1ኛ ቆሮ.15:35-58)

ጥያቄ 6. በቁጥር 35 ላይ ሁለት ጥያቄዎች ተጠይቀው ሐዋርያው መልስ ሰጥቷል፤ ጥያቄዎቹን ከመልሶቻቸው ጋር አዛምድ። 

ጥያቄ 7. በቁጥር 44 ላይ መንፈሳዊ አካል ሲል ምን ማለቱ ነው? 

ጥያቄ 8. ሐዋርያው የነገራቸው ምሥጢር ምንድነው? (ቁጥር 51 እና 52) 

ጥያቄ 9. በቁጥር 55 ላይ ሐዋርያው የጠቀሰው ጥቅስ የተወሰደው ከየት ነው? 

ቁጥር 35-50፡- በቁጥር 35 ላይ ሁለት ጥያቄዎች ተነሥተዋል። ከዚያ ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ በሙሉ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ነው። የመጀመሪያው ጥያቄ «ሙታን እንዴት ይነሣሉ?» የሚል ሲሆን ሁለተኛው ጥያቄ ደግም «በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ?» እነዚህን ጥያቄዎች በሰፊው እንደሚከተለው ይመልሳል። 

አስቀድሞ ግን ቢያስተውሉ ኖሮ ይህን ነገር ከተፈጥሮ ሊማሩ ይችሉ እንደነበር «ሞኝ» ብሉ አላማስተዋላቸውን ይገሥጻል፡፡ የሚከተሉትን የተፈጥሮ ሕጉች ለትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ያቀርባቸዋል። 

1ኛ/ ስንዴ ዘሩ ተዘርቶ ሌላ ስንዴ ከነሰበዙ አምሮና ደምቆ፥ ከተዘራው ቅንጣት እጅግ ደምቆ ይበቅላል። እግዚአብሔር ይህን በተፈጥሮ ካዘጋጇ ትንሣኤንም እንዲሁ እንደሚያሳምረው መረዳት አለብን፤ (ቁጥር 36-38)። ይህንን ከቁጥር 42-44 ጋር አስተያይ፡፡ ይህ ምሳሌ በምድር ላይ ያለው አካላችንና መንፈሳዊ አካላችን ተመሳሳይነት እንዳላቸው ያስተምረናል። ተዘርቶ እንደሚበቅለው ስንዴ የእኛም አካል አሁን ካለው አካላችን ትንሽ ለየት የሚል ይሆናል። 

2ኛ/ በሥጋም ደረጃ የተለያየ ሥጋ አለ። የሰውና የእንስሳ ሥጋ እንደ መልኩ በፈጣሪው ተለያይቷል። በምድር ላይ እንዲህ ያለ የተለያየ ሥጋ እንደለ ሁሉ ሰማያዊ ሥጋም ይናራል፤ (ቁጥር 39 እና 40)። ምንም እንከን ከሙታን የተነሣው አካላችን ከምድራዊው አካላችን ጋር መመሳሰል ቢኖረውም፥ ከሙታን የተነሣው ሰውነታችን የበለጠ ክብር አለው። ይህ አርጅቶ የሚሞተውና የሚበሰብሰው ሥጋዊ አካላችን ከሙታን ከተነሣን በኋላ ለሞትና ለመበስበስ የተጋለጠ አይሆንም። በሕይወታችን ውስጥ ያለው የማይከብረው የኃጢአት ተፈጥሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ቅድስና ይለወጣል። በዚህ ሂደት ወስጥ መንፈሳዊ የሆነ አካል ይሰጠናል፡፡ 

«ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፤» (ቁጥር 44)። አሁን ያለን ሥጋ ፍጥረታዊ ነው። ይህ ፍጥረታዊው ግን በትንሣኤ መንፈሳዊ ሆኖ ይነሣል፡፡ ፍጥረታዊውን አካላችንን ከመጀመሪያው አባታችን ከአዳም ወረስን፤ በዚህም እርሱን መሰልን። እንዲሁ ዳግሞ አንድ ቀን የሕይወት ሰጭውን የክርስቶስን አካል መስለን የምንለወጥበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ክርስቶስም እንዲህ እንደ መጃመሪያው አዳም የርሱ የሆኑትን የራሱን መልክ እንዲመስሉ ስለሚለውጣቸው ሁለተኛው አዳም ተባለ፤ (ቁጥር 45-49)። ይህ እንዲህ ሊሆን ግድ ነው፤ ምክንያቱም በዚህ ሥጋ አካላችን የትንሣኤን ሕይወት መካፈል አንችልምና የግድ መለወጥ አለብን። 

እዚህ ላይ መረዳት ያለብን የትንሣኤውን አካል «መንፈሳዊ» ሲል ረቂቅ የሆነ አካል ማለቱ ሳይሆን የክብሩን ታላቅነት መግለጡ ነው፡፡ ረቂቅ ማለቱ እንዳልሆነ የምናውቀው የክርስቶስ የትንሣኤ አካል ረቂቅ ባለመሆኑ ነው፤ (ዮሐ.20፡27)። እኛም በትንሣኤ እርሱን ስለምንመስል እርሱን መምሰል መንፈሳዊ አካል መልበስ ነው ማለት ነው። 

ጥያቄ 10. ከመሞቱ በፊት የነበረው የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና ከምቶ ከተነሣ በኋላ የነበረው አካሉ የሚመሳሰለው አንዴት ነው? የሚለያየውስ? 

ከቁጥር 51-57:- ትንሣኤያችን መቼ ነው? ለዚህ ጥያቄ መልሱ ክርስቶስ ሲመለስ ነው። ጌታ ሲመጣ በሕይወት ያለነው ከመቅድበት እንለወጣለን፤ የሞቱትም አማኞች የትንሣኤ አካል ለብሰው ይነሣሉ። ይህ ሲሆን ሞትና ኃጢአት በክርስቶስ ፈድመው ድል ይሆናሉ። ጳውሎስ ይህን «ምስጢር» ብሎ ይጠራዋል። በመድሐፍ ቅዱስ «ምስጢር» የሚባለው አንድ የተደበቀና ለጥቂት ሰዎች የሚታወቅ ነገር ሳይሆን፥ ከዚህ ቀደም እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ያልገለጸው ነገር ግን አሁን በደቀ መዛሙርቶቹ አማካኝነት የገለጸው እውነት ማለት ነው። ይህ አዲስ እውነት ያለመለኮታዊ መገለጥ ሊታወቅ የማይችል ነገር ነው። አዲስ ኪዳን በመፈጸሙ እንደዚህ ዓይነት ምስጢራት ዛሬ ለእኛ አይገለጹልንም። ሐዋርያው ከትንቢተ ሆሴዕ 13:14 በመጥቀስ ይደመድማል። ይህ የትንሣኤ ተስፋ ስላለን ተስፋ ሳንቆርጥ በብርታት ጌታን እናገለግላለን፤ (ቁጥር 58)። 

ጥያቄ 11. የትንሣኤው እውነተኛነት እንዴት ነው ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለጌታ ሥራ እንድንሰጥ ሊያደርገን የሚችለው?

Leave a Reply

Discover more from

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading