እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው ፍቅር (ሆሴዕ 11-14)

የትንቢት መጻሕፍት መልእክቶቻችን እንዴት ሚዛናዊ መሆን እንዳለባቸው የሚያሳዩ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው። የትንቢት መጻሕፍት የፍርድና የኃጢአት ብቻ ሳይሆን፥ የተስፋን መልእክት አጣምረው የያዙ ናቸው። ይህ ሚዛናዊ ሁኔታ በትንቢተ ሆሴዕ ውስጥ ይታያል። እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚቀጣ ሲናገር፥ ወደፊት በረከቱን እንደሚመልስላቸውም ተስፋ ሰጥቶአቸው ነበር።

የውይይት ጥያቄ፥ ሀ) ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖችን የሚያበረታቱ መልእክቶችን ከመስበክ ይልቅ የሚኮንን መልእክት መስበክ የሚቀልለው ለምንድን ነው? ለ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ የሚገኙትን ክርስቲያኖች ለማበረታታት መልእክት ልታቀርብባቸው የምትችል የአሥር ርእሶች ዝርዝርን አዘጋጅ። 

የውይይት ጥያቄ፥ ሆሴዕ 11-14 አንብብ። በዚህ ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ የሰጣቸው ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

ሆሴዕ በእግዚአብሔርና በእስራኤል መካከል ያለውን ኅብረት ለመግለጽ በባልና በሚስት መካከል ያለውን ግንኙነት በሚያነጻጽር ምሳሌ እንዴት እንደተጠቀመ ቀደም ሲል ተመልክተናል። ሆሴዕ ይህንን ፍቅር ለመግለጽ አሁን ሌላ ምሳሌ ይጠቀማል። ይህም አባት (እግዚአብሔር) ለልጁ (ለእስራኤል) ያለው ፍቅር ነው። አዲስ ኪዳንም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለመግለጥ እነዚህን ሁለት ተመሳሳይ ማነጻጸሪያዎች እንደተጠቀመ ስንመለከት እንደነቃለን፤ ለምሳሌ (ዮሐንስ 1፡12)። እግዚአብሔር ልጁን እስራኤልን ስለወደደው አሳደገው። እስራኤል ግን በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀ። እግዚአብሔር ከእርሱ ርቆ ያለውን ልጅ ቢቀጣም፥ ለእስራኤል ያለው ፍቅር ግን ሙሉ በሙሉ እንዲያጠፋው የሚያስችለው አልነበረም። ይልቁንም አንድ ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ ይሰበስባቸዋል።

እስራኤላውያን የኃጢአታቸውን ቅጣት ቢሸከሙና በሰይፍ ቢጠፋም እንኳ አንድ ቀን እግዚአብሔር ይህንን ሕዝብ ከሞት ይቤዣል። ካለባቸው በኃጢአት የመንከራተት ዝንባሌ በሽታ እስራኤላውያንን ይፈውሳቸዋል። በአኃጢአታቸው ንስሐ ይገባሉ። እግዚአብሔርም በረከቱን ለእስራኤል ሕዝብ ይመልሳል። 

እነዚህ የተስፋ ቃሎች ለእስራኤል ሕዝብ ገና አልተፈጸሙም። ከይሁዳ ሕዝብ የሚለዩበት ነገር ቢኖር ወደ እስራኤል ምድር አለመመለሳቸው ነው። ስለዚህ እነዚህ የተስፋ ቃላት ወደ ፊት ይፈጸማሉ። በዘመናት መጨረሻ ክርስቶስ በምድር ላይ በሚነግሥስበት ጊዜ አይሁድ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደሚመለሱ፥ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ላይ በጭራሽ ኃጢአት እንደማያደርጉና እርሱም እንደገና እንደሚባርካቸው የሚመስላቸው ምሁራን በርካታ ናቸው። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው ቃል ኪዳን ይፈጸማል። 

የውይይት ጥያቄ፦ ሀ) በዚህ የመጨረሻ ክፍል የሚገኙና ለአንተ በረከት የሆኑ አንዳንድ መንፈሳዊ እውነቶች ምንድን ናቸው። ለ) እነዚህ ተመሳሳይ እውነቶች በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች በረከት የሚሆኑት እንዴት ነው? ሐ) በቤተ ክርስቲያህ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ትንቢተ ሆሴዕን ለማስተማር ዕቅድ።

(ማብራሪያው የተወሰደው በ ኤስ.አይ.ኤም ከታተመውና የብሉይ ኪዳን የጥናት መምሪያና ማብራሪያ፣ ከተሰኘው መጽሐፍ ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ፡፡)

የመመዘኛ ጥያቄዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ (መስፈንጠሪያ) ይጫኑ፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: