የሚደበዝዝ ክብር – የሚበዛ ክብር (2ኛ ቆሮ. 3፡7-11)

ይህ አንቀጽ የምዕራፉ እምብርት ስለ ሆነ፥ ከዘጸአት 34፡29-35 ጋር ተያይዞ መጠናት አለበት። የሕግ መሰጠት፥ የድንኳንና የቤተ መቅደስ አገልግሎት ውስጥ በትክክል ክብር ያልተለየው ስለ ነበረ፥ ጳውሎስም ቢሆን ይህን የአሮጌውን ኪዳን ክብር አልካደም። ዳሩ ግን እርሱ ለማጠናከር የፈለገው የአዲሱ ኪዳን የጸጋ ኪዳን ክብር እጅግ የሚበልጥ መሆኑንና ለዚሁም በርካታ ምክንያቶች እንዳሉት ነበር። 

1. የአዲሱ ኪዳን ክብር ማለት መንፈሳዊ ሕይወት እንጂ፥ ሞት አይደለም (2ኛ ቆሮ.3፡7-8)። ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከተራራው ላይ ሲወርድ፥ ፊቱ በእግዚአብሔር ክብር ያበራ ነበር። ይህም ከሕግ መስጠት ክብር አንዱ አካል ስለ ነበር፥ ሕዝቡን አስደንቆአቸዋል። ከዚያም ጳውሎስ፥ ሞትን ባመጣው የሕግ መስጠት ውስጥ ክብር ከነበረ፥ ሕይወትን በሚያመጣው አገልግሎት ውስጥ ምንኛ የበለጠ ክብር ይኖር ይሆን! በማለት ይሞግታል። 

እንደ አይሁዳዊነት ወግ አክራሪዎች ሁሉ ሕግ-አጥባቂዎችም የሕግን ክብር አጉልተው ለማሳየትና ደካማ ጎኑን ለመሸፈን ይጥራሉ። ጳውሎስ በገላትያ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በጻፈው ደብዳቤ፡ የሕግን ደካማነት በሚገባ አመልክቷል፡ – ሕግ የጠፋን ኃጢአተኛ ሊያጸድቅ (ገላ. 2፡16፤ 2፡21)። መንፈስ ቅዱስን ሊሰጥ (3፡2)። ርስትን ሊሰጥ (3፡18)። ሕይወትን ሊሰጥ (3፡21)፥ ወይም ነጻነትን ሊሰጥ አይችልም (4፡8-10)። ዳሩ ግን የሕግ ክብር ለሙታን እንደሚደረገው አገልግሉት ዓይነት ክብር ነው። 

2. የአዲሱ ኪዳን ክብር ማለት ጽድቅ እንጂ ኩነኔ አይደለም (2ኛ ቆሮ. 3፡9-10)። ለሕግ በመታዘዝ ደኅንነት ስለማይገኝ፥ ሕግ የተሰጠው ለደኅንነት ዓላማ አልነበረም። ሆኖም ሕግን መተላለፍ ኩነኔ ስለሚያመጣ፥ ፊታችን ምንኛ እንዳደፈ እንደሚያሳይ መስተዋት ነው ለማለት ይቻላል። ዳሩ ግን በመስተዋቱ ውስጥ ፊታችንን ልንታጠብ አንችልም። 

የአዲሱ ኪዳን አገልግሎት ጽድቅን የሚያመጣ ሲሆን፥ ሕይወትን ለእግዚአብሔር ክብር ይለውጣል። ለሰው እጅግ የሚያስፈልገው ጽድቅ 

Lአብሔርም የሚሰጠው ከሁሉም የላቀው ስጦታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው ጽድቅ ነው። «ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ፥ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ!» (ገላ 2፡2)። ከሕግ በታች ለመኖር የሚሞክር ሰው ይበልጥ የበደለኛነት ስሜት እየተጭነው ይሄዳል፤ ይህም ተስፋ የመቁረጥንና የመገለልን ስሜት ሊያስከትል ይችላል። የተቀባይነት ስሜትና ደስታ ሊኖረን የሚችለው በክርስቶስስንታመንና በእግዚአብሔር ጸጋ አምነን ስንመላለስ ብቻ ነው። 

ሁለተኛ ቆሮንቶስ 3፡10 ሕግ እጅግ የበለጠ ክብር ካለው የእግዚአብሔር የጸጋ አገልግሉት ጋር ሲነጻጸር «ክብሩን እንዳጣ» ያህል እንደሚቆጠር ይናገራል። ባጭሩ ሊወዳደሩ አይችሉም ማለት ነው። የሚያሳዝነው የበደለኛነትን ስሜት እስካላነገቡ ጊዜ ድረስ፥ «መንፈሳዊነት የማይሰማቸው» አንዳንድ ሰዎች መኖራቸው ነው። ሕግ የዕዳን ሰንሰለትና (ቆላ. 2፡14) የሚቀጣንን ተቆጣጣሪ (ገላ 4፡1-5) የሚመስል፥ ብሎም ለመሸከም የማይሞክሩት ብርቱ ቀንበር ስለ ሆነ፥ በደልና ኵነኔ ያመጣል (ገላ. 5፡1፤ የሐዋ. 15፡10)። 

3. የአዲሱ ኪዳን ክብር ቋሚ እንጂ ጊዜያዊ አይደለም (2ኛ ቆሮ. 3፡1)። በዚህ ሥፍራ የተጠቀሰው የጊዜ አመልካች ግስ (አንቀጽ) በጣም አስፈላጊ ነው፡- «ያ ይሻር የነበረው» ጳውሎስ የጻፈው ወደ ፍጻሜ የሚነጉደውና አዲስ የሚያቆጠቁጠው ዘመን የጋርዮሽ ሚና በሚጫወቱበት የታሪክ ወቅት ነበር። አዲሱ የጸጋ ዘመን የተጀመረ ቢሆንም፥ ዳሩ ግን የቤተ መቅደስ አገልግሎቶች አሁንም የቀድሞውን መልክ ይዘው ይከናወኑ ነበር፤ ሕዝበ – እስራኤልም ገና ከሕግ በታች ይኖር ነበር። በ70 ዓ.ም. የኢየሩሳሌም ከተማና ቤተ መቅደሱ በሮም ተደመሰሱ፤ ያም የአይሁድን የሃይማኖት ዘይቤ ከፍጻሜ አደረሰው። 

የአይሁድ እምነት አስፋፊዎች የቆሮንቶስ አማኞች የኋሊት ተጉዘው ከሕግ በታች እንዲኖሩና ሁለቱን ኪዳኖች «እንዲቀላቅሉ» ፈለጉ። ጳውሎስም፥ «ወደ ኋላ ተመልሳችሁ፥ ጊዜያዊና ጠፊ ወደ ሆነው ነገር ለምን ትሄዳላችሁ? ይበልጥ እየደመቀና እየመጠቀ በሚሄደው በአዲሱ ኪዳን ክብር ውስጥ ኑሩ» ይላቸዋል። የሕግ ክብር ያለፈ ታሪክ ክብር ብቻ ሲሆን፥ የአዲሱ ኪዳን ክብር የአሁኑ ልምምድ ክብር ነው። አማኞች እንደ መሆናችን፥ «ከክብር ወደ ክብር» (3፡18) ልንለወጥ እንችላለን፤ ይህንን ደግሞ ሕግ ከቶውንም ሊሠራው የማይችለው ነገር ነው። 

በጳውሎስ ዘመን የሕግ ክብር እየደበዘዘ ነበር፤ ዛሬ ያ ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ተመዝግቦ ይገኛል። ዛሬ የእስራኤል ሕዝብ ቤተ መቅደስም ሆነ የካህናት አገልግሎት የለውም። ደግሞም ሕዝቡ አዲስ ቤተ መቅደስ ቢሠራ እንኳን፥ በቅዱሳ-ቅዱሳን ውስጥ የሚያድረው የእግዚአብሔር መለኮታዊ ክብር አሁን ሊኖር አይችልም። የሙሴ ሕግ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ክብር የነበረው ሃይማኖት ነበር፤ ዛሬ ግን ያ ክብር የለውም። ብርሃኑ ሥፍራውን ለቅቆአል፡- የቀረው ነገር ቢኖር ጥላው ብራ ነው (ቆላ 2፡16-17)። 

ጳውሎስ የጸጋ አገልግሎት ሕይወትን እንደሚያስገኝ(ቁ 4-6)፥ እየደመቀና እየጨመረ የሚሄድ ክብር ያዘለ መሆኑንና (ቁ. 7-10 ውስጣዊ ጠቀሜታ (2ኛ ቆሮ. 3፡1-3) እንዳለው ገልጿል። የዚህኑ የአዲሱን ኪዳን የጸጋ አገልግሎት የበላይነት ለማረጋገጥ አንድ የመጨረሻ ማነጻጸሪያ ያቀርባል፡- 

Leave a Reply

%d bloggers like this: