ሥነ መለኮት ምንድን ነው?

በዚህ የትመማ መጽሐፍ የመንፈስ ቅዱስን ሥነ መለኮት እናጠናለን። ሥነ መለኮትን ስለ ማጥናት ስንነጋገር ስለ ሁለት ነገሮች መናገራችን ነው። 

አንደኛ፥ ስለ አንድ ርእሰ ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ እውነቶችን በሙሉ በአንድነት ለማሰባሰብ መፈለጋችንን ያመለክታል። መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እውነተችን (ርእሰ-ጉዳዮችን) በየመስካቸው ከፋፍሎ በሚያስቀምጥ መንገድ አይደለም። ይልቁንም መጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ ትረካዎችን ደብዳቤዎችን የያዘ ሲሆን እነዚህም እግዚአብሔር ምን እንድናውቅ እንደሚፈልግ ያስተምሩናል። በእያንዳንዱ ትረካ ወይም ደብዳቤ ውስጥ በርካታ እውነቶች ወይም ርእሰ ጉዳዮች ተጠቅሰዋል። ስለ እግዚአብሔር፥ ስለ ድነት (ድነት (ደኅንነት)) ወይም ስለ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እውነቶች በሙሉ በአንድ ስፍራ እጢቃልሉ የያዘ ክፍል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ስለሆነም፥ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን እውነቶች በአንድነት በማድረግ በሥርዓት እናጠናቸዋለን ማለታችን ነው። 

ሁለተኛ፥ ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን እንዴት እንደምንረጻ እንመለከታለን ማለታችን ነው። የሥነ መለኮት ትምህርትን የመረዳታችን መጠን ሁልጊዜ ውሱን ነው። መረዳቶቻችንን ሁልጊዜ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ያነሱ አድርገን ልንመለከት ይገባል። ሥልጣን ያለው መጽሐፍ ቅዱስ እንጂ የእኛ መረዳት አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን በሙላት በትክክል የመረዳት ችሎታ ማናችንም የለንም። እውነትን የማወቃችን ችሉታ ውስን የሆነው በባሕላዊ መረዳሞቻችን፥ በማንነታችን ወይም በቤተ ክርስቲያን ልማዳችን እንኳ ተጽእኖ ስለሚደርስበት ነው። የመንፈስ ቅዱስን ሥነ መለኮት እናጠናለን ስንል የእግዚአብሔር ቃል ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምረን ያለንን መረጻት ሥርዓት ባለው የአጠናን ዘዴ እንመለከተዋለን ማለታችን ነው። 

ስለ እግዚአብሔርና ስለ ቃሉ ያለን መረዳት ውሱንና ከፊል እንደሆነ ሁልጊዜ መዘንጋት የለብንም። ቢሆንም እንኳ መረዳታችንን ለማሳደግ የእግዚአብሔርን ቃል ያለማቋረጥ ማጥናት ኃላፊነታችን ነው። ይሁንና፥ ከእኛ በተለየ ሁኔታ እውነትን ከሚረዱ ሌሎች ክርስቲያኖች የአመለካከት አቅጣጫ ሆነን ለማየትም ጥረት ማድረግ ይገባናል። በዚህ የጥናት መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር እንመለከታለን። በተጨማሪ ሌሎች ክርስቲያኖች በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸውን የተለየ አቋም በመመልከት ያንን አቋም ለምን እንደምንቀበል ወይም እንደማንቀበልም እንገልጻለን። ይህንን የምናደርገው በፍቅርና በዚህ ጉዳይ ላይ ለሁሉም ነገር መልስ እንደ ሌለን በማመንም ጭምር ነው። ትልቁ ፍላህታችን በአንድነት ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመመልከት «መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?» የሚለውን ጥያቄ እንድናነሣ ነው። 

ጥያቄ፡- እንደ መንፈስ ቅዱስ ያሉ ጉዳዮችን ማጥናት አስፈላጊ ነው ብለህ የምታስበው ለምንድን ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.