በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጡ ትምህርቶች አጠቃላይ መግለጫ (ሐዋ. 1-2 )

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ካረገበት ቀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እሰከወረደበት ቀን ድረስ የነበሩት አምሳ ቀናት ለደቀ መዛሙርት እጅግ በጣም የተራዘሙባቸው ነበሩ። በመቶ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት በኢዩኤልና በነቢያት የተነገረው፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርትን በምድር ትቶ ወደ ሰማይ ከማረጉ ከጥቂት ጊዜ በፊት ያረጋገጠው የተስፋ ቃል ሊፈጸም ተቃርቦ ነበር። ሰማይና ምድር (አዲስ ዘመን) የሚጀመርበትን፥ መንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ የሚሰጥበትን ቀን በናፍቆት ይጠባበቁ ነበር። በድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ድምፅና በደቀ መዛሙርት ራስ ላይ እንደተቀመጠ ታላቅ የእሳት ልሳን ሆኖ መንፈስ ቅዱስ በዚያ አነስተኛ የአማኞች ጉባኤ ላይ ወረደ። የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተወለደች። ደቀ መዛሙርቱም ታሪክን መቀየር ጀመሩ። 

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የመጀመሪያቱን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይዘግባል። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚያሳየን መንፈስ ቅዱላ በደቀ መዛሙርት አገልግሎትና በቤተ ክርስቲያን እድገት ምን ያህል አስፈላጊ እንደነበረ ነው። አንዳንድ የሥነ መለኮት ሊቃውንት ይህን መጽሐፍ «የመንፈስ ቅዱስ ሥራ» ብለው የሚጠሩት ለዚህ ነው። የሚያሳዝነው ነገር ዛሬ በሥነ መለኮት «ካሪዝማቲክ» በሆኑ ቡድኖችና «ካሪዝማቲክ ባልሆኑት » መካከል ትልቅ ያለመግባባት እንዲፈጠር ያደረገው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ መሆኑ ነው። ዛሬ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ነገር በአጭሩ እናያለን። ወደፊ ት በተከታታይ በምናያቸው ትምህርቶች ደግሞ ከፍተኛ ያለመግባባት ያለባቸውን ክፍሎች በጥልቀት እንመለከታለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) የሐዋ. 1፡4-8፤ 15-17 አንብብ። ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ምን እንማራለን? ለ) የሐዋ. 2፡1-21፤ 32-33፤ 38-39 አንብብ። 1) መንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርት ላይ በወረደ ጊዜ ምን እንደተፈጸመ በራስህ ቋንቋ ግለጥ። 2) በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ስላ መንፈስ ቅዱስ የተነገሩ አንኳር እውነቶች ምንድን ናቸው? 

1. መንፈስ ቅዱስ በሐዋ. 1-2 ውስጥ 

ሀ. ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ የተሰጠው ተስፋ፡- የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚጀምረው ኢየሱስ፤ መንፈስ ቅዱስን ለደቀ መዛሙርት እንደሚል ክ በሰጠው የተስፋ ቃል ነው። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለደቀ መዛሙርት የተሰጠ «ስጦ ታ» ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ በርካታ እውነቶችን ማየት ይቻላል። 

1. መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስ የሚያጠምቀው በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ የተናገረ ሲሆን፥ ኢየሱስ ግን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያጠምቅ ብቻ ተናገረ። ይህ ምናልባት የእሳቱ ጥዏቀት ኢየሱስ በፍርድ ዳግም ላሚመጣበት ጊዜ የዘገየ በመሆኑ ይሆናል። 

2. የመንፈስ ቅዱስ መምጣት የመንፈስ ቅዱስ «ጥምቀት» ተብሎ ይጠራል። በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ እንጂ ተጠመቁ ያለማላቱን ልብ ማለት የሚያስገርም ጉዳይ ነው። ይህ የሚያመላክተው በሁለቱ ቃሎች መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ነው። 

«ጥምቀት» የሚለውን ቃል በሁለት መንገዶች ልንጠቀምበት እንችላለን። በመጀመሪያ፥ አማኞች በኢየሱስ ሲያምኑ በውኃ መጠመቃቸውን በቀጥታ እንደሚያመላክት አድርገን ልንወስደው እንችላለን። መጥምቁ ዮሐንስ ያደረገው ይህን ነበር (ማር. 1፡4)፥ ኢየሱስ የተቀበለው ይህን ነበር (ማር. 1፡9-11)፥ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርት ለአዲስ አማኞች እንዲያደርጉት የነገራቸውም ይህን ነበር (ማቴ. 28፡19)። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ቃሉ በምሳሌያዊ አቀራረብ አገልግሎት ላይ ውሎ ሊሆን ይችላል። ዮሐንስ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን ስላመስጠቱ ለማመልከት ተጠቅሞበታል። አዲስ ኪዳን ጥምቀትን ኈሁለት ምክንያቶች በምሳሌያዊ አቀራረብ ሳይጠቀምበት አልቀረም። በመጀመሪያ፥ ከውኃ ጥምቀት ሥርዓት ጋር በቅርብ የተያያዘ ነበር። በአዲስ ኪዳን አንድ ሰው ኢየሱስን እንደ ግል እዛኙ በሚቀበልበት ጊዜና በውኃ በሚጠመቅበት ጊዜ መካከል ምንም መዘግየት አልነበረም። አንድ ሰው ኢየሱስን ሲያምን ወዲያውኑ ይጠመቅ ነበር። አንድ ሰው ኢየሱስን አምኖ ሊጠመቅ ለዚህ አዲስ ክርስቲያን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በስጦታ መልክ ይሰጠው ነበር። ሰው ሰውኃ የሚጠመቀውና መንፈስ ቅዱስን በዚያው ጊዜ የሚቀበለው በአንድ ጊዜ ስለሆነ መንፈስ ቅዱስን መቀበል የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ተብሎ ተጠርቷል። ስሁለተኛ ደረጃ ፥ የውኃ ጥምቀት ሥርዓት ሰው ሙሉ በሙሉ እራሱን ከኢየሱስ ጋር አንድ የሚያደርግበት ምልክት ነበር። የውኃ ጥምቀት እማኙ ከክርስቶስ ሞት፥ መቀበር ና መነሣት ጋር እራሱን አንድ ማድረጉን በድርጊታዊ መግላጭ የሚያሳይበት ሥርዓት ነበር (ሮሜ. 6)። በተመሳሳይ መንገድ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መንፈስ ቅዱስ ከአዲሱ ክርስቲያን ጋር እራሱን አንድ ለማድረግ መኖሪያውን በልቡ ሊያደርግ እና የክርስቶስ አካል ከሆነችው ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሊያጣምረው እን ደመጣ የሚያሳይ ነበር (1ኛ ቆሮ. 12፡13)። 

(ማስታወሻ፡- ወደፊት በምንመለከተው አንድ ትምህርት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን ከመንፈስ ቅዱስ ሙላት ጋር እናወዳድራለን።) 

3. የመንፈስ ቅዱስ ከደቀ መዛሙርት ጋር የመሆን ጉዳይ ከኃይልና ከምስክርነት ጋር ተቆራኝቶ የቀረበ ነው። በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው ኃይል ከተአምራትና ከፈውስ ጋር የተያያዘ ለመሆኑ የምናየው ነገር የለም። ይልቁኑ ትኩረቱ ያረፈው ለምስክርነት የሚሆን ኃይልን በማግኘት ላይ ነው (የሐዋ. 2፡19። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ተቀዳሚ ትኩረት የተሰጠው የመንፈስ ቅዱስ ሚና ይህ ነበር። ኃይሉ በተአምራቶች ውስጥ የታየ ቢሆንም ወንጌልን ለመስበክ ከሚመጣው ኃይል ጋር ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው። 

ለ.የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ሊጻፍ የመንፈስ ቅዱስ ሚና፡- ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ በዳዊት አፍ (ወይም ቅዱሳት ጽሑፎችን በጻፈበት ብእርቹ)ተጠቅሞ የይሁዳን ጥፋት ስለግመልከቱ (የሐዋ. 1፡16) በተናገረው ንቀር በመንፈስ ቅዱስና በብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች መካከል የነበረውን የቅርብ ግንኙነት አሳይቷል። 

ሐ. በበዓለ ኀምሳ ቀን የመንፈስ ቅዱስ በደቀ መዛሙርት ላይ መውረድ፡- (ወደፊት በምንደርስባቸው ትምህርቶች ይህን በጥልቀት እናጠናላን የሐዋ. 2፡1-4)። 

ጥያቄ፡– እነዚህን ሦስት የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች መረዳት ዛሬ ለእኛ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.