መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ

ከ400 ዓመታት ፀጥታ በኋላ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደገና መሥራት ጀመረ። በብዙ መንገዶች አገልግሎቱ በብሉይ ኪዳን ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ነበር። ነገር ግን በመጀመሪያ በኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት በኋላም በቀደመችው ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በብሉይና በአዲስ ኪዳን መካከል የነበረው የሽግር ጊዜ ተጀመረ። በወንጌላት ውስጥ አዲሱ ዘመንና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከነበረው አገልግሎቱ ተመሳሳይ ነበር። በጥንቷ እስራኤል በብዙ መሪዎች ሕይወት እንደሆነው መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ በመውረድ የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመራና እንዲያገለግል ኃይልን አጐናጸፈው። እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት መንፈስ ቅዱስ በሁሉም የእግዚአብሔር ሰዎች ውስጥ ወደሚኖርበት ዘመን የገባንበትን የሽግግር ጊዜ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እናገኛለን። 

አንድ ቀን የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ኤልሳቤጥ በመምጣት ከማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ የሚያድርበት ሕንን እንደምትወልድ እንደነገራት ያ የእግዚአብሔር የዘመናት ፀጥታ ተገፈፈ (ሉቃስ 1፡8)። በዚህም የመሢሑ መንገድ ጠራጊ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ መኖሩ የተረጋገጠው በተአምራት ሳይሆን ስለ መሢሑ መምጣት ባስተላለፈው ጠንካራ መልእክት ነበር። 

ሀ. መንፈስ ቅዱስና የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ 

ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስናስብ አምላክነቱን በአንደኛ ደረጃ ፥ ሰው መሆኑን ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ እናያለን። ምንም እንኳ ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ ባያስፈልገውም ፍፁም ሰውም ነበር። እንዲያውም የፍጹም ሰው ሦሳሌ ነው ማለት እንችላለን። ጳውሎስ ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጋር ያወዳድረዋል። እርሱ ኋለኛው እቶም፡ ሁለተኛው ፍጹም ሰው ነው (ሮሜ 5፡14-17)። ኢየሱስ ልክ እንደ እኔና እንደ አንተ ፍጹም ሰው ነበር። ሰው ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ አስፈልጐት ነበር። በምድር ላይ በኖረው ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፍጹም የሆነ ሕይወትን እንዴት መኖር እንደምንችል የተሟላ ምሳሌ ይሰጠናል። እርሱ ልንከተለው የሚገባን ምሳሌያችን ነው። 

ወንጌላትን በምናነብበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ዋና ተሳታፊ እንደነበር እናያለን። የኢየሱስ ልደት መረዳታችንን የሚያልፍ ተአምር ነበር። መንፈስ የሆነው ዘላለማዊ እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ለብሶ ፍጹም ሰው እንዴት ሊሆን ይችላል? እግዚአብሔር በሴት ማኅፀን ውስጥ እንደማንኛውም ሕፃን የሚያድግ ቅንጣት ዘር እስኪያክል ድረስ እራሱን እንዴት ለማሳነስ ቻላ? አናውቅም። መልሱን ግን የምናገኘው በመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ውስጥ ነው። ተአምራቱን ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ቃል ትንሽ ዘር ሆኖ በማርያም ማኅፀን ውስጥ በማደር ማደግ ጀመረ (ሉቃስ 1፡35)። እግዚአብሔር አብ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለኢየሱስ ሥጋዊ አካልን አዘጋጀለት (ዕብ 10፡5)። በምድር ላይ እንደ ፍጹም ሰው ኖረ። ልክ እንደ እኛ ሰው ሆኖ በሰብአዊ ውስንነት የተገደበ ነበር። ለምሳሌ ኢየሱስ እንደ መንፈስ በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኝ ነበር። ነገር ግን ከመቅጽበት በሥጋዊ አካል ተገደበና በአንድ ጊዜ በአንድ ስፍራ ብቻ የሚኖር ሆነ። ሰብአዊ ህልውናን መለማመድ እንዲችል አብዛኛዎቹ መለኮታዊ ኃይላቱ ውስን ሆኑ። በዕብራውያን መጽሐፍ ዘላለማዊ አምላክ የሆነው ኢየሱስ «በመከራው መታዘዝን ተማረ» (ዕብ. 5፡8) ተብሎ ተጽፎለታል። ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥጋዊ አካል ላይ የሚደርስ ሕመም፥ መከራ፥ ረሃብ፥ ስደት፥ ስድብና መናቅ የመሳሰሉ፥ እኛ በሰብአዊነታችን የምንለማመዳቸው ነገሮች ይደርሱበት ጀመር። ኢየሱስ የተለየ የሆነው ኃጢአታዊ ተፈጥሮ ስላልነበረው እና ኃጢአትን ስላላደረገ ብቻ ነው። ኃጢአት የሌለበት ፍጹም ሰው በመሆኑ በችግራችን ሁሉ ሊራራልን የሚችል መልካም ሊቀ ካህናችን ነው (ዕብ 4፡14-16)። ኢየሱስ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ስለሚያውቅና የሚያስፈልገንንም ስለሚሰጠን ምንም መካከለኛ (አማላጅ) አያስፈልግም። 

