በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 3-8 )

ጥያቄ፡- የሐዋ. 4፡5-13፤ 28-31፤ 5፡1-12፤ 29-32፤ 6፡1-10፤ 7፡51፤ 8፡1፡1-25፤ 26-29፤ 39-40 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስና ከእያንዳንዱ ክርስቲያን ጋር ስላለው ንኙነት የተጠቀሱትን የተላያዩ እውነቶች ዘርዝር። 

ሀ. መንፈስ ቅዱስ በሌሎች ፊት በግልጽና በድፍረት ለመናገር የሚያስችል ኃይልና ችሎታን ሰጠ፡- በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በተደጋጋሚ መንፈስ ቅዱስን ስለመሞላት የተጠቀሱ ክፍሎችን ስንመለከት ከተአምራት፥ በልሳናት ከመናገር ወይም ከመስበክ ጋር የተያያዙ አለመሆናቸውን ልብ ማለት መልካም ነው። ይልቁኑ በመንግሥታት መሪዎች ፊት ቆመው መልስ በሚሰጡበት ወቅት ኢየሱስ አስቀድሞ ስላ መንፈስ ቅዱስ እንደተናገረው ኃይል እንደሰጣቸው እንመለከታለን (በማቴ. 10፡17-20)። ደቀ መዛሙርት ተቃውሞን የሚቋቋሙበትንና ወንጌልን በግልጽነት የሚሰብኩበትን ድፍረት የሰጣቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። ደቀ መዛሙርት በዚህ መልክ በሚገባ ወንጌልን ይናገሩ በነበሩበት ጊዜ የሕዝብ መሪዎች ከኢየሱስ ጋር የነበሩ መሆናቸውን እንዳወቁ እንመለከታለን የሐዋ. 4፡13)። ቆይተው ደቀ መዛሙርት የጸለዩት ተአምራትን እንዲያደርጉ ሳይሆን ወንጌልን በፍጹም ግልጽነት እንዲናገሩ ነበር። እግዚአብሔር የጸሎታቸውን መልስ ሰጠ። የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ «በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።» የዚህ ሙላት ውጤት ምን ነበር? «የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥነት መናገራቸው ነበር።» (የሐዋ. 4፡31)። እስጢፋኖስ በድንጋይ በተወገረ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በግልጥ እንዲናገር ከማስቻሉም ሌላ ወደ ሰማይ በማተኮር ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመለከት አድርጎት ነበር። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ ደቀ መዛሙርት ታላላቅ ተአምራትን እንዲያደርጉ አስቻላቸው፡= በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ሰዎችን መፈወስን፥ አጋንንትን ማስወጣትን የመሳሰሉ ተአምራቶችን በተደጋጋሚ ማድረጋቸውን እንመለከታለን። እነዚህ ተአምራት ስደቀ መዛሙርት ሕይወት መንፈስ ቅዱስ የመኖሩ ቀጥተኛ ምልክት ሆነው የቀረቡበት ጊዜ ግን ፈጽሞ የለም። በመንፈስ ቅዱስ የመሞላት ውጤት ተደርገውም አልቀረቡም። ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና አንዳንድ ክርስቲያኖችን ወንጌልን በልጽነት እንዲሰበኩ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የመልእክታቸውን እውነተኛነትና ሥልጣን ለማረጋገጥ ተአምራትን እንዲያደርጉ ችሎታን እንደሰጣቸው መገመት እንችላለን። ተአምራትን የማድረግና ወንጌልን የመስበክ ሥራ ብዙ ጊዜ ተቆራኝተው የሚቀርቡ መሆናቸው የሚያስገርም ነው። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ትኩረት የወንጌል መስበክ ነው። ተአምራትን ማድረግ ተቀዳሚ የአገልግሎት ዓላማው ሆኖ የቀረበበት ስፍራ ፈጽሞ የለም። ደቀ መዛሙርት ያለ ወንጌል ስብከት ተአምራትን ላለማድረጋቸው የተጻፈ አንድም ስፍራ አናነብም። ተአምራትን ሳያደርጉ ወንጌል ስለመሰበካቸው ግን እናነባለን። ይህ የሚያመለክተን የደቀ መዛሙርት ተቀዳሚ ዓላማዎች የእግዚአብሔርን ቃል መስበክ እንጂ ተአምራትን ማድረግ እንዳልነበረ ነው። በተጨማሪ የ መዛሙርት ተአምራትን ያደረጉት በቅድሚያ ለክርስቲያኖች ጥቅም እንደነበረ አናነብም። ሐዋርያት ትኩረታቸው ፈውስ ላይ አልነበረም። ይልቁኑ ውላ ሆነ አጋንንትን የማውጣት ተግባር ያተኮረው በቅድሚያ ሰማያምኑ ሰዎች ላይ ነበር። «ሕዝቡም የፊልጶስን ቃል በሰሙ ጊዜ ያደርጋት የነበረውን ምልክት ባዩ ጊዜ፥ የተናገረውን በአንድ ልብ እደመጡ» ተብሎ ተጽፎአ ( የሐዋ. 8፡6)። በኋላም የሚቀጥለውን ቃል እናገኛለን። «ምልክትና ድንቅ በእጃቸው ይደረግ ዘንድ እየሰጠ ለጸጋው ቃል ስለ መሰከረው ለለ ጌታ ገልጠው እየተናገሩ ረጅም ወራት ተቀመጡ።» (የሐዋ. 14፡3)። ተአምራትን የማድረግ ሥራ እንደ ሐዋርያት ባሉ የተወሰኑ ክርስቲያኖችና እንል እስጢፋኖስ ባሉ ስጦታ በነበራቸው ሌሎች ጥቂት የቤተ ክርስቲያን መሪ የተከናወነ ይመስላል። ለሁሉም ክርስቲያኖች የሚሰጥ ስጦታ አልነበረም፡፡ 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን በትክክል እንሩ አስችሎአቸዋል (የሐዋ. 1፡6)። የክርስቲያኖች ቁጥር ሐዋርያት በረ ሊመሯቸው ወደማይችሉበት ደረጃ ሲደርስ ለሚነሡት አንዳንድ ችግሮች መፍትሔ መስጠት እንዲቻል ሌሎች መሪዎች ተመረጡ። መመረጥ የነበረባቸው እንዴት ነበር? ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰዎች እንዲመርጡ ለደቀ መዛሙርት ነገሩአቸው። የተመረጡት ሰባት መሪዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳላቸው በሕይወታቸው ያረጋገጡ ነበሩ። ይህ በሕይወታቸው የተረጋገጠው እንዴት እንደነበር አልተጻፈም። ነገር ግን ሕዝቡ ልዩነቱን ስለሚያውቁ ለመመስከር ችለው ነበር። መንፈስ ቅዱስ ከሰባቱ ጋር እንደነበር እና የእዚአብሐርን ሕዝብ ለመምራት ጥበብ እንደነበራቸው ያውቁ ነበር። 

መ. ሰዎች መንፈስ ቅዱስን ሊዋሹት፥ ሊፈታተኑትና ሊቃወሙት ይችላሉ ( የሐዋ. 5፡1-11)። ይህ መንፈስ ቅዱስ ዝም ብሎ ኃይል ብቻ እንዳይደለ ነገር የን እካላዊ ህልውና ያላውና ከሰዎች ጋር ሕያው የሆነ ቀንኙነት የሚያደርግ መሆኑን ያመለክታል። መንፈስ ቅዱስ፥ ለፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እንዲያነጋግር ግልጽ የሆነ ትእዛዝ ሰጥቶታል (የሐዋ. 8፡29)። 

ሠ. መንፈስ ቅዱስ ለሰማርያ አማኞች በሐዋርያት እጅ መጣን ተሰጠ። (ወደፊት በምናጠናው ትምህርት ስለዚህ ጉዳይ በጥልቀት እንመለከታለን። የሐዋ. 8፡14-17) 

ጥያቄ፡- ሀ) ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ከእነዚህ አንዳንዶቹ ወይም ሁሉም የመንፈስ ቅዱስ እገልግሎቶች አስፈላጊ የሆኑት በምን መንገድ ነው? ለ) መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያንህ ተመሳሳይ ነገሮች ያደረበትን ጊዜ ግለጽ።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.