ትንሣኤዎች

አሳቡ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም፥ አንድና አጠቃላይ የትንሣኤ ቀን አይኖርም። ከጊዜ ሳይሆን ከሰዎች አንጻር ሲታይ ሁለት ዓይነት ትንሣኤ እንደሚኖር ይታወቃል። ይህም የጻድቃንና የኃጥአን ትንሣኤ ነው (ሐዋ. 5፡28-29፤ ሉቃስ 14፡14)። በሞትና በትንሣኤ መካከል ባለው ጊዜ ጻድቃንም ሆን ኃጥአን “በነቃ ሕሊና” ይኖራሉ። አማኙ በዚህ ጊዜ ከጌታ ጋር ሲሆን (2ኛ ቆሮ. 5፡1-8፤ ፊልጵ. 1፡23)፣ የማያምኑት በስቃይ ይኖራሉ (ሉቃስ 16፡19-31)። 

የጻድቃን ትንሣኤ 

የጻድቃን ትንሣኤ የመጀመሪያው ትንሣኤ ሲባል፥ ይህም በተለያየ ደረጃ የሚሆን እንጂ፥ በአንድ ጊዜ የሚፈጸም አይደለም። በክርስቶስ የሞቱት ከቤተ ክርስቲያን ጋር አስቀድመው ይነጠቃሉ (1ኛ ተሰ. 4፡16)። በፍዳው ዘመን የሚዋጁትና በዚያው ዘመን የሚሞቱ ከሺህ ዓመቱ አገዛዝ በፊት ይነሳሉ (ራእይ 20፡4)። በብሉይ ኪዳን የተዋጁትም በጻድቃን ትንሣኤ የመካፈል ዕድል ይኖራቸዋል። እርግጥ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች፥ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን የሚነሱበትን ጊዜ በተመለከተ ያላቸው አሳብ የተለያየ ነው። አንዳንዶቹ በቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ጊዜ ከቅዱሳን ጋር ይነሳሉ ሲሉ፥ ሌሎቹ ደግሞ ትንሣኤያቸው በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይሆናል ይላሉ (ዳን. 12፡2)። ጸሐፊው ሁለተኛውን አመለካከት ይደግፋል። 

የኃጥአን ትንሣኤ 

ስለ ነጩ ዙፋን ፍርድ ስናጠና እንደተመለከትነው፥ ያልዳኑ ሰዎች ከሺህ ዓመቱ በኋላ ይነሱና ወዲያው ይፈረድባቸዋል፤ ከዚያም ለዘላለም ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ (ራእይ 20፡11-15)። በትንሣኤያቸውም የእሳት ባሕር ስቃይ ሊሰማው የሚችልና ለዘላለም የሚኖር ልዩ አካል ይሰጣቸዋል።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.