ስለ መንፈስ ቅዱስ ለምን እናጠናለን?

ጥያቄ፡- ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ማጥናታቸው አስፈላጊ እንደሆነ የምታስበው ለምንድን ነው? 

ዛሬ ዓለማችንን ብንመለከት ከብዙ ችግሮች ጋር በሚታገል ዓላም እንዳለን እንገነዘባለን። ከእነዚህ ችግሮች ጥቂቶቹ ጦርነቶች፥ ረሃብ፥ የዘር ልዩነት ውጥረትና ድህነት ናቸው። ከፍቅሩ የተነሣ የሰው ልጆች እነዚህን ችግሮች እንዲያሽንፉ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማድረግ እግዚአብሔር ጽኑ አቋም አላው። ይህንንም በሁለት መንገዶች ያደርጋል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ላሉ ችግሮች ሁሉ መነሻ ለሆነው የሰው ኃጢአተኛነት ዴስ ቅዱስ መንፈስ ቅዱፅዚአብሔርጽታት መፍትሔ ለመስጠት ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ላከው። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን ሰጥቶአል። ይህ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ተቀዳሚ ስጦታ ነው። (2ኛ ቆር. 9፡5) ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞት የኃጢአትን ዋጋ ከፍሎ የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር የሚመጡበትንና ኅብረት የሚፈጥሩበትን መንገድ ከፍቶአል። 

ቀጥሎ ደግሞ እግዚአብሔር መንፈሱን በመላክ በሕይወታችን ኃጢአት እንዳይቆጣጠረን ድል የምንነሳበትን ኃይል ሰጥቶናል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው ሁለተኛው ታላቅ ስጦታ መንፈስ ቅዱስ ነው። ኃጢአትን ድል ይነሣ ዘንድ ለመርዳት መንፈስ ቅዱስ ለሰዎች ተሰጠ። መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን እንድንመስል ያደርገናል። የተሰጠን መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን በሕይወታችን ድል እንድንነሣ ብቻ ሳይሆን፥ በዚህ ምድር ወኪሎቹ ለመሆን ኢየሱስን እንድናገለግለው ያግዘናል። 

ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጣቸውን የድነት (ድነት (ደኅንነት)) ስጦታ እንደማይጠቀሙበት ሁሉ ብዙ ክርስቲያኖች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ በሕይወታቸው አይጠቀሙበትም። በዚህም ምክንያት ያለማቋረጥ ከኃጢአት ጋር ይታገላሉ። ወይም ከመንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ስጦታዎች በአንዱ ላይ ብቻ በማተኮር ወደ ስሕተት ይወድቃሉ። ባለድል ሕይወት እንድንኖር በባሕርያችንም ሆነ በአገልግሎታችን እግዚአብሔር እንደሚፈልግብን እንድንሆን ከተፈለገ በርካታ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ የአገልግሎት ስጦታዎችን በሕይወታችን ልናውቅና ልንላማመድ ይገባናል። 

ስለ መንፈስ ቅዱስ የምናጠናባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። ከምክንያቶቹ ጥቂቶቹ ቀጥሎ ተጠቅሰዋል። 

1. የክርስቲያን ሕይወት ተቀዳሚ አላማ እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከሥላሴ አካላዊ ሕልውናዎች አንዱ ነው። ስለዚህ ልናውቀው ይገባል። 

በዘመናት ሁሉ ክርስቲያኖች እውነተኛው አምላክ እራሱን የገለጠው በቅድሚያ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሆነ አጥብቀው ተናግረዋል። እውነት ምን እንደሆነ በተለይ እውነተኛው አምላክ ማን እንደሆነ የሚገልጥ የተሟላ ትክክለኛ፥ ስሕተት የሌለበት መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን ነው። ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ካጠኑ በኋላ እግዚአብሔር በሦስት አካላዊ ሕልውና የተገለጠ ማለትም እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንደሆነ ያምናሉ። 

የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ጭብጥ ስው ስላመፀና ኃጢአትን ስላደረገ ከእግዚአብሔር መለየቱን መግለጽ ነው። እግዚአብሔር ግን በፍቅርና ስምሕረት ከሰው ልጅ ጋር ኅብረት ለማድረግ ያለማቋረጥ ጥረት ያደርጋል። በምድር ላይ ያሉ የቅርብ ጓደኞቻችንን እንደምናውቃቸው ሁሉ እግዚአብሔር እንድናውቀው ይፈልጋል። እንደዚሁም እግዚአብሔር መንፈስ ውቅርፅ ጓደኞታች ያለማቋረጥ ጥረት በፍቅርና ቅዱስ እንድናውቀውና በዕለታዊ ሕይወታችን እርሱን እንድንለማመደው ይፈልጋል። 

ጥያቄ፡– ኤፌሶን 1፡21 አንብብ። ሀ) ጳውሎስ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሆነ ነው የሚጸልየው? ለ) ክርስቲያን ከሆንክ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ፥ ከእግዚአብሔር ወልድና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ያለህ ቀንኙነት እንዴት እንደተለወጠ ግለጽ። 

2. ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለው ግንኙነት ጥልቀት ከሌለው እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ ለመኖር አይችልም። 

እግዚአብሔርን ለማወቅ በምናደርገው ነገር ሁሉ እርሱን በመታዘዝ ሕይወት መመላላስ ይጠበቅብናል (ዮሐንስ 14፡2)። መንፈስ ቅዱስን እንዴት ማዳመጥ እንደሚገባን ካልተማርን በስተቀር የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ስለማናውቅ እርሱን ደስ ለማሰኘት አንችልም። ከኃጢአት ተለይተን በቅድስና አንኖርም። ኃጢአትን ለማሸነፍ ወይም በድፍረት ለመመስከር ወይም በቤተ ክርስቲያን እንደሚገባ ለማገልገል ኃይል አናገኝም። 

3. መንፈስ ቅዱስ በሚናገርበት ጊዜ እንዴት ልናደምጠው እንደምንችል ካላወቅን በእግዚአብሔር ድምጽና በሰይጣን ድምጽ መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ አንችልም። 

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳን ሰይጣን ብዙ ጊዜ የብርሃን መልአክ መስሎ ወደ ሰዎች ይመጣል (2ኛ ቆሮ. 11፡14 ተመልከት)። ይህም ማላት ወደ እኛ የሚመጣው መልካም መስሎ ነው ማለት ነው። እውነታው ሲታይ ግን የሚያደርገው ወይም የሚያስመስልበት ነገር የክፋትና የጥሩት ነው። ሰይጣን ውሸት የሆነውን እንድናምን ያለማቋረጥ ይሞክራል። እግዚአብሔር ግን የእውነት አምላክ ስለሆነ እውነትን እንድናውቅ ይፈልጋል። ትክክል የሆነውን ነገር ካልሆነው እንዴት ለመለየት እንችላለን? የሰይጣን ድምፁ የቱ እንደሆነና የእግዚአብሔር ድምፁ ደግሞ የቱ እንደሆነ ካላወቅን፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በመጠቀም መንገዱን እንዴት እንደሚያሳየን ካላወቅን ትክክለኛ የሆነውን ነገር ካልሆነው ለይተን ለማወቅ አንችልም (ዮሐንስ 10፡14-16)። መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚናገረን ካልተረዳን በስተቀር በሕይወታችን ሚዛናዊነት እናጣና ወደ ስሕተት እንወድቃለን። (ማስታወሻ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ የሚናገርበት ተቀዳሚ መንገድ በእግዚአብሔር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ነው ስብከቶችን መስማትና፤ የቪዲዮ ዝግጅቶችን መመልከት ወዘተ… ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና ማጥናት አስፈላጊ የሚሆነው።) 5ኛ ጥያቄ፡- ስለ መንፈስ ቅዱስ ለማጥናት ምክንያት የሆኑት ከላይ የተመለከትናቸው እነዚህ ሁለት ነጥቦች በዚህ ዘመን ላለችው ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጉበትን መንገዶች ግለጽ። 

4. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ነገር ካላወቅን በስተቀር በመሠረታዊ የክርስትና እምነት ትምህርታችን ስሕተት ላይ እንወድቃለን። 

አብያተ ክርስቲያኖቻችን የተሞሉት በደካማና ሁልጊዜ በሚታገሉ ክርስቲያኖች ነው። ሚዛን-ለቀቅ በሆኑ አስተማሪዎች የሚዛመቱ ወይም በቪዲዮዎች የሚታዩ እንግዳ ትምህርቶች እንደ ብርቱ አውሎ ነፋስ ምድራችንን እያናወጡት ሲሆን፥ ከዚህም የተነሣ ብዙዎች በተለያዩ ስህተቶች ወስጥ የመግባት እዴጋ አንዣቦባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ማወቅ ያለብንና መንፈስ ቅዱስን ለመለማመድ፡ በሕይወታችን በሚከሰት ኃጢአት ላይ ያለውን ኃይሉን ለመገንዘብ፡ እንዲሁም ወደ እውነት ሁሉ ሊመራን ለማድመጥ እንድንችል ክእርሱ ጋር ሥር የሰደደ ኅብረት ማድረግ የሚገባን ለዚህ ነው (ዮሐንስ 14፡25-26)። 

5. በሕይወታቸው የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ባለመለማመዳቸው ምክንያት በመንፈሳዊ ሞት አደጋ ላይ ያሉ ክርስቲያኖች በርካታ ናቸው። 

ክርስትና በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ለብዙ ሺህ ዓመታት በኢትዮጵያ ኖሯል። በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት እንኳ መንፈስ ቅዱስ በደቡብ መሥራት ከጀመረና በርካታ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ካመጣ 70 ዓመታት አልፈዋል። አንድ ትውልድ እልፎ ሌላ ትውልድ ተተክቷል። እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ላሉ ክርስቲያኖች ቶርነቱን ስላላጓደለ፥ በስደቱ ምክንያትም ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ የመሞቷ አዝማሚያ ተገትቷል። በአንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ግን የመንፈስ ኃይል በመቀነስ ላይ ይመስላል። ሰዎች አሁን ካሉበት መንፈሳዊ ሁኔታ ይልቅ በትውፊታቸውና በቀድሞ ታላቅ ታሪካቸው ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ኃጢአት በገፍ ነው። የአምልኮ መልክ ተላብሳው የመንፈስ ቅዱስ እውነታ ግን የሌላቸው ብዙዎች ናቸው። (2ኛ ጢሞ. 3፡5 ተመልከት)። የመንፈስ ቅዱስን ኃይል እንደገና እንደ አዲስ ካልተለማመድንና ቅድስና ስሜት እንደገና ካልተሞላን እንደ መሳፍንት ዘመን የአባቶቻቸውን አምላክ የማያውቅ ሌላ ትውልድ የሚነሣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም (መሳፍንት 2፡10-11)። እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ እሳትን በብዙዎች ሕይወት እንደገና የሚያቀጣጥልበት እንዲሆን ስለ መንፈስ ቅዱስ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስን አውቀን ኃይሉም በሕይወታችን እንዲረጋገጥ እሻለሁ። 

ጥያቄ፡- የመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንዳንድ ጊዜ በሕይወትህም ሆነ በቤተ ህክርስቲያን ሲቀንስ እንዴት እንዳየህ ግለጽ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.