መንፈስ ቅዱስን በተመለከተ የተለያዩ መረዳቶች የሚታዩት ለምንድን ነው?

እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ ነው። ነገሮችን ሁሉ ክፈቃዱ ዓላማ አኳያ የሚቆጣጠር ብርቱና ኃይለኛ አምላክ ነው። ነገር ግን አፍቃሪና ታጋሽ አምላክም ነው። ልንገምተው ከምንችለው በላይ በሆነ መንገድ ይጠነቀቅልናል። የእግዚአብሔርን ፍቅር የምናይበት አንዱ መንገድ እምነታችን ሙሉ በሙሉ ቃሉ እንደሚያስተምረው ትክክል ባልሆነበት ጊዜ እንኳ በትዕግሥት ከእኛ ጋር ለመሥራት በመፍቀዱ ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከመሥራቱ በፊት እምነታችን ወይም የመሠረተ እምነት አስተምህሮአችን ሙሉ በሙሉ ትክክል እስኪሆን አይጠብቅም። ነገር ግን ባለንበት ሁኔታ ይገናኘንና እርሱን በመምሰል እንድናድግ ያግዘናል። እግዚአብሔር ያለማቋረጥ እንድንማር እርሱንና ቃሉን የበለጠ እያወቅን ለመሄድ ጥረታችንን እንድንቀጥል ይጠብቅብናል። በጊዜው ላስተማረን እውነት በመታዘዝ በትሕትና እስከኖርን ድረስ እኛን እንደ ልጆቹ ለመዛመድ ደስ ይለዋል። 

ይህ እውነት በተለይ ስለ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ መረዳት ላላቸው ክርስቲያኖችም ይሠራል። እግዚአብሔር ስለተሳሳተ እምነታቸው አያሳድጓቸውም። በትዕግሥት እያስተማራቸውም ሳለ እንኳ፥ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ውስጥና በእነርሱ በኩል እንዲሠራ በማድረግ እርሱም አብሮአቸው ሲሠራ ደስተኛ ነው። ነገር ግን ይህንን አጋጣሚ የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት ወይም እምነታችንን የበለጠ ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ጋር እንዲጣጣም ጥረት ላለማድረግ እንደ ምክንያት ልንጠቀም አይገባም። እግዚአብሔር እውነት ነው ብሎ ካስቀመጠው ቃሉ ጋር መስማማታቸውን ለማረጋገጥ እያንላንዱ ክርስቲያን እምነተቹና ተግባሮቹ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላላቸው ዝምድና ልምምዱን የመመርመር ኃላፊነት አለበት (2ኛ ጢሞ. 2፡15 አንብብ)። ስለ መንፈስ ቅዱስ የሥነ መለኮት ትምህርት ይህን መጽሐፍ የምናጠናው ለዚህ ነው። 

ጥያቄ፡- እግዚአብሔር ታጋሽ መሆኑና ከእኛ ጋር መሥራት ከመጀመሩ አስቀድሞ በሁሉም ነገር ፍጹም ሆነን መገኘትን የማይጠብቅብን መሆኑ የሚያበረታታን እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ላላ መንፈስ ቅዱስ ና ስለ እገልግሎቱ ከሚታወቁት የተለያዩ አመለካከቶች እንዳንዶቹን ዘርዝር። የተለያዩ አመለካከቶች የሚታዩበት ምክንያት ለምን ይመስልሃል? 

ስለ መንፈስና ህልውናው ስለሚረጋገጥበት ሁኔታ ክርስቲያኖች ባሉአቸው አንዳንድ ግንዛቤዎች ላይ ይለያያሉ ብለናል። ልዩነት የሚያሳዩበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከመመልከታችን በፊት ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ በሚሰጡ ትምህርቶች በአብዛኛዎቹ አሳቦች ላይ እንደሚስማሙ መጥቀስ አስፈላጊ ነው። የእሳብ ልዩነት በሚታይበት ወቅት የምንስማማባቸው እውነቶች ከማንስማማባቸው ሰብዙ እጅ የላቁ መሆናቸውን ለማጤን እንዘነጋለን። ምናልባት 80% ያህል መንፈስ ቅዱስን አስመልክቶ የተጻፉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቶች ሁሉም ክርስቲያኖች ያምናሉ። ልዩነት አሳይተው የሚከራከሩ 20% በሚያህሉት ሲሆን እነዚህ ልዩነቶች ሰው በእግዚአብሔር ፊት ያለውን የድነት (ደኅንነት) አቋም የሚያናጉ አይደሉም። ስለዚህ በልሳን ስለመናገር፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፥ ስለ ተአምራትና የመሳሰሉ ልዩነት ወደምናሳይባቸው አካባቢዎች በምንገባበት ወቅት፥ የሚያስማሙንን ጠቃሚ ነጥቦች በማስታወስ በትሕትናና እርስ በርስ በመቀባበል ልዩነቶቻችን ማስተናገድ ይገባናል። 

በመንፈስ ቅዱስ ሚና ላይ ክርስቲያኖች ይህን ያህል ልዩነት የምናሳየው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ነገር ግልጽ አይደለምን? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ሰዎች እውነትን፥ በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጡ እውነቶችን እንኳ ሳይቀር የሚረዱት እንዴት እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡

ዝሆን ምን እንደሚመስል ለመረዳት ስለ ሞከሩ አራት ዓይነ ስውራን የሚናገር አንድ ታሪክ አለ። ወደ ጫካ ገቡና ዝሆኑ ወዳለበት ደረሱ፤ አንደኛው ኩምቢውን ዳሰሰ፥ እንዱ እግሩን ዳሰሰ፥ ሌላኛው ጐኑን የመጨረሻው ደግሞ ጭራውን ዳሰሰ። ከዚያ በኋላ ዝሆን ምን እንደሚመስል እያንዳንዳቸው ለሌላ ሰው መግለጫ ለመስጠት ሞክሩ። ዝሆን ምን እንደሚመስል ሲናገሩ የመጀመሪያው ዝሆን እንደ ትልቅ የውኃ ማስተላለፊያ ቧንቧ ነው አለ። ሁለተኛው ዝሆን እንደ ትልቅ ግንድ ነው እለ። ሦስተኛው ደግሞ የቤት ግድግዳ ነው የሚመስለው ሲል፥ የመጨረሻው አለንጋን ይመስላል አለ። አራቱም ዓይነ ስውራን የተናገሩት በእነርሱ እምነት ያቀረቡት እውነታኛና ትክክለኛ መግለጫ ነው ብለው ያመኑበትን ነገር ነው። ሆኖም ግን እያንዳንዳቸው የተረዱት ከፊል እውነት ስለነበር ለሌሎች ያቀረቡት ሙሉ እውነት ያልያዘና ሰዎችን ወደተሳሳተ አመለካከት የሚመራ ነበር። 

ማናችንም ብንሆን ስለ እውነት ፍጹም የሆነ መረዳት እንደሌለን መገንዘብ ይገባናል። የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እውነት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ፊት ለፊታችን ቢኖረንም እንኳ እንደ እራቱ ዓይነ ስውራን ከፊል እውነትን ብቻ እናያለን። በዓለም ላይ የሚገኙ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ክርስቲያኖች ሁሉ የሚያጠኑት አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም እንኳ እንዳንድ ክፍሎችን በተለያየ መንገድ የሚረዱት በዚህ ምክንያት ነው። የመጀመሪያው ምእተ ዓመት ታላቅ የሥነመለኮት አስተማሪ የነበረው ጳውሎስ እንኳ ይህን እውነት ተቀብሏል። «ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ» (1ኛ ቆሮ. 13፡12)። 

መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ክርስቲያኖች በተለየ መንገድ እንድንረዳው የሚያደርጉን ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ሌሎች በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም እንኳ የእግዚአብሔርን ቃል ከሌሎች በተለየ መንገድ እንድንረዳ የሚያደርጉን ዐበይት ነጥቦች ቀጥለው ተዘርዝረዋል። 

1. ያደግንበት ባሕል፡- እያንዳንዳችን ያደግነው ከወላጆቻችን በተቀበልነው ልዩ ባሕል ውስጥ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ይህን ባሕል የተቀበሉት ከእነርሱ ቀደም ብለው ከነበሩት ወላጆቻቸው ነው። ለምሳሌ በሰሜን ኢትዮጵያ አማራ ወይም ትግሬ ሆነው ያደጉ ሰዎች እንደ ኦሮሞ ወይም ወላይታ ሆነው ካደጉ ወይም በደቡብ ኢትዮጵያ ካሉ ሌሎች ሰዎች ባሕላቸው ይለያል። ያደግንበት ባሕል አስተሳሰባችንን፥ ለለ አከባቢያችን ያላንን አመለካከትና እውነትን በምንረዳበት ሁኔታ ሁሉ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል። ባሕላቸው ከእኛ በተለየ ሕዝቦች መካከል ስንኖር ወይም ከእነርሱ ጋር ስንሠራ ይህን እውነት ሁላችንም ተለማምደናል። በባሕላችን የሚፈቀድ አንድን ነገር መናገር ወይም ማድረግ በሌላው ባሕል የሚያስነቅፍ ሊሆን ይችላል። በዚህም ምክንያት ሌላው ሰው በተሳሳተ መንገድ ሊረዳና ምናልባትም ጸብ ሊፈጥር ይችላል። ሁላት ባሕሎች በጣም ተመሳሳይ ከሆኑ የባሕል ግጥታቸው ዝቅተኛ ይሆናል። በባሕሎች መካከል ያለው ልዩነት የሰፋ ከሆነ ያለመግባባቱም በዚያው መጠን የሰፋ ይሆናል። እንደ አሜሪካ ባሉ ምዕራባውያን አገሮች ያደጉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የሚረዱበት መንገድ በእስያና በአፍሪካ ካደጉ ሰዎች እጅግ የተለየ ነው። ባለን የተለያየ ባሕላዊ ልዩነት መሠረት መጽሐፍ ቅዱስን ስንመለከትና እውነቶችን ለመረዳት ስንጥር ብዙ ጊዜ እንደ እራቱ ዓይነ ስውራን ብዙ ጊዜ የምናየው የእውነትን የተለያዩ ገጽታዎች ነው። 

2. ሃይማኖታዊ ልዩነት፡- ልጆች ሆነን የተማርነው የሃይማኖት ትምህርት እውነትን በምንረዳበት መንገድ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ያደርጋል። ለምሳሌ እንዱ ሙስሊም ሌላው ኦርቶዶክስ የሆኑ ሁለት ኦሮሞዎች ነገሮችን የሚረዱት ፍጹም በተለያየ መንገድ ነው። እንደዚሁም በመካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ወይም በቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ወይም በሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ብናድግ ልዩነቶችን እናሳያለን። ልጆች ሆነን የተማርናቸው እውነቶች የእግዚአብሔርን ቃል እንዴት እንደምንመለከትና እንዴት እንደምንረዳው ተጽእኖ ያሳድራሉ። እንደ ባሕል በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል ያለው ልዩነት ከፍተኛ በሆነ ቁጥር በክርስቲያኖች መካከል ያለው የአሳብ ያለመግባባት እየጨመረ ይመጣል። እንደ ሙሉ ወንጌል ባሉ ፔንትኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ያደጉ ሰዎች እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያላቸው መረዳት ካሪዝማቲክ መሠረት በሌላቸው አብያተ ክርስቲያናት ካደጉቱ በጣም ይለያል። ታሪካዊ መነሻቸው ተመሳሳይ ስለሆነ የባፕቲስትና የቃለ ሕይወት አተረጓጐም በጣም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።  

3. ዕድሜያችን፡– በሁሉም ዘመናት በወጣቶችና በእድሜ በገፉ ሰዎች መካከል ውጥረት ይታያል። ወጣቶች ከፍተኛ ምኞትና ኃይል ያላቸው፥ የሚመጣውን አደጋ ለመጋፈጥ የበለጠ ፈቃደኛ የሆኑ፥ ለለውጥ በጣም የተጋለጡና አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር በጣም ደፋሮች ናቸው። በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ዝንባሌ ደግሞ ነገሮችን እንዳሉ በተረጋጋ ሁኔታ መቀጠላቸው ነው። ነገሮች እንዲለወጡና ስሜታቸው ራሳቸውን እንዲቆጣጠራቸው ብዙ የማይፈልጉ ናቸው። ስለዚህ ዕድሜ ስው እውነትን በሚረዳበትና ይህ እውነት በአምልኮውና በዕለታዊ ሕይወቱ በሚገለጽበት ሁኔታ ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። 

የቤተ ክርስቲያን ዕድሜም ልዩነት ያመጣል። ብዙ ጊዜ አዲስ አብያተ ክርስቲያናት በራእይና ለክርስቶስ ባላቸው የመጀመሪያ ፍቅር የተሞሉ ስለሆኑ ወደ ስሜተኛነት ያዘነብላሉ። አዳዲስ ትምህርቶችን ይወዳሉ። በልሳን መናገር፥ ተአምራትን ማድረግ ወይም ስሜታዊ የሆነ የአምልኮ ስብሰባን ያካሂዳሉ። በእግዚአብሔር ቃል ላይ ከማተኮር በአምልኮና በኅብረት ጉዳይ ላይ ያተኩራሉ። ነገር ግን እየበሰሉ በሄዱ ቁጥር ቤተ ክርስቲያን መቀየር ትጀምራለች። የአምልኮአቸው ጊዜ ብዙ ስስሜት ላይ ያልተመሠረተ ሆኖ በቃሉ ራሱን የገለጠውን እግዚአብሔርን ወደ መረዳት የሚያዘነብል ሲሆን፥ ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ላይ ያተኩራል። በስሜታዊ አምልኮ ላይ የሚደረገው ትኩረት ይቀንስና ሚዛኑ እውነትን በመረዳት ላይ ይሆናል። እንደ የወንጌል ምስክርነት፥ የሰንበት ትምህርት፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትና በመሳሰሉት አገልግሎቶች ላይ የሚደረገው ተሳትፎ ያይላል። ሁለቱን አጣምዶና አጣጥሞ መጓዙ መልካም ነበር። ነገር ግን ለአብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት አስቸጋሪ ነገር ነው። ሆኖም ዓላማችን የእግዚአብሔርን ቃል በማወቅ ለመታዘዝና ሌሎችን በወንጌል ለመድረስ እስከሆነ ድረስ የአምልኮ ፍቅርንና የእግዚአብሔርን ኃይል አጣምረን በመካከላችን ብንላማመድ ብርቱዎች እንሆን ነበር። 

ትልቁ አደጋ እጅግ የደንብና የሕግ ሰው ከመሆናችን የተነሣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕይወት ከተመናመነ ነው። አንድ ቤተ ክርስቲያን በአምልኮ ሥርዓት ብቻ የምትንቀሳቀስ፥ ምእመኑ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቶው አካሄድ የማይደሰቱ፥ ሁልጊዜ ከመታደስ ይልቅ ትውፊቷን ለማስጠበቅ የምታብር ከሆነ፥ ያች ቤተ ክርስቲያን በመሞት ሂደት ላይ ነች ማለት ነው። ሥሩ የሞቱበት ዛፍ የሞቱ ሽታ በቅርንጫፎችና በቅጠሎቹ ወዲያውኑ መታየት እንደሚጀምር ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ውስጣዊ 

ሕይወትና አምልኮዋ የማይታደስ ከሆነ መሞቷ አይቀርም። ለኢየሱስ ያለን ፍቅር በየዕለቱ ካልታደሰ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሁል ጊዜ ለለውጥ ክፍት ካልሆንንና ለኢየሱስ ያለንን አምልኮ ዘወትር በአዲስነት ካልጠበቅን እንደ ሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ እንገኛለን ራእይ 3፡14-22 ተመልከት)። 

ጥያቄ፡ ሀ) ሰዎች እየበሰሉ ሲሄዱ እንዲለወጡ የሚፈልጓቸውን ነገሮች ያየኸው እንዴት ነው? ለ) ቤተ ክርስቲያን በዕድሜ እየገፋችና የበለጠ እየተደራጀች ስትሄድ የምታሳየውን ለውጥ ያየኸው እንዴት ነው? ይህ መልካም ወይም መጥፎ የሚሆነው እንዴት ነው? ሐ) አንዲት ቤተ [ክርስቲያን ሕያው የሆነ ግንኙነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከማድረግ ይልቅ [በትውፊቶቿ ላይ ማተኮር ስትጀምር ሞቷም መጀመሩን ያየኸው እንዴት ነው? 

4. የግል ባሕርያችን፡- እግዚአብሔር ሁለት ዛፎችን እንኳ ፍጹም ተመሳሳይ አድርጐ አልፈጠረም። በተመሳሳይ ሁኔታ እግዚእብሔር ሙሉ በሙሉ አንድ ዓይነት የሆኑ ሁለት ሰዎችን አልፈጠረም። አንዳንዶቻችን ክሊላችን ፈጽሞ የተላየን . ነን። እግዚአብሔር እኛን ሲፈጥረን በምንወዳቸውና በምንጠላቸው ነገሮችም የተለያየን አድርጐ ፈጥሮናል። አንዳንዶቻችን ከፍተኛ ድምፅንና ግርግርን እንወዳለን። ሌሎቻችን ደግሞ ፀጥታንና እርጋታን እንወዳለን። አንዳንዶቻችን በአምልኮ ጊዜያችን እልልታን ስንወድ፥ ሌሎቻችን አክብሮትና ፀጥታን እንወዳለን። አንዱ ከሌላው የሚሻል ወይም የሚብስ አይደለም። ብዙ ጊዜ የምንመርጠው ነገር ማንነታችንን ያመለክታል። 

ጥያቄ፡– ሀ) እነዚህ አራት ነገሮች በሰዎች መካከል ልዩነቶችን ሲፈጥሩ ያየኸው እንዴት ነው? ለ) እነዚህ ነገሮች ክርስቲያኖች ላለ መንፈስ ቅዱስ ባላቸው መረዳት ላይ እንዲከራከሩ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለህ የምታስበውስ እንዴት ነው? 

ሰዎች ነገሮችን የሚያዩት በተለያየ መንገድ መሆኑን መገንዘብ በብዙ መንገድ ይረዳናል። በቅድሚያ ትሑት እንድንሆን ይረዳናል። ኩሩ ከመሆንና ሊታወቅ የሚቻለውን ሁሉን ነገር የምናውቅ መስለን ከመገኘት ይጠብቀናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኙ አስቸጋሪ ክፍሎች ላይ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች ለጥያቄአቸው ግልጽና የማያሻማ መልስ የመፈለግ ዝንባሌ አላቸው። መልሱ ይህና ይህ ነው ብለው በቀጥታና ባለማወላወል አክርረው የሚነግሯቸውን ይፈልጋሉ። «በበኩሌ መልሱ እንዲህና እንዲህ ነው ብዬ አስባለሁ ነገር ግን ይህንኑ እውነት ሌሎች በተለየ መንገድ ይረዱታል» ብለው በታማኝነት የሚነግሩአቸው ሊገጥሙአቸው ይደነግጣሉ። ሌሎች ክርስቲያኖች ግልጽ ስላልሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተለየ እመለካከት ቢኖራቸውም፥ በቀኖናዊነት ትክክለኛው መልስ የእኛ ትርጉም ብቻ ነው ብለን ካልን፥ ይህ የመታበያችን ምልክት ነው። 

ነገር ግን ይህ እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ላይ የተላየ እተረጓጐም ያላቸውን ሰዎች ለመቀበል ሊረዳን ይገባል። እኛ የምናውቀውና የምናየው በከፊል እንደሆነ ከተረዳን በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ አሳብ ላይ የተለየ እተረጓጐም ያላቸውን ሌሎች ሰዎች መንፈሳዊ እንዳልሆኑ አድርገን ሳንቆጥር የምንቀበል እንሆናለን። 

ይህ እውነት በሕይወት ላይ ደስታን ይጨምራል። በዓለም ላይ የሚገኙ ዛፎች በሙሉ አንድ ዓይነት ሲሆኑ ዓለም ውብ ልትሆን እንደማትችል ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ሰው አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ቢኖረው ወይም በእንድ ዓይነት መንገድ አምልኮ ቢፈጽም ያማረ አይሆንም ነበር። ልዩነትና ዓይነት ውበትን ይፈጥራሉ። 

መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት ጉዳይ ሲነሣ፥ እንደ እውነቱ ከሆነ የበለጠ በትክክል እንድንረዳ ከተፈለገ አንዳችን ለሌላችን አስፈላጊ እንሆናለን። ከአራቱ ዓይነ ስውራን መካከል አንዱ ብቻ ዝሆን ምን እንደሚመስል እንዲናገር ቢደረግ ሰዎች ስለ ዝሆን የሚኖራቸው መረዳት የተሳሳተ ይሆን ነበር። ነገር ግን አራቱም ዝሆንን እንዲገልጹ ቢደረጉና የአራቱም አመለካከት እንዲዋሀድ ሲደረግ ዝሆን ምን እንደሚመስል የበለጠ ትክክለኛና ሙሉ የሆነ ግንዛቤ ይገኛል። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነትም እንደዚሁ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ ለመረዳት ምዕራባውያን ከአፍሪካና ከእስያ ሰዎች ሊማሩ ይገባል። ደግሞም የአፍሪካና የእስያ ሰዎች ከምዕራባውያን ሊማሩ ይገባል። በሰሜን ኢትዮጵያ ያሉ ሰዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ያሉትን ሊሰሟቸው ይገባል። ከአማራ ነገድ የሆኑት ከወላይታ ሊሰሙ ይገባል። ትላልቅ ሰዎች ከወጣቶች ሊሰሙ ይገባል። የካሪዝማቲክ እንቅስቃሴ አማኞች በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ የሌሉትን ሊሰሙ፥ እነዚህም ደግሞ እነዚያን ሊሰሙ ይገባል። ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል ያለንን መረዳት በግልጥና በታማኝነት ስንነጋገር እውቀታችን የበለጠ ወደ ሙሉነት ያድጋል። 

በእርግጥ አንድ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ አለ። የምንነጋገረው መጽሐፍ ቅዱስን ቅን በሆነ መንገድ በመተርጐም ስለሚፈጠር ልዩነት ነው። ይህ ማለት የእውነት ሁሉ ምንጭ በሆነው ጉዳይ መስማማት አለብን ማለት ነው። ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን ለመለየት የምንጠቀምበት ብቸኛ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ሁላችንም መስማማት አለብን። ከመልእክት የምንሰማው ነገር የመጨረሻው ምንጭ አይደለም። በቪዲዮ የምናየው የመጨረሻ ምንጭ እይደለም። በሕልምና ሰራእይ የምናያቸው ወይም ከጌታ መገለጥን አገኘን ከሚሉ ሰዎች የምንሰማቸው ነገሮች የመጨረሻ ምንጭ አይደሉም። እነዚህ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያስተምረው ትምህርት መፈተን አለባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነና የመጨረሻ ባለሥልጣናችን ወይም ገላጋያችን እንደሆነ ሁላችንም ልንስማማበት ያስፈልጋል። ያለአንዳች ስሕተት እግዚአብሔር ምን እንደሚመስል የሚያስተምረን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እንደሆነ ካላመንን ለግላዊ ስሜቶቻችን ወይም ትርጉሞቻችን በመጋለጥ እውነት የሆነውንና ያልሆነውን ለመለየት የማንችልበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን። ስለዚህ እንደ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ያለንን የእምነት ትምህርት ጨምሮ በነገሮች ሁሉ ላይ የመጨረሻ ባለሥልጣን መሆኑን እምነን መጠቀም አለብን። ካልተስማማን አለመስማማታችን መጽሐፍ ቅዱስን በምንረዳበት መንገድ ይሁን እንጂ የተለያዩ የሥነ መለኮት ትምህርት አስተማሪዎች ወይም የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በሚሉት ጉዳይ አይሁን። 

የመሠረተ እምነት ትምህርታችንን መዘርጋት ያላብን በመጽሐፍ ቅዱስ እንጂ በሌላ እንዳልሆነ ሁላችንም ከተስማማን የምንጀምረው በጋራ መሠረት ላይ ይሆናል። በተጨማሪ ሊዋሽ የማይችል እግዚአብሔር ለአንዳችን አንድ ነገር ለሌላችን ሌላ ተቃራኒ የሆነ እውነት አይነግረንም። በጥቂቱ እንለያይ ይሆናል እንጂ ነገር ግን ልዩነታችን ትክክለኛ የሆነውን ነገር ትክክለኛ ኈእንዳልሆነ የሚያሳይ ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ስሕተት ነው ብሎ ያስቀመጠውን ነገር ትክክለኛ የሚያደርግ አይሆንም። 

በትምህርታችን ላይ ሚዛናዊ የመሆን አስፈላጊነት ለማንኛይቱም ቤተ ክርስቲያን እጅግ በትምህርታችን ታላቅ አደጋ ከሚባሉ ነገሮች ዋናው አንድን እውነት እጅግ አጥብቆ በመያዝ መጽሐፍ ቅዱስ በሚዛናዊነት መያዝ በሚገባቸው በርካታ እውነቶች የተሞላ መሆኑን መዘንጋት ነው። ክርስቲያኖችን ወደ ሐሰት ትምህርት የሚመሩ ብዙ ኑፋቄዎች ሌሎች እውነቶችን ሁሉ ትተው በአንድ እውነት ላይ ያተኩራሉ። እንደ መንፈስ ቅዱስ ባለ አንድ እውነት ላይ ብቻ ትኩረታችንን ካደረግን በትምህርታችንና በሕይወታችን ሚዛን እናጣለን። በልሳን በመናገርና ተአምራትን በማድረግ ላይ ብቻ የሚያተኩር ክርስቲያን ሚዛኑን ያጣል፤ ደግሞም የወንጌልን ኃይል ሳይለማመድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎችን ብቻ ለማወቅ የሚጥር ሰው ሚዛኑን ያጣል። ሚዛናዊ ለመሆን ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ወጥነት ባለው መንገድ ማጥናት ይጠበቅብናል። ላለ በትምህርታችንና በሕይወታችን ሚዛን እናጣለን። በልሳን በመናገርና ተአምራትን በማድረግ ላይ ብቻ የሚያተኩር ክርስቲያን ሚዛኑን ያጣል፤ ደግሞም የወንጌልን ኃይል ሳይለማመድ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነታዎችን ብቻ ለማወቅ የሚጥር ሰው ሚዛኑን ያጣል። ሚዛናዊ ለመሆን ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱሳችንን ወጥነት ባለው መንገድ ማጥናት ይጠበቅብናል። ስለ አንድ ርእስ የተላያዩ ጥቅሶችን በመጥቀስ ማጥናት ብቻ ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን በመውሰድ ማጥናት ያስፈልጋል። በአንድ ጥቅስ ላይ ያለ እውነትን ለመረዳት ስንፈልግ የክፍሉን ሙሉ አሳብ ለማግኘት ከጥቅሱ በፊትና በኋላ ያለውንም ማንበብ ያስፈጋል። ከዚህ ጋር የሚያያዙ ጥቅሶችንም ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ማየት ያስፈልጋል። 

ጥያቄ፡– ሀ) በኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን ወደ ሐሰት የሚመሩ አንዳንድ መናፍቃንን ዘርዝር። ለ) እነዚህ መናፍቃን ሚዛናዊ ያልሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በመያዛቸው ስሕተት ላይ የሚወድቁት እንዴት ነው? ሐ) አንዳንድ ክርስቲያኖች በማስተማር አገልግሎታቸውና በሕይወታቸው እንዴት ሚዛናዊ እንደማይሆኑ ሌሎች ምሳሌዎችን ጥቀስ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.