2ኛ ቆሮ. 4፡7-12

ጥያቄ 6. «ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን» ሲል ምን ማለቱ ነው? 

ጥያቄ 7. በቁጥር 12 ላይ «ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል» ሲል ምን ማለቱ ነው? 

ቁጥር 7:- «ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን»። መዝገብ ያለው ክቡር ዕቃ ወይም እንደ ወርቅና እንደ አልማዝ የሆነ የከበረ እንቁ እንደ ማለት ነው። መዝገብ ያለው ሕይወት ሰጭውን ወንጌል ሲሆን ሸክላ ያለው ደግሞ የራሱንና የወንጌላውያንን ሕይወት ነው። የወንጌል ክብር ከተሸካሚዎቹ አለመሆኑን ይገልጻል። ወንጌሉን የሚያስተላልፈውን ሰው እግዚአብሔር ደካማ ያደርገዋል። ይህንንም የሚያደርገው፥ የወንጌል ሕይወትን የመቀየር ኃይል ምንጭ የተገኘው ከእግዚአብሔር እንደሆነና ከወንጌላዊው ችሎታ እንዳልሆነ ለማሳየት ነው። በዚህም እግዚአብሔር ክብር ለእርሱ እንደሚሆንና ለወንጌላዊው እንደማይሆን ያረጋግጣል። 

ከቁጥር 8-10፡- ሸክላ ክብር የሌላው ከመሆኑም በላይ ተሰባሪ ነገር ነው። ወንጌላውያንም እንዲሁ ተሰባሪ ናቸው። እንዲያውም በታላቅ አደጋ ተጋልጠው ይገኛሉ። ለአደጋ ይጋለጡ እንጂ እንደሸክላ አይንኮታኮቱም። አንዲያውም ለስብራት አልፈው በተሰጡ ቁጥር የእግዚአብሔር ኃይል በሕይወታቸው ይገለጣል። እርግጥ ቀናቸው ሲደርስ ሩጫቸውን ሲፈድሙ በሞት መወሰደቸው አይቀርም። ሆኖም ወንጌል ከእነርሱ ጋር አይጠፋም እግዚአብሔር ሌሎችን በምትካቸው ያስነሣል። 

የወንጌል ጎዳና ቀላል አይደለም። ጠላትና መከራ ተባብረው እግዚአብሔርን ለመከተል የወሰኑትን ሰዎች ለማጥፋት ይጥራሉ። ደካሞች በመሆናችን በችግር፥ በንዴት፥ በስደትና በሞትም ጭምር ተወጥረን እንጨነቃለን። ነገር ግን የሕይወታችን ኃይል በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ ስለሆነ መቼም ቢሆን ክርስቲያኖች አንሸነፉም። መከራን ስንቀበል የኢየሱስ መከራ ተካፋዮች ነው የምንሆነው። ያውም አንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን በምንቀበልበት ወቅት የረሳችን ሕይወት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንደ ሞተ ሆኖ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት በሙላት አንደምንኖር ዓይነት ነው የሚሆነው። 

ጥያቄ 8፣ ይህ ጥቅስ በአንተም ሆነ በቤተ ክርስቲያንህ መሪዎች ሕይወት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆነው እንዴት ነው? 

ቁጥር 11 እና 12:- ይህ ለሞት መሰጠት፥ ሁልጊዜም ተሰባሪ ሆኖ መገኘት የክርስቶስን መሞት መካፈል ነው። ግን ተሰባብሮ ወድቆ ዓላማ ሳይበላሽ ሁልጊዜ የዓላማ መሳካት ማግኘት የክርስቶስን የትንሣኤ ኃይል መካፈል ነው። ስለዚህ ምንም እንኳን ወንጌላውያን ለስብራት አልፈው ቢሰጡም በተጎሰሙ መጠን ሕይወት ከእነርሱ የመፍለቅና ሰሚዎችን የማደስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የማስፋፋት እድል ይኖረዋል። 

ጥያቄ 9፤ እግዚአብሔር መከራንና ስደትን በመጠቀም ቤተ ክርስቲያንህ እንድታድግ ያደረገው እንዴት ነው?

Leave a Reply