2ኛ ቆሮ.1:15-22

ጥያቄ 12. በቁጥር 15 እና 16 እንደተጻፈው ጳውሎስ ምን ፕላን አውጥቶ ነበር? 

ጥያቄ 13. ይህን ቃሉን አላመፈጸሙና የሰበከው የወንጌል እውነተኝነት ምን ግንኙነት እንዳለው እንረዳለን? 

ቁጥር 15ን ከ1ኛ ቆሮ.16፡5 ጋር ስናስተያይ ሐዋርያው ከመቄዶንያ ሲመለስ በቆሮንቶስ እንደሚያልፍና እንደሚጎበኛቸው ተስፋ እንደሰጣቸው እናነባለን። ይህ ክመቄዶንያ ሲመለስ ብቻ መጕብኘት በፊት ከነበራቸው የተቀየረ ነበር። በፊት የነገራቸው ወደ መቄዶንያ ሲሄድም ከመቄዶንያ ሲመለስም ሁለት ጊዜ እንደሚሆን ገልጾ እንደነበር በዚህ ክፍል እናነባለን። ያ በ1ኛ ቆሮ.16፡5 የጻፈው ፕላኑን እንደቀየረ የሚያስታውቅ ነበር። ይህ የፕላን መቀየር በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ሐሜትንና ቅሬታን አስነሣ። ይህን ቅራኔ ለማስወገድ ሐዋርያው ይሞክራል። በቁጥር 17 ላይ «እንግዲህ ይህን ሳስብ ያን ጊዜ ቅሌትን አሳየሁን?» ብሉ ክሳቸውን ይጠቅሰዋል። 

ዓለማውያን የሰጡትን ቃል አያከብሩም። ዛሬ የተናገሩትን ጥቅም የማይሰጣቸው ከሆነ ነገ ይለውጡታል። ሐዋርያው ግን ሃሳቡን የቀየረው ለጥቅማቸው አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለት ጊዜ እንዲጉበኛቸው ስላሰበ እንደሆነ ይናገራል። 

ሐዋርያው ዓለማዊ አለመሆኑን በሰበከላቸው ወንጌል ተረድተውታል። በጳውሎስ የተሰበከው ወንጌል በአንድ ጊዜ «አዎንና አይደለም» የሚል ሳይሆን ቃሉና ተስፋው የማይሻር ሆኖ ሁልጊዜ «አዎን» ነው። በቁጥር 18 ላይ የአማርኛው ትርጉም «እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው» ይላል። ትክክለኛው ትርጉም ግን «እግዚአብሔር እውነት ነው» ማለቱ ነው። ይህም እንደ መሐላ ነው፡፡ 

ጥያቄ 14. ቃላችንን ስለመጠበቅ ይህ ክፍል የሚሰጠን ትምህርት ምንድነው? ብዙ ጊዜ ክርስቲያኖች ቃላቸውን የማይጠብቁት በምን ዓይነት አኳኋን እንዳሆነ ምሳሌ በመስጠት ገለጽ። 

እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ለልጆቹ ብዙ ቃል ኪዳናችን ሰጥቷል። ለእነዚህ ቃል ኪዳኖች የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች ስናሟላ ቃል ኪዳኖቹ ይፈጸማሉ። 

ጥያቄ 15. እግዚአብሔር ከሰጠን ቃል ኪዳናች ውስጥ አንዳንዶቹን ግለጽ። 

እግዚአብሔር ቃል ኪዳናቱን (ለምሳሌ፡- ካመንን እንዳምንድን፥ ስንደልይ እንደሚሰማን፥ ሁሌ ከእኛ ጋር አብሮ እንደሚሆን) በመፈጸም ረገድ ታማኝ ነው። እኛም የእርሱ ልጆች እንደመሆናችን መጠን ልክ እንደ እርሱ ለሌሎች የምንገባላቸውን ቃል ኪዳኖች መፈጸም አለብን። 

ስለ መንፈስ ቅዱስ ማህተምና መያዣ ቁጥር 21 እና 22 ይናገራል። ማህተም ሲል መንፈስ ቅዱስ ሕይወታችንን በመቀየር በተፈጥሮ ተሰጥቶን የነበረው እግዚአብሔርን መምሰል (ዘፍ.3፡16-17) በኃጢአት ግን የተበላሸው አሁን በወንጌል መታደሱን ነው። ይህም መታደስ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ስለሆነ የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ይባላል። 

እግዚአብሔር በወንጌል ቃሉ የታመነ ለመሆኑ የመንፈሱን መያዣ ሰጥቶናል፤ (ቁጥር 21 እና 22)፡፡ ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ በሙላት ልንቀበለው ላለን ወንጌል ለሰጠን ለወደፊቱ ተስፋችን መያዣ (ቀብድ) ሆና ተሰጥቶናል ማለት ነው (ሮሜ 8፡9፤ ኤፌ.1:13፤ 4፡30)። 

የመጨረሻውን ደህንነታችንን በተመለከተ፥ እንደ እግዚአብሔር ልጆች በቁጥር 21 እና 22 ላይ እግዚአብሔር የሰጠንን አራት ቃል ኪዳኖች እንመለከታለን። 

በመጀመሪያ፡- በክርስትና እምነታችን አጽንቶ እንደሚያቆመን ቃል ይገባልናል። 

ሁለተኛ፡- እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ቀብቶናል። 

ሦስተኛ፡- መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር እንደሆንን የሚያሳይና የሚያረጋገጥ ማህተም ነው። 

አራተኛ:- መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ነው ያለው። መንፈስ ቅዱስ እኛን ማደስ ብቻ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ልጆች መንግሥተ ሰማይ እንደምንገባና ክርስቶስን ወደ መምሰል እንደምንደርስ የሚያረጋግጥልን ዋስትናችን ነው። 

ጥያቄ 16. የመንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ መያዣ ወይም ዋስትና ሆኖ መሰጠት እንዴት እኛን ሊያበረታታን ይችላል?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.