ጥያቄ፡-የምናልፍበትን ሐዘን ሁሉ ኢየሱስ እንደሚገነዘብ ማወቃችን በምን በምን መንገድ ያበረታተናል? 

ኢየሱስ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ስለሆነ አሁን ጊዜ ወስደህ አወድሰው። ማስታወስ ያለብን ኢየሱስ ህልውና ያገኘው መንፈስ ቅዱስ በማርያ ማኅፀን ተአምር በሠራ ጊዜ እንዳልነበር ነው። ኢየሱስ አምላክ ነው። ከእግዚአብሔር አብ ጋር በዘላላማዊ ትስስር እንደ ልጅ ሆኖ ይኖር ነበር። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ከድንግል ሲወለድ አልነበረም። ሥጋዊ አካልና ሌላ ተፈጥሮ የተሰጠው ከድንል በተወለደ ጊዜ ነበር። የሰውን ተፈጥሮ በመውሰፋ ሰውና አምላክ ማለትም ፍፁም አምላክና ፍፁም ሰው ያለው አካል ሆነ። መንፈስ ቅዱስ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ሰብዓዊ ተፈጥሮ ከሰጠው ቅጽበት ጀምሮ በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ ሀነ። ለዘላለም በሁለቱም ተፈጥሮው ይኖራል። 

[ማስታወሻ፡- አብዛኛው የክርስቲያን ክፍሎች የሮማ ካቶሊክና የፕርቴስታንት) ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚለዩት በኢየሱስ ሰብዓዊና መለኮታዊ ተፈጥሮ መረዳት ላይ ነው። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ በተቀጻሚ መለኮት ሲሆን ሰብአዊ ተፈጥሮው የመለኮታዊ ተፈጥሮው ጥገኛ ሆኖ ውስንና ጊዜያዊ ነው ብላ ታስተምራለች። ይህ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ መለኮታዊ ባሕርይ ላይ እንድታተኩር አድርጓታል። በዚህ አካሄድ ኢየሱስ እውነተኛ ሰውና ላሰው ልጅም የሚራራ መሆኑ ስለማይታይ፥ ሰዎች እነርሱን የበለጠ ወደ ሚገነዘቡና በእግዚአብሔርም ፊት ሊወክሉአቸው ወደሚችሉ፥ እንደ ማርያምና ገብርኤል ወደ መሳሰሉ እማላጆች ፊታቸውን ያዞራሉ። የካቶሊክና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት ግን ኢየሱስ በአንድ አካል ውስጥ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ያምናሉ።] 

ኢየሱስ በተወለደበት አካባቢ የነበሩ ሰዎችም በመንፈስ ቅዱስ በሚገባ ተነክተዋል። የዮሐንስ እናት ኤልሳቤጥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ኢየሱስ ልዩ እንደሚሆን ተነዘበች (ሉቃስ. 1፡41-45)። ዘካርያስም (ሉቃ. 1፡67-69) እንደ ስምዖን (ሉቃስ 2፡25-32)፥ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ሕፃኑ ኢየሱስ የእስራኤል መሢሕና የዓለምም አቶኝ እንደሆነ እንዲገነዘቡ አደረጋቸው። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ አገልግሎት 

የኢየሱስ መምጣት መንገድ ጠራጊና የአክለት ልጅ የሆነው መጥምቁ ዮሐንስ አገልግሎቱን በጀመረበት ጊዜ የሚመጣው መሢሕ ዋና አገልግሎቱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ማጥመቅ እንደሆነ ይናገር ነበር (ማቴ. 3፡11)። እሳት የሚያመለክተው በጰንጠቆስጤ ዕለት በሐዋርያት ላይ የወረደው (የሐዋ. 2፡1-4) እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳኖችን ሳይሆን ኢየሱስ በእርሱ ባላመኑት ላይ ስለሚያመጣው ፍርድ ነበር። ንስሐ ካልገቡ በስተቀር ታላቅ የእግዚአብሔር ጽኑ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ዮሐንስ አስጠንቅቋቸው ነበርና። 

በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስን በእነርሱ ላይ የሚያፈስሰው ኢየሱስ እንደሆነ ዮሐንስ ለሕዝቡ ነገራቸው። በዚህም በብሉይ ኪዳን ነቢያት የተነገረለትን አዲሱን የመንፈስ ቅዱስ ዘመን የሚያስጀምረው ኢየሱስ እንደሆነ ዮሐንስ ይናገር ነበር። ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በኢየሱስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል የሚኖረውን የቅርብ ቁርኝት አስቀድሞ እመልክቷል። 

ኢየሱላ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ 30 ዓመት ሞልቶት በሕዝቡ መካከል አገልግሎቱን መስጠት እስከጀመረበት ጊዜ ድረስ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ምን ዓይነት ግንኙነት እንደነበረው ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ምንም ፍንጭ የለም። አንዳንድ ሰዎች ስለእነዚያ ዓመታት አስቂኝ የሆኑ ታሪኮችን ቢናገሩም መጽሐፍ ቅዱስ ግን በፀጥታ ያልፈዋል። ግልጽ የሆነው ነገር ቢኖር ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል አገልግሎቱን በጀመረበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በቅርብ ይተባበረው እንደነበር ነው። 

1. መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ የወረደው በሕዝቡ ዘንድ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስጀመር ነበር፡ ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል የሚሰጠው እገልግሎት የተጀመረው በዮሐንስ እጅ በተጠመቀበት ወቅት ነበር። መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን ባጠመቀበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ በርግብ አምሳል በኢየሱስ ላይ ወረደ። ይህ የኢየሱስ «መቀባት» ተብሎ ይጠራል (ሉቃስ 4፡18፤ የሐዋ. 4፡27፤ ዕብ 1፡9 አንብብ)። ይህ የመንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ መውረድና እርሱን መቀባት ኢየሱስ ከዚህ ጊዜ በፈት መንፈስ ቅዱስ አልነበረውም ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ለይቶ ይህንን ባይናገርም እንኳ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላው መንፈስ ቅዱስ በማርያም ማኅፀን ውስጥ ታምራዊ ተግባሩን በፈጸመበት ጊዜ ይሆናል። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ዘመን ዳዊት ዘይት ተቀብተ ለንጉሥነት ሊለይ መንፈስ ቅዱስ እንደወረደበት ሁሉ፥ የኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቀባትም የተከናወነው ለሕዝባዊ እገልግሎቱ ላመለየት ነበር። ኢየሱስ በሕዝቡ መካከል በሰጠው አገልሎት የመንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ጋር መሆን የእግዚአብሔርን ቃል በማወጅ ለድሀች መልካም በማድረግና ባደረጋቸው ተአምራት ይገለጥ ነበር (ኢሳ. 61፡1-2፤ ሉቃስ 4፡18-21)። 

2. መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ሞላው፡- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ተሞላ ልንል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ሆነ ማለታችን ነው። ፍጹም ሰው የሆነው ኢየሱስ ያለማቋረጥ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ነበር። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለኢየሱስ በሙላት ሰጠው (ዮሐ 3፡34)። ኢየሱስን የሞላው መንፈስ ቅዱስ ስኢየሱስ ተግባራት ሁሉ ውስጥ በቅርበት ይሳተፍ ነበር። 

3. መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ይመራው ነበር፡- መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ ጋር እንደነበረና እንደሞላው የምናረጋግጥበት አንድ መንገድ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ይመራው ላለነበር ነው (ሉቃ. 4፡1)። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ በሚገርም ሁኔታ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ነበር። ይህ የመንፈስ ቁጥጥር በአምላክነቱ አያስፈልገውም ነበር፥ ነገር ግን ፍጹም ሰው ስለሆነ ደግሞ ያስፈልገዋል። መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ በሚሠራበት ወቅት ኢየሱስ የሰዎች ትኩረት ወደ እርሱ እንዲሆን ወይም ሰዎች ክብርን ለእርሱ እንዲሰጡ አያደርግም ነበር። ይልቁኑ ክብርን ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ እንዲሰጡና ወደ እርሱ እንዳያተኩሩ ያደርግ ነበር። ለዚህ ነው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ እርሱ ሁልጊዜ የሚያደርገው የአብን ፈቃድ እንደሆነ የተናገረው። ኢየሱስ በምድር ላይ የነበረው ተቀዳሚ ዓላማ እግዚአብሔር አብን እንጂ እራሱን ማክበር አልነበረም። ስለዚህ የሚሠራቸው ሥራዎች ሁሉ እብ እንዲሠራቸው የሰጠው እንጂ የራሱ አልነበሩም (ዮሐ 8፡50፤ 17፡4)። 

4. መንፈስ ቅዱስ ለኢየሱስ የደስታው ምንጭ ነበር፡- የሉቃስ ወንጌል ትኩረት ኢየሱስ ያላሟቋረጥ እንዴት በመንፈስ ቅዱስ ይመራ እንደነበር መናገር ነው። አንድ ቀን ደቀ መዛሙርት ከወንጌል ስብከት ሥራቸው በመመላለ አጋንንት እንኳ እንዴት እንደተላቸው ለኢየሱስ ሲናገሩ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት እንዴት እንደተሞላ እንመለከታለን (ሉቃስ 10፡2)። የኢየሱስ ስሜቶችም እንኳ በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ነበሩ። 

5. መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ በኩል ያስተምር ነበር፡- በሐዋ. 1፡2 ላይ ሉቃስ፥ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርት ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠው ትምህርት በመንፈስ ቅዱስ በኩል የተከናወነ እንደነበር ይነግረናል። ይህ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከሰጣቸው በርካታ አገልግሎቶች አንዱ ለመሆኑ አንዳችም ጥርጥር የለም። 

6. መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ተአምራትን ያደርግ ዘንድ በኃይል አስታጥቆታል፡ ኢየሱስ አምላክ ስለሆነ በራሱ ብርታት ተአምራትን ማድረግ ይችል ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ ብዙ ጊዜ የእራሱን መለኮትነት በመገደብ እንደ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ላይ ይደገፍ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ተአምራትን በሚያደርግበት ጊዜ ማለትም ሰዎችን ሲፈውስ፥ አጋንንትን ሲያወጣና ሙታንን ሲያስነሣ የሚሠራው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነበር። (ማቴ 1፡28 ሉቃስ 4፡14-15፤ 18 ተመልከት)። ኢየሱስ ተአምራቱን ሁሉ የፈጸመው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካይነት ይሁን ወይም አንዳንዶቹን ተአምራት ለመሥራት የራሱን ኃይል ተጠቅሞ እንደሆን የሚለው እሳብ አከራካሪ ነው። ኢየሱስ በራሱ ኃይል እንደፈወሰ የተነገረባቸው በርካታ ጊዜያት አሉ (ማር. 5፡30፤ ሉቃስ 6፡19)። ነገር ግን እግዚአብሔር ማለት እካላት ቢኖሩትም አንድ የመሆኑን ጽንስ አሳብ ካስታወስን በኢየሱስ ሥራ የሥላሴ አካላት ሁሉም ተሳትፈዋል ማለት ነው። ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ሲናገር የሚሠራቸው ሥራዎች (ተአምራት) የአባቱ እንጂ የራሱ እንዳይደሉ የተናገረውም ለዚህ ነበር (ዮሐ 17፡4)። 

ጥያቄ፡- ሀ) መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት የሚኖረው ህልውና በኢየሱስ ሕይወት ከነበረው ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው? ለህ ዛሪ በእኛ ሕይወትለ የሚለየው እንዴት ነው? ሐ መንፈስ ቅዱስ ተመሳሳይ የሆኑ ነገርችን በሕይወታችሁ እንዴት እንዳደረገ ምሳሌ በመስጠት ዘርዝሩ። 

ኢየሱስ ፍጹም ሰው በመሆኑ አማኞች በፍጹምነት ሊከተሉት የሚገባቸውን የሕይወት ምሳሌ በመኖር አሳይቷል። በኢየሱስ ሕይወት የተመለከትናቸው በርካታ ነገሮች ዛሬ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ከሚሠራቸው ነገርች ጋር ተመሳሳይ ናቸው። የሚመራን፥ በኃይል የሚያስታጥቀን፥ ሊገለጽ የማይችል ደስታ የሚሰጠንና አስፈላጊ በሆነ ጊዘ በእኛ ውስጥ ተአምራትን የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው፡ እንድ ትልቅ ልዩነት ብቻ አለ። ይህም የመጠን ልዩነት ነው። በምድር ላይ በምንኖርበት ጊዜ በመንፈስ ብንወለድም እንኳ ኃጢአታዊ ተፈጥሮአችን አብርን ይኖራል። ስለዚህ መንፈሳዊ ተፈጥሮአችን በኃጢአታዊ ተፈጥሮአችን ላይ ጦርነትን ያውጃል (ገላ. 5፡16-18)። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ሙሉ ተቆጣጣሪ አይደለም ማለት ነው። በሌላ በኩል ቀን ኢየሱስ ኃጢአታዊ ተፈጥሮ አልነበረውም። እርሱ ፍጹም ንጹሕ ነበር። ስለዚህ መንፈስ ቅፋል ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረው መኖር የቻላ እርሱ ብቻ ነው። እርሱ ፍጹም ምሳሌያችን ነው። መንፈስ ቅዱስ በዚያ መጠን ሕይወታችንን ሊቆጣጠር ሳይችልም እንኳ ሰርትተን ክርስቶስን እስክንመሰል ድረስ እንድንቀጥልና በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር እንድንመላለስ የማበረታቻ ምክር ተሰጥተናል (ኤፈ 419 ተመልከት)። 

ጥያቄ፡- ዕብ 9፡1 ሮሜ 8፡ 1ኛ ጴጥ. 3፡18 አንብብ። በጥቅሶቹ እንደተገለጸው ለክርስቶስ ሕይወት የመንፈስ ቅዱስን ተሳትፎ የሚያሳዩ ሁለት ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? 

ሐ. በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ የመንፈስ ቅዱስ ተሳትፎ 

በኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት መንፈስ ቅዱስ ትልቅ ተሳትፎ አድርጓል። በተጨማሪ ቀን በኢየሱስ የመስቀል ሞት የተሳተፈ ይመስላል። በዕብ 9፡14 ላይ ኢየሱስ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ተጽፎልናል። በዚህ ጥቅስ ውስጥ የተመለከተው መንፈስ የኢየሱስ የራሱ መንፈስ ወይም መንፈስ ቅዱስ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በምድር ላይ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ ስለተሳተፈ ኢየሱስ እራሱን ፍጹም መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር አብ ባቀረበበት ሁኔታ መንፈስ ቅዱስ እንደረዳው ጎመን ትክክል ነገር ነው። ከመሰቀሉ በፊት በነበሩ በእዚያ ጨለማ ሰዓታት ኢየሱስ በታላቅ ኅዘን ውስጥ ነበር። ኅሆኑ እላከሞት እንኳ የበረታ ነበር (ማቴ. 26፡36-38)። በመስቀል ላይ በመሞት የሥጋ ስራን መቀበል ብቻ ሳይሆን የዓላምን ሁሉ ኃጢአት በመሸከም እግዚአብሔር አብ ዝም ሲለው ካሰቡ እንደ ሰው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ አጠገብ በመሆን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት የዘላላም መሥዋዕት አድርጐ እራሱን ያቀርብ ዘንድ እንደረቶው አያጠራጥርም። 

ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው እግዚአብሔር አብ እንደሆነ አአ ኢቶን ይናገራል (የሐዋ. 2፡32፤ ገላ. 1 ኤፈ ፡20)። ነገር ቀን ኢየሱስ እራሱን ከሞት እንደሚያስነግ ተናር ነበር ዮሐ 10፡17-18)። ይህም ሆኖ በኛ ጴጥ. 3፡18 መሠረት ደግሞ ኢየሱስን ከሞት በማስነሣት ሥራ መንፈስ ቅዱስ ተሳትፏል። 

በሦስት አካል የተገለጠውን አንድ አምላክ እናመልካለን። በፍጹም ስምምነት ይሠራሉ። አንተ የሠራው ማንኛውም ሥራ የሌሎቹም ሥራ ተደርጐ ሊቀርብ ይችላል። ስለዚህ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ በጥንቃቄ ስናጠና መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት ከመወለዱ ጀምሮ እስክ ሞቱና ትንሣኤው መካሪሉን እናረጋግጣለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) ዛሬ እንድከተላቸው ምሳሌ የሚሆኑን ኢየሱስ የሠራቸውን ተግባራት ወይም አደራረጉን ወይም ባሕርዩን ዘርዝር። መንፈስ ቅዱስ በእዚህ ሁሉ ተሳትል። ለ) መንፈስ ቅዱስ ለጌታ ኢየሱስ ያደረገውን በሕይወትህ እንዴት እንደሚሠራ አብራራ። ሐ) የሰለጠ ኢየሱስን ትመስል ንድ በተሻለ ሁኔታ እራስህን ለመንፈስ ቅዱስ የምታቀርብባቸው መንገዶች የትiች ናቸው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

One thought on “መንፈስ ቅዱስ በጌታ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት ውስጥ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.