የፍዳው ዘመን [Tribulation]

በመጽሐፍ ቅዱስ፥ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሌሎች ትምህርቶች ይልቅ ስለ ፍጻው ዘመን በስፋት ተጽፎ እናገኛለን። 

የጊዜው እርዝማኔ 

ዘመኑ በትልቁ የዳንኤል ትንቢት ሰባኛ ሳምንት ይሆናል (ዳንኤል 9፡24-27)። የዚህም ግማሽ ጊዜ 42 ወራት ወይም 1260 ቀናት እንደሚሆን ተጠቅሷል (ራእይ 11፡2-3)። ምንም እንኳን በብዙ አገሮች ወራት የተለያዩ ቀናት ቢኖሯቸውም፥ በብሉይ ኪዳን ጊዜ (ዛሬ በኢትዮጵያም እንደሚታየው) አንድ ወር 30 ቀናትን መያዙ ይታወቃል (ዘፍጥ. 7፡11፥ 24፤ 8፡4፤ ዘኁል. 20፡29፤ ዘጸግ. 34፡8፤ 21፡13)። ይህ 7 ዓመት ለሁለት እኩል የሚከፈለው በዳንኤል 9፡27 መሠረት የሚደረገው ቃል ኪዳን ሲፈርስ ነው። ሁለቱም ክፍሎች ታላቅ ስደትና የደም መፍሰስ የሚታይባቸው ይሆናሉ። 

የፍዳው ዘመን ልዩ ገጽታ 

የፍዳ ዘመን ከዓለም ታሪክ ሁሉ ልዩ እንደሚሆን ጌታችን ተናግሯል (ማቴ. 24፡21)። እርግጥ ይህ ቃል ከተነገረ ወዲህ ብዙ አስከፊ ጊዜያቶች አልፈዋል። እንዲያውም ጌታ ራሱ ተከታዮቹን በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ብሏቸዋል (ዮሐ. 16፡33)። ታዲያ የሚመጣውን የፍዳ ዘመን እጅግ ልዩ የሚያደርገው ምን ይሆን? 

የፍዳውን ዘመን፥ ዓለም ከዚህ በፊት ካያቸው መከራና ፍርዶች የተለየ የሚያደርጉት ሁለት ባሕርያት አሉ። በመጀመሪያ ፍዳው ዓለምን ሁሉ የሚያዳርስ እንጂ፥ በአንድ ቦታ የሚወሰን አይደለም (ራእይ 3፡10)። ስለሆነም በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች በተናጠል የሚደርሱባቸው ስቃዮች የፍዳ ዘመንን መምጣት አያመለከቱም። ምክንያቱም መከራው በጊዜው በዓለም ሁሉ ነው የሚሆነው። የፍዳውን ዘመን ልዩ የሚያደርገው ሌላ ነገር፥ ሰዎች የዓለም ፍጻሜ መቅረቡን መረዳታቸው ብቻ ሳይሆን በሥራቸውም ሁሉ የሚመሰክሩ በመሆኑ ነው። በመጀመሪያ ፍርድ ወቅት ሰዎች ራሳቸውን በጎሬ፥ በዋሻ በተራሮች፥ ለመደበቅ ይፈልጉና በላያችን ውደቁ፥ በዙፋኑም ከተቀመጠው ፊት፥ ከበጉም ቁጣ ሰውሩን” ይላሉ (ራእይ 6፡16)። ሰዎች ስለ መጨረሻው ዘመን መቃረብ ብዙ ከማውራታቸው ጋር፥ አርማጌዶን የሚለውን ቃል እንደ ፍጻሜው ምልክት ይወስዱታል። ይሁን እንጂ ፍጻሜው መድረሱን የሚያምኑ መሆናቸውን በድርጊት አይገልጡም። ሕይወት ያለማቋረጥ እንደምትቀጥል በማመን የንግድ ልውውጥ፥ የገንዘብ ክምችትና የሕንፃዎች ግንባታ ያካሂዳሉ። የፍዳው ዘመን ሲመጣ ግን የሚያጓጓ ነገር አያዩምና ሰዎች ከሕይወት ሞትን ይመርጣሉ። 

አገላለጡ 

የመከራው ዘመን የሚጀምረው፥ የምዕራብ መንግሥታት ፌዴሬሽን መሪ የሆነው የዓመፅ ሰው ከአይሁዳውያን ጋር የትብብር ስምምነት ሲፈራረም ነው (ዳን. 9፡27)። በቤተ ክርስቲያን መነጠቅና በስምምነቱ መካከል ጊዜ ቢኖርም፥ መነጠቁ ግን ከዚያ ቀደም ብሉ ይፈጸማል፡፡ የሰባት ዓመቱ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ልክ ይህ ስምምነት ሲፈረም ነው። በራእይ 6፣ 8፣ 9፣ 16 ሦስት ተከታታይ ፍርዶች ተጽፈዋል። ምናልባት አንዱ አንዱን እየለጠቀ በየተራ ይከናወኑ ይሆናል። እንዲያ ከሆነ በምዕራፍ 6 ላይ የተጠቀሱት የማኅተሙ ፍርዶች፥ በፍዳው ዘመን መጀመሪያ ዓመታት ላይ የሚከናወኑ ይሆናሉ። እነርሱም ጦርነትን፥ ረሃብን፥ ሞትን፥ መሥዋዕትነትንና በዓለም የተፈጥሮ ሚዛን መመሰቃቀልን ያካትታሉ። 

ከዚህ ጊዜ ጥቂት ቀደም ብሉ አንዲት ዓለም አቀፋዊ ሐሰተኛ ቤተ ክርሰቲያን ገናና ትሆናለች (ራእይ 17፡3)፤ በዓለም መንግሥታት ላይም ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ታሳድራለች። ለዚህ ዓላማ በታተሙ ሰዎች ምስክርነትም ብዙ ሰዎች ይለወጣሉ (ራእይ 7)። አንዳንዶች ግን ስለ እውነተኛ እምነታቸው ወዲያውኑ ይሰዋሉ (ራእይ 6፡9-11)። ይህን ሁሉ ጌታ በደብረ ዘይት ስብከቱ ገልጦታል፥ (ማቴ. 24፡4-14፥ ስለ ፍርዱ ቁ. 6-7፣ ስለሚሰውት ቁ. 9፥ ስለ ምስክርነት ቁ. 14)። 

በፍዳው ዘመን አጋማሽ ላይ አንዳንድ ታላላቅ ድርጊቶች ይከናወናሉ። ግብፅ በዓመፁ ሰው ሠራዊት ድል ትሆናለች (ዳን. 11፡40-43)። በፍዳ ዘመን መጨረሻ የሩቅ ምሥራቅ አገሮች አንድ ግንባር ይፈጥሩና ወደ ፍልስጥኤም ይዘምታሉ። ከሰሜን የሚነሳ ጎግ ማጎግ የተባለ ኃይል እስራኤልን ይወራል። ሆኖም በእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ይጠራረጋል (ሕዝ. 38-39)። ልክ በመካከሉ የዓምፁ ሰው ከእስራኤል ጋር የነበረውን ስምምነት ያፈርስና የእስራኤል ጠባቂ በመሆን ፋንታ፥ እንደ አምላክ እንዲመለክ ይፈልጋል (2ኛ ተሰ. 2፡4)። ዓለምን ሁሉ ድል ለማድረግ ይሻል። በዚህ ጊዜ የመጨረሻው የፍዳ ዘመን ስለሚቃረብ እግዚአብሔር ተመጨሪ የፍርድ ጽዋውን በምድር ላይ ያፈሳል። እነዚህ ሁሉ በራእይ 8-9 መለከቶችና በምዕራፍ 16 ጽዋዎች ተገልጠዋል። እነዚህ የተፈጥሮን ሚዛን የሚያመሰቃቅሉ ናቸው። ሰዎች የሚጠጡት ውኃ አይኖርም፥ ብዙዎች ይሞታሉ፥ ሰይጣናዊ ስደት ይነሳል፥ ሕመምና ቁስል፥ የከፋ መመሰቃቀል ይከሰታል። የዓመፅ ሰው ዓለምን ለመቆጣጠር ሲገሰግስ በስተምሥራቅ ከሚነሳው ጠላቱ ጋር ከፍልስጥኤም በስተሰሜን ከሚገኝ አርማጌዶን ላይ ጦርነት ይገጥማል። በጦርነቱ መካከል ጌታ ይገለጥና ጠላቶቹን ሁሉ ድል ያደርጋቸዋል። የዓመፅ ሰውና ሐሰተኛ ነቢያቱ ዘላለም ወደሚሰቃዩበት የእሳት ባሕር ይባላሉ። እንዲህ ያለው ጊዜ መኖሩ ለምን አስፈለገ? ቢያንስ ሁለት ምክንያቶች አሉ፡- መጀመሪያ የሰዎች በደል መቀጣት አለበት። እግዚአብሔር አሁን ስላለው ክፋት ምንም የሚያደርግ ባይመስልም፤ ቅጣቱን በግልጥ የሚሰነዝርበት ጊዜ ይምጣል። ሁለተኛው፥ ሰዎች ሁሉ በምንም እኳኋን ይሁን በምን በገሥታት ንጉሥና በጌቶች ጌታ ፊት መንበርከክ አለባቸው። ከዚህ ሁሉ ይድኑ ዘንድ አሁኑኑ በፈቃደኝነትና በእምነት ወደ ክርስቶስ በመቅረብ ድነትን (ደኅንነትን) መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህን ባያደርጉ፣ ለድነት (ደኅንነት) ሳይሆን ለፍርድ ይሰግዱለታል።

ምንጭ፡- “የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓተ ትምህርት ጥናት”፣ በዶክተር ቻርልስ ሲ. ራይሪ ተጽፎ፣ በሲሳይ ደሳለኝ የተተረጎመ እና በየላፕስሊ/ብሩክስ ፋውንዴሽን የታተመ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.