የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በክርስቶስ ሕይወት

ከድንግል ከመወለዱ ጋር 

የሚወለደው ሕፃን ከመንፈስ ቅዱስ እንደሚጸነስ ገብርኤል ለማርያም በግልጥ አበሰራት (ሉቃስ 1፥35)፤ ለዮሴፍም ይህ እውነት በመልአክ ተነግሮታል (ማቴ. 1፡20)። 

በሕይወቱ 

ክርስቶስ በጥምቀቱ ወቅት ልዩ በሆነ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቷል (ሉቃስ 4፡18፤ ዮሐ. 1፡32)። ይህም እግዚአብሔርን ያገለግል ዘንድ ኃይል ሰጥቶታል (ሐዋ. 10፡38)። ጌታችን በመንፈስ የተሞላና የሚመራም ነበር (ሉቃስ 4፡1 እንዲሁም ዮሐ. 3፡34፤ ኢሳ. 42፡1)። በመንፈስ ኃይል ተአምራትን ያደርግም ነበር (ማቴ. 12፡28)። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ጥገኛ መሆኑ የትሕትናውን ጥልቀት ከማመልከቱ ባሻገር፥ ይህ ድጋፍ ለኛም በጣም አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል። እርሱ ይህን ያህል የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ካስፈለገው፥ እኛስ በምን ያህል ብልጫ በመንፈሰ ቅዱስ መደገፍ አለብን? 

በምትና ትንሣኤው 

ዕብራውያን 9፡14 ስለ መንፈስ ቅዱስ ከተናገረ (አንዳንዶች እንደሚሉት ስል ከርስቶስ ስለ ራሱ መንፈስ ሳይሆን) ራሱን መሥዋዕት አድርጐ ያቀረበው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነበር ማለት ነው። ሮሜ 1፡4 (አንዳንዶች 1ኛ ጴጥ. 3፡18ንም ይጠቅሳሉ) መንፈስ ቅዱስ በትንሣኤው የነበረውን ሥራ ያሳይ ይሆናል። ደግሞም ትእዛዛቱን ለሐዋርያቱ የተሰጡትና በነርሱም በኩል ለእኛ የተላለፉልን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው (ሐዋ. 1፡2)።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.