2ኛቆሮ.2:12-13

ጥያቄ 7. በቁጥር 12 ላይ “ለጌታ ሥራ በር ምንም ቢከፈትልኝ” ሲል ስለዚህ በር ሰፋ አድርገህ አብራራ። 

ሐዋርያው ጳውሎስ አገልገሉቱ በአንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎች አንደሆነ በሐዋርያት ሥራ እናነባለን። አሁንም ሐዋርያው በቆርንቶስ ቤተ ክርስቲያን ችግር እንዳለ ከሰማ በኋላ ችግሩን እንዲያርሙ ልቡ በሃዘን ተሞልቶ 1ኛ ቆሮንቶስን ጻፈ። የደብዳቤውንም ውጤት ቲቶ እንዲያመጣለት በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቅ ነበር። 

ልቡ በሃዘን ስለተሞላ የቲቶን መልስ ለመጠበቅ ወደ መቄዶንያ ተሻገረ። ይህን እርምጃ የወሰደው ለአገልግሎት የተከፈተለትን በር ትቶ ነው። በ2ኛ ቆር.7:5 ላይ ይህንን ታሪክ ይቀጥላዋል። አሁን ግን ለጊዜው በሌላ ትምህርት ላይ ነው የሚያተከረው። 

ስለ በር መከፈት በአጭሩ እንወያይ። በዚህ ቃል ላይ እንደምናየው በር ከፋቹ ሐዋርያው ሳይሆን ራሱም በሩ በራሱ ሳይሆን ሌላ ከፋች አለው፤ እርሱም እግዚአብሔር ነው። ስለ በር መከፈት ሐዋርያው ጸሎት እንዲደረግለት በቆላ.4:3 ይናገራል። ይህም በር ሁለት አቅጣጫ አለው። አንደኛው ሐዋርያው ወንጌልን ይዞ በአንድ ሥፍራ እንዲሄድ የሥፍራው በር መከፈቱን ያመለክታል። ሁለተኛው አቅጣጫ ደግሞ እግዚአብሔር የአድማጮችን ልብ መክፈቱን ያመልክታል። ለዚህ ማስረጃ የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት የሐዋ. 14:27፤ 16፡14። ሰው በወንጌል የሚያምነው እግዚአብሔር ልቡን ሲከፍትለት ስለሆነ ጌታ የሰዎችን ልብ በመክፈት ለወንጌል ሥራ መሳካትን እንዲሰጥ ልንጸልይ ይገባል። የእኛንም ልብ ከፍቶ የወንጌልን ብርሃን በልባችን ስላበራ ስሙ የተባረከ ይሁን። 

ጥያቄ 8. እግዚአብሔር እንዴት አድርጎ የአገልገሎት በር ለአንተም ሆነ ለቤተ ክርስቲያንህ አንደከፈተ ምሳሌዎችን በመስጠት አስረዳ። 

Leave a Reply