የክርሰቶስ መለኮታዊና ሰብአዊነት ውህደት

መለኮትና ሰውነት በኢየሱስ ክርስቶስ አካል እንዴት ለመዋሀድ በቁ? የሚለው ጥያቄ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በጣም አከራካሪ ሆኖ የቆየ ጉዳይ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ አካል፥ መለኮትና ሰብአዊ ባሕርያት ስለመኖራቸው ሊጠየቅ የሚችለው ጥያቄ ሁሉ ተጠይቋል። አንዳንዶች የክርስቶስን መለኮታዊነት ክደዋል (ኢቦናይታውያንና፥ አርዮሳውያን፤ ሌሎቹ ደግሞ (ዶሴቲሲውያን Docetists/ዶሲቲስትስን እንደ አምላክ ምትሀታዊ ምስል ይቆጠራል በማለት ሰብአዊነቱን ክደዋል። አፖሊናሪያኖች [Apollinarians/እፓሊናሪያንስ] የተባሉት በበኩላቸው ሰብእዊነቱ ሙሉ አልነበረም፤ መንፈሱ ግን ዘላለማዊ “ቃል” ነበር ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ከርስቶስ በጥምቀቱ ጊዜ እግዚአብሔር ሰማደጎ ስለወሰደው መለኮታዊነት አግኝቷል ይላሉ [ዩኒተሪያኖች]። “የይሖዋ ምስክሮች [Jehovah’s Witnesses] ከፍጥረታት ሁሉ ከፍተኛው የእግዚአብሔር ተወካይ ነው ይላሉ። ባርቲያኖች የሚባሉትም በበኩላቸው ሙሉ ሰው ሲሆን (የኃጢአት ባሕርይም ጭምር ነበረው)፤ እግዚአብሔር ራሱን ለመግለጥ በመፈለጉ በተለይ በመስቀሉ፥ በዚህ ሰው አማካይነት ተጠቀመ ብለው ያምናሉ።

አጥባቂው የክርስትና እምነት ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው መሆኑንና፣ እነዚህ ሁለት ባሕርያት በአንድ አካል መዋሀዳቸውን፥ ማለት ሦስተኛ ባሕርይ ሳይፈጥሩ (አውጣኪ በEutyches] እንዳለው) ወይም ሁለት የተለያዩ አካላት ሳያስገኙ (ንስጥሮስ [Nestorius] እንዳስተማረው) መዋሃዳቸውን ያምናል።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.