በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 9-28)

ጥያቄ፡- የሐዋ 9፡5-22፤ 27-28፤ 31፤ 10፡1-48፤ 11፡2-18፣ 22-24፤ 13፡1-3፣ 6-12፣ 52፤ 15፡6-11፣ 27-29፤ 16፡6-10፤ 19፡1-7፤ 20፡22-24፣ 28፤ 21፡4፣ 11 አንብብ። በእነዚህ ጥቅሶች የሚገኙትን የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ እጎልሎች ዘርዝር። 

ሀ. ጳውሎላ በዳነበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት (የሐዋ. 9)። እግዚአብሔር ጳውሎስን በደማስቆ መንገድ እንዴት እንደተገናኘው የሚናገረውን ታሪክ ሁላችንም እናውቀዋለን። እግዚአብሔር ሐናንያ የተባለን ሰው ጳውሎስ በኢየሱስ ማመኑን እንዲያረጋግጥ ነገረው። ሐናንያ በጳውሎስ ላይ እጁን በመጣን ይህን አጸና። ሐናንያ በጳውሎስ ላይ እጁን በማነ ጊዜ ማየት መቻል ብቻ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስም ተሞላ። ይህ ሙላት በምን እንደተረጋገጠ አልተገለጠልንም። የምንመለከተው ነገር ወዲያውኑ ጳውሎስ መጀመሪያ በደማስቆ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ስለ ኢየሱስ በድፍረት የሚመሰክር ሰው ሆነ። ዛሬ ሰዎች ብዙ ጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጋር የሚያያይዟቸውን በልሳናት መናገርንና የተአምራትን ጉዳይ እዚህ ላይ አናይም። 

ለ. ከታላቁ ልደት በኋላ አማኞችን ያጠነከራቸውና ያበረታታቸው መንፈስ ቅዱስ ነበር። 

ሐ. መንፈስ ቅዱስ በእሕዛብ ላይ ወረደ (ይህንንም ክስተት ወደፊት በሌላ ትምህርት እንመለከታለን።) 

መ. መንፈስ ቅዱስ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ይመራቸው ነበር። ጴጥሮስን ወደ ቆሮነሌዎለ ቤት መርቶታል። ጳውሎስና በርናባስን ለወንጌል መልእክተኝነት ሥራ በመለየት ወደ መጀመሪያው የወንጌል መልእክት ጉዞአቸው የላካቸው መንፈስ ቅዱስ ነው። አሕዛብ ክመጻናቸው በፊት የብሉይ ኪዳንን ሕዓጋትን በመከተል ወደ አይሁድነት መግባት ይባቸው እንደሆነና እንዳልሆነ በሚወያዩበት ወቅት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን የመራቸው እርሱ ነበር። ጳውሎስ በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ወቅት መንፈስ ቅዱስ ወደ አንዳንድ ስፍራዎች እንዳይሄድ በመከላከል ወደ ሌሎች ስፍራዎች ቀን እንዲሄድ መርቶታል። በኢየሩሳሌም እስር እንደሚጠብቀው ቢያውቅም እንኳ እንዲሄድ ግድ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ስለዚህ በመጀመሪያይቱ ቤተ ክርስቲያን ከመንፈስ ቅዱስ ዋነኛ አገልሎቶች አንዱ ለክርስቲያኖች በሥራቸው ምሪትን መስጠት ነበር። 

ሠ. አንዳንድ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን እረኞችና መሪዎች እንዲሆኑ የሚሾም መንፈስ ቅዱስ ነበር። ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩ ሽማግሌዎች የመጨረሻ የስንብት ንግግር በሚያደርግላቸው ወቅት እንደ መሪዎች የመረጣቸው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ነግሮአቸው ነበር። ስለዚህ ለራሳቸው ሕይወትና በቤተ ክርስቲያን ላሉ ክርስቲያኖች ሕይወት መጠንቀቅ ነበረባቸው። 

ረ. መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ሰዎች ስለ ወደፊት ጉዳይ ትንቢት እንዲናገሩ አስችሎአል። እነዚህ ሰዎች ጳውሎስ ወደ እስር ቤት እንደሚጣል አውቀው ነበር። ሆኖም ግን የሚናገሩት መልእክት ሁል ጊዜ ከመንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ ግልጽ አልነበረም። ምከንያቱም ጳውሎስ መደ ኢየሩሳሌም እንዳይሄድ ግድ ብለውት ነበር። ይህም ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ መንፈስ ቅዱስ እንዳዘዘው ከተናገረ በኋላ በመሆኑ ጉዳዩን ስናጤነው መንፈስ ቅዱስ በሚፈልገውና ነቢያቱ በሚፈልጉት መካከል የኦሳብ ግጭት ነበር። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከእነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች መካከል ዛሬ በቤተ ክርስቲያንህ የሚያስፈልጉት የትኞቹ ናቸው? ለምን? ለ) የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እንደሚገልጸው መንፈስ ቅዱስ ለፈጸማቸው ነገሮች ሁሉ የዛሬውን ትምህርት በመከለስ ዝርዝር አዘጋጅ። 

በዚህ ትምህርት የመንፈስ ቅዱስ ጥናታችንን በሐዋርያት ሥራ የተዘገበልንን በማየት ጀምረናል። በእያንዳንዱ ገጽ መንፈስ ቅዱስ ተጠቅሷል። በዓላምና በክርስቲያኖች የሚፈጸሙት ተግባራቱ ኢየሱስ ከጀመረው የአዲስ ኪዳን ዘመን ዋነኛ ምልክቶች አንዱ ነው። ክርስቲያኖች የአሳብ ልዩነት የሚያሳዩባቸውን ሰርካታ ክፍሎች በሌላ ትምህርት እናጠናለን። ነገር ግን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ስቃኘንበት ወቅት ከድነት (ደኅንነት) እስክ ክርስቲያናዊ እውነት ብሎም በቤተ ክርስቲያን እስከማገልገል ድረስ ያለው የማንኛውም ክርስቲያን ልምምድ የሚፈጸመው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሆኑ ተመልክቷል። ስለ መንፈስ ቅዱስ አወዛጋቢ ጉዳዮች ስናጠና ከመንፈስ ቅዱስ አገልቀሎቶች አብዛኛዎቹ አማኞች ሁሉ የሚስማሙባቸው እንደሆኑ መዘንጋት የለብንም። የሚበጀን የምንለያይባቸውን ነጥቦች እየመዘዙ መጣላት ሳይሆን የምንስማማባቸው ሰፊ ክልሎች እንዳሉ መገንዘብ ነው። በተጨማሪ ልዩነት በምናሳይባቸው ትምህርቶችና ልምምዶች ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ለመረዳት በጥንቃቄ ላማጥናት ቆርጠን እንነሣ። ይህንን በሚቀጥሉት ትምህርቶች እንደግማለን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: