መንግሥተ ሰማያትና የቅጣት ስፍራ

መንግሥተ ሰማያት 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንግሥተ ሰማያት ያወሳል (ዘፍጥ. 1፡1፤ ዕብ. 4፡14)፣ ሦስት ሰማያት ያሉ ይመስላል (2ኛ ቆሮ. 12፡2)። ሦስተኛው ሰማይ የጌታ መገኛ ነው። መንግሥተ ሰማያት እርግጠኛ ቦታ እንደሆንና፥ ወደዚያ ለመግባት የሚቻለውም በክርስቶስ በኩል ብቻ መሆኑን ጌታችን ራሱ ተናግሯል (ዮሐ. 14፡1-3)። 

ከመንግሥተ ሰማይ ገጽታዎች አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው፡- መኖሪያ ነው (ዕብ. 12፡22-24)፥ ውብ ስፍራ ነው (ራእይ 21፡1-22፡7)፥ በዚያ መዋለድ አይኖርም (ማር. 12፡25)፥ ቅዱስ ስፍራ ነው (ራእይ 21፡27)፥ እግዚአብሔርን እናመልክበታለን፥ እናገለግለዋለን፥ ከርሱም ጋር ኅብረት ይኖረናል (ራእይ 4-5)፥ መንግሥተ ሰማይ መግባታችን ስለ ማንኛውም ነገር አዲስ አመላካከት እንዲኖረን ያደርጋል (ኢሳ. 66፡24)። 

የቅጣት ስፍራ 

የቅጣቱ ቦታ በብሉይ ኪዳን በዕብራይስጥ “ሺኦል” ተብሏል። ትርጉሙም አንዳንዴ መቃብርን ሲያመለክት፥ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሞቱ ሰዎች ሁኔታ ከሕያዋን ጋር ተነጻጽሮበታል። የስቃይ (መዝ. 30፡9፤ ዘኁል. 16፡33)፣ የልቅሶ (ኢሳ. 38፡3) እና የቅጣት (ኢዮብ 24:19) ስፍራ እንደሆነ ተቆጥሯል። 

አዲስ ኪዳን ውስጥ የኃጢአተኞችን የቅጣት ቦታ የሚያመለክቱ ሦስት ቃላት አሉ፡- 

1. “ሄዲስ” በብሉይ ኪዳን ሲኦል ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ይህም ያልዳኑ ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ የሚሄዱበትና ትንሣኤያቸውንና በታላቁ ነጭ ዙፋን የሚፈጸመውን ፍርድ የሚጠብቁበትን ቦታ ያመለክታል። “ሄዲስ” ጊዜያዊ ቦታ ነው። በመጨረሻው ቀን እዚያ ያሉ ሰዎች በሙሉ ወደ እሳት ባሕር (ገሃነም) ይጣላሉ። 

2. “ታርታሮስ” የሚለው ሌላ ቃል (2ኛ ጴጥ. 2፡4) በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን፥ የወደቁ መላእክት የሚታሠሩበት ስፍራ ነው። 

3. ገሃነም፥ “ገኸነም” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ሲሆን ቀደምት ትርጉሙም የሄኖም ሸለቆ ማለት ነው። ይህ ሸለቆ ከኢየሩሳሌም በስተደቡብ ነው የሚገኘው። በዚህ ቦታ ሕጻናት ሞሎክ ለተባለ የጣዖት አምላክ ለመሥዋዕትነት ይቀርቡ ነበር (2ኛ ቆሮ. 33፡6፤ ሐዋ. 7፡43)። በኋላም የከተማው ቆሻሻ የሚጣልበትና የሚቃጠልበት ቦታ ሆነ። በዚህ ምክንያት “ሄኖም” የሚለው ቃል ከዘላለም እሳት ቦታ ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ችሏል፡፡ ገሃነም እንደ ጭለማ ስፍራ ይታወቃል (ማቴ. 8፡12)፤ ዘላለማዊ የቅጣትና የስቃይ ቦታ ነው (ራእይ 14፡10-11)። 

ያልዳኑ ሰዎች የሚቀጡት እንዲጠፉ በመደረግ አይደለም፤ ወይም ከጥቂት ቅጣት በኋላ ይቅርታ አይደረግላቸውም። ያልዳኑ ሰዎች ቅጣት ዘላለማዊ ነው። በዘላለማዊ ፍርድ (ዕብ. 6፡2) ላይ የተጠቀሰው “ዘላለም” የሚለው ቃል ዘላለማዊውን አምላክ ለመግለጥ አገልግሏል (ራእይ 15፡7)፤ ዘላለማዊ ሕይወት (ዮሐ. 10፡28)፥ ዘላለማዊ ቅጣት (ራእይ 14፡11) ለሚሉ አገላለጦችም ጥቅም ላይ ውሏል። ከእነዚህ አንዱ ብቻ ጊዜያዊ ከሆነ፥ ሌሎችም ይሆናሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ካልን፥ በእሳት ባሕር መቀጣትም ዘላለማዊ ነው። ጠፍቶ መቅረት፥ ወይም መታደስ የሚል አሳብ አይኖርም። አንዳንድ ሰዎች ሁሉም ያለ ምንም ዓይነት ቅጣት ይድናሉ ብለው ያምናሉ። የእምነታቸው መሠረትም በሐዋርያት ሥራ 3፡21፤ በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፡24-28 እና በቆላስያስ 1፡20 ላይ የተጠቀሰው የተዛባ ትርጉም ነው። እንዲሁም የጻድቃንንና የኃጥአንን ፍጻሜ የሚመለከተውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ችላ በማለት ያልፉታል (ማቴ. 25፡46፤ ዮሐ. 5፡29፤ ሮሜ 2፡8-10፤ ራእይ 20፡10፥ 15)።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.