበው፡፡
ይህ ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ የወጣና ሊሰራ የማይችል ሕልም ነው፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ምድራዊ ምቾት በሌለበት ጎዳና ሊመራን ይችላል፡፡ ጳውሎስ እንዲህ ይላል፣ ‹‹… ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም›› (ፊል. 1፡29)፡፡ ስንጓዝበት ከነበረው የመከራ ጉዟችን ስንወጣ እያንዳንዱን ሁኔታ እግዚአብሔር ለዘለቄታዊ ጥቅማችን ሲል የፈቀደው እንደነበረ ይገባናል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ የሆነው ኤፍ ቢ ሜየር እንዲህ አለ፣ ‹‹ካለፍንበት መንገድ የተሻለ ተስማሚ ወይም ደህና መንገድ የለም፤›› ‹‹አንድን መንገድ ልንመረጠው የምንችለው እግዚአብሔር እንደሚያየው፣ እኛም ማየት ስንችል ብቻ ነው፡፡›› ዴቪድ ሮፐር ይህን አስመልክቶ ሲናገር ደግሞ እንዲህ ይላል፣ «እግዚአብሔር መከራዎቻችንን የፈቀደበት ምክንያት አውቀነው ቢሆን ኖሮ የትኛውም መከራ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንድንገባ ባላደረገን ነበር፡፡››

ወንጌል በድረ ገጽ አገልግሎት፤ https://ethiopiansite.com/
Our daily Bread – (መጋቢት 21, 2005) – የሚያንገጫግጭ መንገድ
ትርጉም፣ አዳነው ዲሮ

3 thoughts on “የሚያንገጫግጭ መንገድ”

  1. On Wed, Nov 13, 2019, 10:26 PM ወንጌል በድረ-ገፅ አገልግሎት wrote:

    > tsegaewnet posted: ” ሰዎች፣ ሕይወት አስቸጋሪ እንደሆነች ሲነግሩኝ ሁልጊዜ የምመልሰው ‹‹በእርግጥ
    > አስቸጋሪ ናት፡፡›› በማለት ነው፡፡ ልሰጥ ከምችላቸው ምላሾች በላይ ይህ መልስ ያረካኛል፡፡ ፀሐፊ ቻርለስ ዊሊያምስ
    > በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፣ ‹‹አለም በሁሉም ረገድ ስቃይ አለባት፤ ይህን ስቃይ መውደድ ይኖርብናል የሚለውን ሃሳብ
    > መስማት ደግሞ ሊሸከሙት የማይችሉት ዜና ነው፡፡›› እግዚአብሔር እኛን ይዞ”
    >

  2. i want to know detail about one into three(son, father, and holysprit)
    please attach detail issue on this if it is ok.

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading