2ኛ ቆሮ. 7:2-4

ጥያቄ 1. በቁጥር 2 ላይ “በልባችሁ ስፍራ አስፋልን” ሲል ይህን መሰል ንግግር ከዚህ በፊት የት ተጽፎ እናገኛለን? 

ጥያቄ 2. በቁጥር 3 “ለኩነኔ አልልም” ማለቱ ምን ማለቱ ነው?

በቁጥር 2 ላይ ከዚህ በፊት በ6፡12 የተናገረውን በመድገም “በልባችሁ ሥፍራ አስፉልን” ይላል። ልባቸውን ለሐዋርያው የማያሰፉበት ምንም ምክንያት የለም፤ ምክንያቱም በሐዋርያው በኩል ምንም በደል አልነበረምና! በተለያዩ ሦስት ቃላት ይህንን ይገልጻል፤ ማንንም አልበደልንም፤ ማንንም አላጠፋንም፤ ማንንም አላታለልንም። 

ጥያቄ 3. አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ምዕመናኑን እንዴት አድርጎ ሊያሳስት፥ ሊጎዳ ወይም ለራሱ ፍላጎት ሊጠቀምባቸው እንደሚችል መንገዶቹን በመጥቀስ አስረዳ። 

በቁጥር 3 ላይ «ለኩነኔ አልልም» ማለት ለፍርድ ወይም ለወቀሳ አልልም ማለቱ ነው። ሐዋርያው እንዲህ አድርጎ የእርሱን ልብ መግለጡ እነርሱን ለመውቀስና ለማሳፈር እንዳልሆነ መናገሩ ነው። እንዲያውም ለእነርሱ ጥልቅ ፍቅር እንዳለው ይገልጽላቸዋል። «በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን እንዳላችሁ አስቀድሜ ብዬአለሁና።» ብዙውን ጊዜ እኛ ወንጌላውያን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ስናስተምር እንደዚህ በፍቅር ልብ ሳይሆን ቅር ባለውና በቀዘቀዘ ልብ ስለሚሆን ሕዝቡ እንደሚገባ አይባረኩም፤ እግዚአብሔርም በሙላት በረከቱን አይልክም። ስለዚህ በፍቅር ለማገልገል የሐዋርያውን አርአያ እንከተል። ሕዝቡን የምንገስጸው ከራሳችን ቅያሜ አንፃር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፍቅር አንፃር መሆን አለበት። 

ጥያቄ 4. አንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ አንድን ክርስቲያን በሚገስጽበት ፍቅር ማሳየቱ በጣም አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ምንድነው? 

በቁጥር 4 ላይ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ ያለውን ትምክሕት ይገልጻል። እኛም በምናገለግለው የአግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ትምክሕት ሊያድርብን ይገባል። 

Leave a Reply

%d bloggers like this: