መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንረዳበት ምንጭ

ላቱለፋዩ ጓደኛው ግርማ አዲስ የቪዲዮ ክር ሰጠው። ቪዲዮው የሚያሳየው ታላላቅ ተአምራትን እንደሚያደርግ ስለሚናገር አንድ ታዋቂ ሰባኪ ነበር። ቪዲዮው ከእነዚህ ተአምራት አብዛኛዎቹን ያሳያል። በትዕይንቱ መጨረሻ ላይ ሰባኪው እንዲህ ሲል ይደመጣል። «ተአምራትን ታደርጉ ዘንድ ይህ ኃይል እንዲኖራችሁ ብዙ ገንዘብ ላኩልኝ። መሐረቤን እልክላችሃለሁ። መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ይመጣና እኔ አሁን የምለማመደውንም ኃይል ይሰጣችኋል።» ተስፋዩ በጣም ተደሰተ። ስለዚህ ጥሪቶቹን ለሰውዬው ላከ። ከብዙ ወራት በኋላ መሐረቡ ደረሰው። ተስፋዬ የተሰጡትን ትእዛዛት በጥንቃቄ በመከተል መንፈስ ቅዱስን በአዲስ መንገድ እንዳገኘ አመነ። በቀጥታ ወደ ጐዳና ላይ በመውጣት አዲስ የተቀበለውን ኃይል ለመለማመድ ሞከረ። ወደ አንድ በሽተኛ ለማኝ በመመልከት «ተፈወስ» ብሎ ጮኸ። ነገር ግን ምንም አልተፈጸመም። ተአምራት አልተደረገም። ከዚያም በእግዚአብሔር ላይ እያዘነና በክርስትናው እየተጠራጠረ ወደ ቤቱ ተመለሰ። 

ጥያቄ፡- ክርስቲያኖች ይመላከቱት ዘንድ የሚፈልጓቸውን ተአምራትና ሌሎች አስደናቂ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ዘርዝር። እነዚህ ቪዲዮዎች የሚጠቅሙ ይመላሉሃል ወይስ የሚዱ? መልስህን አብራራ። 

እንደ ተስፋዬ ያሉ ክርስቲያኖች ብዙዎች ናቸው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ከመጽሐፍ ያነባሉ ወይም ቪዲዮ ይመለከታሉ፤ የሰሙትንም ነገር ወዲያውኑ ያምናሉ። እግዚአብሔር በቃሉ ከገለጸላቸው ነገሮች ውጭ ያሉትን ትምህርቶች መፈተንና መመርመር የእያንዳንዱ ክርስቲያን ኃላፊነት መሆኑን ይዘነጋሉ። ሙሉ በሙሉ ትክክል የሆነና ሊወድቅ የማይችል እውነት ያለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ክርስቲያኖች አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የሆነን ትምህርት ሲያስተምራቸው ባለመፈተናቸው ወደ ስሕተት የወደቁባቸውን ሁኔታዎች ግለጽ። ለ) በኢትዮጵያ ያሉ ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ትምህርቶች የሚያገኙባቸውን ምንጮች ዘርዝር። 

ስለ እግዚአብሔር እውቀትን የምናገኘው ከየት ነው? ስለ መንፈስ ቅዱስና ስለ ተግባሩ የሚገልጸውን እውቀት የምናገኘው ከየት ነው? ከሰብአዊ ችሎታችን አንጻር እውቀታችን እርግጠኛ መሆኑን የሚያሳየን ምንጭ ወይም ስፍራ የምናገኝበት ሁኔታ አለን? 

አንዳንድ ሰዎች እርግጠኛ እውነትን የምናገኝበት ስፍራ የለም ይላሉ። ስለ እውነት የተለያዩ መረዳቶች አሉ። ሰው እስካመናቸው ድረስ ሁሉም ተቀባይነት አላቸው ይላሉ። ስለዚህ ሙስሊሞች የሚያምኑት ለሙስሊም ትክክል ነው፤ ክርስቲያኖች የሚያምኑት ደግሞ ለክርስቲያን ትክክል ነው ይላሉ። እነዚህ ሰዎች እንደሚሉት አሳቦች፥ ፍልስፍናዎች፥ ሃይማኖቶችና ተግባራት ሁሉ ሊመዘኑ የሚችሉበት እንድ ፍጹም እውነት የለም። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህን ትምህርት ማመን ለእኛ አደገኛ የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ለ) ይህን የሚያምን ሰው አጋጥሞህ ያውቃልን? እንዲህ ዓይነቱ ሰው ምን እንደሚያምን አብራራ። 

እንደ ክርስቲያን ይህን ትምህርት በጥብቅ መቃወም አለብን። እውነት የሆነውን ካልሆነው ለመለየት የምንሄድበት ስፍራ አለን። በአሳቦች፥ በፍልስፍናዎች፥ በሃይማኖቶችና በተግባራት ሁሉ ላይ ሊፈርድ የሚችል ምንጭ አለን። እርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ነው። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ፡- መዝ (119፡9፥ 89+105፥ 33፤ ማቴ. 5፡7-18፤ 2ኛ ጢሞ 3፡16-17፤ 2ኛ ጴጥ 1፡20-2፤ ዕብ 4፡12። ሀ) እነዚህ ጥቅሶች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ስለሚናገረው ምን ያስተምሩናል? ለ) ይህ ሰዎች አዳዲስ ትምህርቶችን ይዘው ሊመጡ ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳያል? ትክክል መሆኑንና ያለመሆኑን በምን እናውቃለን?

እውነትን የምንመዝንበት ፍጹም የሆነ እውነተኛ ሚዛን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ እራሱ ያስተምረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ የሚሰጠው ምስክርነት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ፥ ስሕተት እንደሌለበት እና የሐሰት ትምህርትን ለማስተማር እንደማይቃጣ ነው። በዚህ የጥናት መጽሐፍ የምናጠናው መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ በመሥራት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የላፉት ሁሉ እግዚአብሔር ለሰዎች ሊያስተላልፈው የፈለገውን መልእክት ብቻ እንዲሆን አድርጓል። ርቀትን ለመለካት የምንጠቀምበት መለኪያ ሜትር እንደሆነ ሁሉ በምድር ላይ ያሉ ትምህርቶች ሁሉ የሚመዘኑበት መስፈርት መጽሐፍ ቅዱስ ነው። 

እውነት ሁሉ የሚዳኝበት መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነ ለመቀበል ብዙ ክርስቲያኖች ፈቃደኛ ቢሆኑም፥ ብዙ ክርስቲያኖች ደግሞ እምነታቸውን የሚመሠርቱት በዓል ለማተቻቸው፥ ወይም ከሌሎች ስሚሰሟቸውና በመሳሰሉት ሌሎች ምንጮች ላይ መሆኑ የሚያሳዝን ነገር ነው። ይህ ክርስቲያኖችና ቤተ ክርስቲያንን እጅግ አደገኛ የሆነ አቋም ላይ ይጥላቸዋል፤ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ለእምነታችን የመጨረሻው ባለሥልጣን አድርገን ካልተጠቀምንበት በፍጥነት ከስሕተት ላይ እንወድቃለን። ቀጥለን የምንመለከታቸው ነገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ሁሉ ሊያሳስቧቸው የሚገቡ ናቸው። 

1. በቤተ ክርስቲያን ከሚስፋፉት ትምህርቶች አብዛኛዎቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም። 

ጥያቄ፡- 2ኛ ጢሞ. 4፡1-5 አንብብ። ሀ) የመጨረሻዎቹ ዘመናት ባሕርያት ምን እንደሚመስሉ ግለጽ። ለ) እነዚህ ባሕርያት በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል ይዘወተራሉ? ሐ) የእግዚአብሔር ሰው ምን ማድረግ አለበት? 

በ2ኛ ጢሞ. 4፡1-5 ጳውሎስ፥ በመጨረሻው ዘመን ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የሕይወታቸው መመሪያ መሆኑን እንደማይቀበሉ ይነግሩናል። በዚህ ምትክ ሕይወታቸውን ስም ስት ነገሮች ላይ ይመሠርታሉ። በስሜቶቻቸው፥ ዓይኖቻቸው በሚያዩትና በትውፊታቸው። 

1. የስሜቶቻቸው መላኪያ (መመዘኛ)፡- የሰሙትና የሚያደርጉት ነገር መልካም እንደሆነ ከተሰማቸውና ሌሎችን የማይጐዳ ከሆነ ትክክለኛና ለማድረግ የተፈቀደ አድርገው ይቆጥሩታል። ለምሳሌ አንድ ሰው በቤተ ክርስቲያን መካከል ተነሥቶ ቢያንስና የለበሳቸውን ልብሶች በሙሉ አውጥቶ ቢጥል ይህን ለሚያደርገው ሰው መልካም ሊመስል ይችላል። ትክክል ይሁን ወይም ስሕተት የምናውቀው ግን በምንድን ነው? ትክክል ይሁን ወይም ስሕተት የሚወስነው የእርሱ ወይም የእርሷ ስሜት ነውን? አይደለም። ስማቶቻችን ሊዋሹ ይችላሉ። የአንድ ነገር ትክክለኛነት ወይም ትክክላኛ ያለመሆን ቀጥተኛ እውነተኛ መመዘኛዎች አይደሉም። ብዙ ወጣቶች በፍትወተ ሥጋ ኃጢአት የሚወድቁት ጊዜያዊ የሆነ አስደሳች ስሜት ስለሚሰማቸው ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መመዘኛነት በመተው ስሜታቸውን እንደ መመዘኛ ይቀበላሉ። ስለ መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያኖቻችን በዛሬው ጊዜ የሚሰጡ ትምህርቶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ከሚደረግ ጥረት የመነጩ ሳይሆን በሰዎች ላሜት ላይ የተመሠረቱ ናቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) የእግዚአብሔርን ቃል ለመከተል ከመፈለግ ሳይሆን በስሜቶቻቸው ላይ ብቻ በመመሥረት ሰዎች የሚያደርጓቸው ሌሎች ምሳሌዎችን ጥቀስ? ላ) እነዚህ ነገሮች በ2ኛ ጢሞ 4፡1-5 ሰዎች በመጨረሻ ዘመን ከሚኖራቸው ዝንባሌ ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው? 

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር ድርጊቶችን ያከናውን ዘንድ አእምሮን፥ ስሜትንና ሥጋዊ አካልን ፈጥሮላታል። እነዚህ ሦስቱም የሰው ክፍሎች መልካምና ሚዛናዊ ተደርገው ተፈጥረዋል። የእግዚአብሔር ዕቅድ አእምሮ ስሜትና ተግባራዊ ድርጊትን በበላይነት እንዲቆጣጠርና እንዲመራ ነበር። 

ሰይጣን ወደ አዳምና ሔዋን በመጣ ጊዜ ይህን ሥርዓት ቀየረው። ስሜት በአእምሮ ላይ የበላይ ሆኖ እንዲገዛና የተሳሳተ ድርጊት እንዲፈጠር አቀነባበረ። ሔዋን የተከለከላውን ፍሬ ስትመለከት ለመብላት መልካም እንደመሰላትና እግዚአብሔር እንዳትበላ እንደከለከላት ብታውቅም እንኳ እንደበላች አስታውስ። ስሜቶቿ አእምሮዋን አሸነፉና ውጠቱ ኃጢአት ሆነ። ሰይጣን የምንሠራቸውን ኃጢአቶች በሙሉ የሚያስፈጽመን ስሜቶቻችን አእምሮአችንን እንዲያሸንፉ በማድረግ ነው። ብዙ ጊዜ ኃጢአት የምንሠራው ትክክለኛ የሆነውን ነገር ባለማወቃችን ሳይሆን ላላሜቶቻችን በመሸነፍና ትክክለኛ ያልሆነውን ነገር በማድረግ ነው። ለዚህም ነው መጽሐፍ ቅዱስ አእምሮአችንን እንድንቆጣጠር፥ አእምሮአችንም ስሜቶቻችንን እንዲቆጣጠርና በአንድነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት ዘወትር የሚያሳስበን። አእምሮአችን፥ ስሜቶቻችንና ተግባራችን በተገቢው ሚዛን በሚሆኑበት ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ኑሮ ልንኖር እንችላለን። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፥ ኢሳይያስ 26፡3፤ ማር. 12፡30፤ ሮሜ 1፡28፡12፡2፤ 1ኛ ቆሮ. 14፡13-5 እያንዳንዱ ጥቅስ አእምሮአችንን በተመለከተ ምን ይላል? 

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ አእምሮአችንን በአግባብ ስለመጠቀም ይናገራል። ኢሳይያስ 26፡3 ሁኔታዎች አስቸጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ እንኳ በእግዚአብሔር ላይ እእምሮአችን በማሳረፍ ሰላምን ልናገኝ እንደምንችል ይናገራል። ማርቆስ 12፡30 እግዚአብሔርን በሚገባ ላመከተል በሙሉ አሳባችን አእምሮአችን) እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለብን ማለትም አስተሳሰባችን ለእርሱ መማረክ እንዳለበት ይናገራል። ሮሜ 1፡28 ወደ ተሳሳተ ድርጊት የሚመራ ኃጢአት እንዴት ከማይረባ አእምሮ እንደሚመጣ ያሳያል። ሮሜ 12፡2 ደግሞ እንደ ክርስቲያን ማደግ የሚመጣው አእምሮአችን ሲታደስ ብቻ እንደሆነ ይናገራል፤ 1ኛ ቆሮ. 14፡13-5 ደግሞ እግዚአብሔር በምናመልከው ጊዜ ስሜቶቻችንን (መንፈሳችንን) እንዳንጠቀም የማይቃወም ቢሆንም አእምሮእችን በመንፈሳችን ላይ ገዥ ሆኖ እግዚአብሔርን በመረዳት ማመስገናችን የላቀ ዋጋ እንዳለው ይነግረናል። 

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የምንመለከተው ሁኔታ ግን ስሜቶቻችን በመረዳታችን ላይ ገዥ መሆናቸውን እንድናምን ያደርገናል። አንዳንድ መዝሙሮችን እየደጋገምን ከ6 ደቂቃ በላይ የምንዘምረው የሰዎች ስሜት ከፍ እያለ እንዲሄድ ነው። ይህ አምልኮአችንን የበለጠ መንፈሳዊ እንደሚያደርገው እናስባለን። ይህ እውነት መሆኑን እጠራጠራለሁ። በምንዘምርበት ጊዜ አእምሮእችን ያለማቋረጥ ከስሜቶቻችን ጋር የማይሠራ ከሆነ፤ የምንዘምረው ነገር ምን እንደሆነ በእርግጥ ካላሰብን እግዚአብሔርን ማምለክ አቁመን ለሚቶቻችን በባዶ ሜዳ እየጋለቡ ናቸው ማለት ነው። ስሜቶቻችን መጥፎ ባይሆኑም እንኳ ከአእምሮአችን ጋር አብረው መሥራት አለባቸው። 

2. የዓይኖቻችንና የጀሮዎቻችን መለኪያዎች፤ የምናያቸው ወይም የምንሰማቸው ወይም ያየናቸውና የሰማናቸው የሚመስሉን ነገሮች፡ በእርግጥ አንድ ነገር ካየን ይህ ነገር ትክክለኛ ወይም ተገቢ ነውን? ለሌሎች የሚጸልይ ሰው ግንባራቸውን ይዞ ሲገፋቸውና ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ ብናይስ? ይህ መልካምና ከመንፈስ ቅዱስ የመጣ ነው ማለት ነውን? የአንድን ተግባር ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በሰብዓዊ ዓይኖቻችን የተመለከትናቸው ነገሮች ትክክለኛ መረጃ ናቸውን? በፍጹም አይደሉም! 

ሔዋን በዔድን ገነት የነበረውን ፍሬ ተመልክታ እንደ እግዚአብሔር አዋቂ እንደሚያደርጋት አሰበች። ነገር ግን ሞትና ጥፋት በሁሉም ላይ አመጣ። ዓይኖቻችን የአንድ ሕንፃ መሠረት ውኃ ልኩን እንደጠበቀ አድርገው ሊያዩ ይችሉ ይሆናል። በእርግጥ ግን አይደለም። ዓይኖቻችን ሊታለሉ የሚችሉባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። እንደዚሁም ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞላሁ ሲሉ በየቤተ ክርስቲያኖቻችን የምንመለከተው ወይም ሰቴሌቪዥንና በቪዲዮ የምናያቸውና የሚያስደንቁን ነገሮች ስላየናቸው ብቻ በእግዚአብሔር እይታ እውነት ወይም መልካም ናቸው ማለት አይቻልም። 

የአንድን ነገር ትክክለኛ መግለጫ የሚሰጠን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። ምን እንደተፈጸመ የትኛው ትክክል የትኛው ደግሞ ስሕተት እንደሆነ፣ የትኛው ከእግዚአብሔር የትኛው ደግሞ ከሰይጣን እንደሆነ ትክክለኛ መረዳት የሚሰጠን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። 

3. ብዙ ክርስቲያኖች እምነታቸውን የሚመሠርቱበት ሦስተኛው መለኪያ 

ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያልሆነ ትውፊት ወይም ልማዳዊ ተግባር ነው። ይህ ለእምነታቸው በስሜቶቻቸው ላይ ከሚደገፉት ተቃራኒ የሆነ ችግር ነው። ትውፊታዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያን ልምምዶች ላይ እምነታቸውን የመሠረቱ ሰዎች መልስ ፍለጋ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ አይሄዱም። ይልቁኑ ድርጊቶቹ ባለፉት ጊዜያት ወደ ተፈጸሙባቸው መንገዶች ይመለከታሉ። ነገሮች ባለፉት ጊዜያት የተፈጸሙባቸው መንገዶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እኩል ሥልጣን እንዳላቸው በማመን በባሕላዊ ልማድ ምክንያት ለውጥን አይቀበሉም። 

ጥያቄ፡- ማር. 7፡1-13 አንብብ። ሀ) ኢየሱስ ፈሪሳውያንን ምን ያደርጋሉ ብሎ ተቃወማቸው? ለ) በዛሬይቱ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ዓይነቱን አደጋ የምንመለከተው እንዴት ነው? 

ሁላችንም በኢየሱስና በፈሪሳውያን መካከል የነበረውን ጠላትነት እናውቃለን። ፈሪሳውያን መንፈሳዊ ነን የሚሉ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኙ የሚያስቡ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ። ነገር ግን እምነታቸው የተመሠረተው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሳይሆን በትውፊታቸው ላይ ነበር። በዚህም የክርስቶስ ዋና ጠላቶች ሆኑ። በዚህ ክፍል ስለ ፈሪሳውያን የተገለጡትን ሦስት ነገሮች ተመልከት። 

1. የእግዚአብሔርን ቃል እንዳይተላለፉ ይረዳናል ብለው ያሰቧቸውን ነገሮች በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጨመሩ። ከመልካም ልባዊ አሳብ በመነሣት እግዚአብሔር በተናገረው ላይ ሕግጋትን ጨመሩ። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን በአምልኮ ጊዜያቸው የመንጻት ሥርዓት ማካሄድ እንዳለባቸው ተናግሮእቸው ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ንጹሕ የሆኑትንና ያልሆኑትን እልዘረዘረ ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘታቸውን እርግጠኛ ለመሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ሕግጋት ላይ ጨመሩ። የቤተ ክርስቲያን ሕግጋትና ደንቦች አብዛኛዎቹ የሚጀምሩት በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ለመሆን ከመፈለግ የተነሣ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሕግጋትና ደንቦች የእግዚአብሔር ቃል አይደሉም። ወይም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሊስተካከሉ አይችሉም። 

2. ትምህርታቸው ወይም ትእዛዞቻቸው እንደ እግዚአብሔር ቃል መጠበቅ እንዳለበት ያስቡ ነበር። የሽማግሌዎቻችን ትምህርቶች መልካም ሊሆኑ ይችላሉ። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚተካከሉበት መንገድ ግን የለም። ስለዚህ ትውፊቶች ቢታዘዙአቸውም ባይታዘዙአቸውም መንፈሳዊ ጉዳት የማያስከትሉ ሆነው ለአመለካከት ልዩነቶች ክፍት ነበሩ። ፈሪሳውያን ቀን ሕጐቻቸውን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል በማድረግ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ይጨምሩ፥ አንዳንድ ጊዜም ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ይቃረኑ ነበር። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ልምምዶቻችንን ወይም ባሕሎቻችንን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እኩል እንዳናደርጋቸው እጅግ መጠንቀቅ አለብን። 

3. የእግዚአብሔር ዋና ትኩረቱ በሕግጋት ውጫዊ ሁኔታ ላይ እንደ ሆነና ከልባቸው ዝንባሌ ጋር ጉዳይ እንደሌለው ያስቡ ነበር። «የሕግን ፊደል» እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ውጫዊ ትእዛዛት እስከታዘዙ ድረስ ልባቸው ጠንካራና መራራ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሁኔታ እንደሚኖሩ ያስቡ ነበር። ለእግዚአብሔር መታዘዝ በመጀመሪያ ከልብ በትክክለኛ ዝንባሌዎች የሚጀምር፥ ከዚያም ወደ ትክክለኛ ተግባር የሚተረጐም መሆኑን አልተገነዘቡም ነበር። 

ውጫዊ ተግባራት ከውስጣዊ ዝንባሌዎች ሰላይ ሆነው የመታየታቸው ነገር በሁሉም ዘመናት የነበረ የቤተክርስቲያን ችግር ነው። ከዓለም የተለየን እንደሆንን የሚያመለክቱ ውዳዊ ድርጊቶች ክፈጸምን፥ ሰይጣን መልካም ወይም መንፈሳዊ እንደሆንን እንድናስብ ያደርገናል። የትኛውም ነገር ሊሆን ይችላል። አለባበስ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የተወሰነ አለባበስ ካዘወተርን መንፈሳዊ እንደምንሆን ያስተምራሉ። ሌሎች በልሳን ከተናገርን መንፈሳዊ እንደምንሆን ያስተምራሉ። እግዚአብሔር ለውጫዊ ተግባራችን የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው፥ ስለ ልባችን ግን በጣም ይገደዋል። ልባችን ትክክል ከሆነ ውጫዊ ተግባራችንም ትክክል ይሆናል። 

ቆላስይስ 2፡8 «እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ» በማለት አስጠንቅቆናል። ልምምዶቻችንን ከዚህ ቀደም በተማርናቸው ነገሮች ላይ ከመሠረትን ውስጣዊ ዓላማችን መልካም ቢሆንም እንኳ ያለማቋረጥ በእግዚአብሔር ቃል ካልፈተንናቸው በስተቀር እደገኛ መለኪያዎች ናቸው፡፡ አንድ የአምልኮ መንገድ ቀደምት አባቶቻችን እኛን ያስተማሩበትን መንገድ የተከተለ ባለመሆኑ ብቻ የተሳሳተ ነው ካልን ሕጐቻችን በእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን ሥር ያሉ መሆናቸው ቀርቶ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚተካከሉ እናደርጋቸዋለን። 

ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ በምናጠናበት ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማወቅ የሚገባንን ጉዳይ ለመዳኘት ዋና መመዘኛችን አድርገን የምንጠቀምበ የእግዚአብሔር ሕያው ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ነው። በስሜት ላያ በመንተራስ ከሰዎች ጋር ክርክር አንገጥምም። ሰዎች በቪዲዮ እየን ወይም በመልእክት ሰማን በሚሉት ነገር ላይ እንሟገትም። ስለ መንፈስ ቅዱስ ጉዳይ በምናስተምርበት ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የትምህርታችን ምንጭ አድርገንም አንጠቀምም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ ማን መሆኑን ለመረዳት ባለን ጽኑ ፍላጐት መጽሐፍ ቅዱስን ዋና መመዘኛችን አድርገን እንጠቀማለን። 

ጳውሎስ የመጨረሻዎቹ ቀናት ሰዎች ባሕርይ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሳይሆን ለስሜቶቻቸው ደስ የሚያሰኙእቶውን ነገሮች በመስማት ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን በመንገር ጢሞቴዎስን ካስጠነቀቀው በኋላ ሙሉ ለሙሉ እራሱን ለእግዚአብሔር ቃል እንዲሰጥ አዝዞታል። የእግዚአብሔርን ቃል ላግል መመሪያው አድርጐ እንዲጠቀምበትና ያለማቋረጥ ለሌሎችም እንዲያስተምረው አዘዘው። ወንድሞቼና እህቶቼ እምነቶቻችሁን በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱላ ና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብቻ እንድትመሠርቱ እለምናችኋለሁ። አንድ ነገር እውነት መሆኑን ወይም ያለመሆኑን የምንለካበት እውነተኛውና ትክክለኛው መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው። በቴሌቪዥን የምናየው ወይም ሰመጽሐፍ የምናነበው ወይም ከሰባኪ የምንሰማው ነገር በእግዚአብሔር ቃል በቀጥታ ካልተደገፈ በስተቀር እውነት ሊሆን እንደማይችል ልናምን ይገባል። ደግሞም አመለካከታችን ብዙ ጊዜ ከዓውደ ንባቡ ተነጥሎ በወጣ አንድ ጥቅስ ብቻ የተደገፈ ያለመሆኑንም ማረጋገጥ አለብን። በመጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ክፍሎችም በሚገኙ ሰፊ ትምህርቶች የተደገፈ መሆን አለበት። ለዚህ ነው እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ላይ ትኩረት ማድረግ ያለብን። መልካም በሚመስሉ አሳቦች ወይም ዓይንን በሚስብ ነገር እንዳንወሰድ የሚጠብቀን የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ብቻ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከቤተ ክርስቲያንህ ወይም ከሌላ ቤተ ክርስቲያን ቢሆንም በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ ያልተመሠረቱ ትምህርቶችን ምሳሌ አቅርብ። ለ) በአሁኖቹ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያን ክርስቲያኖች እንዴት በሦስቱም መመዘኛዎች እምነታቸውን እንደሚመሠርቱ ምሳሌዎችን ጥቀስ። 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.