በመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችና በአምልኮ ልምምዶች ውስጥ ያሉ ልዩነቶችን እንዴት መያዝ አለብን?

በትምህርት አንድ ክርስቲያኖች እምነታቸውን እግዚአብሔር ቃል ላይ በተለያየ ጊዜ እንደማይመሠርቱ ተመልክተናል። ደስ የሚያሰኛቸውን ነገር (ማለትም ስሜታቸውን) ወይም የቤተ ክርስቲያን ልምዶችና ባሕሎችን የእውነት ምንጭ አድርገው ይጠቀሙባቸዋል። ሁለቱም አደገኞች ስለሆኑ በእነርሱ ላይ መደገፍ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስሕተትን ያስከትላል። መሠረታችንንና አመለካከታችንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስናደርግ እንኳ በተለያዩ ምክንያቶች የአመለካከት ልዩነቶች እንዳሉ ተመልክተናል። የሚያሳዝነው ነገር አንዳንድ ጊዜ ይህ በክርስቲያኖች መካከል ፀብና ያለመግባባትን ማምጣቱ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚከሰቱት አሳዛኝ ነገሮች አንዱ ለትክክለኛ ነገር ሳይሆን ለተሳሳቱ ነገሮች ለንጋጭ መገኘታችን ነው። ዛሬ የምንኖረው ብዙም በማያሳስቡ ነገሮች ምክንያት በቤተ ክርስቲያን የማያቋርጥ መከፋፈል እያደገ በመጣበት ዘመን ነው። 

አንዳንድ ጊዜ እንደ ክርስቲያን ያለመግባባት ሁልጊዜ ስሕተት ነው ብለን እናስባለን። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሁለት ዓይነት ያለመግባባቶች አሉ። በመጀመሪያ ትክክለኛ ያልሆኑ፥ ኃጢአት ያለባቸው ከትዕቢትና ከራስ ወዳድነት የሚመነጩ ያለመግባባቶች አሉ። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ነገሮች ትክክል በመሆናቸው የሚመጡ አለመግባባቶች አሉ። ለምሳሌ፡- 

1. ክርስቲያኖች ስለሆንን ክርስቲያን ካልሆኑ ሰዎች ስደት ወይም አንዳንድ ያለመግባባት ሊያጋጥመን እንደሚችል የታወቀ ነው (ዮሐ 5፡18-21)። 

2. ሌሎች ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ለማድረግ ሲፈልጉ እኛ ግን ትክክለኛ ለሆነ ነገር ለመኖር በመወሰናችን ያለመግባባቶች ይፈጠራሉ። ይህ ክርስቲያን ካልሆኑ ስዎች ጋር ደግሞም ከዓለማዊ ክርስቲያኖች ጋር ሊፈጠር የሚችል ያለመግባባት ነው። ለምሳሌ በሥራ ገበታችን ላይ ጉቦ እንድንቀበል ብንጠየቅና ፈቃደኛ ሳንሆን ብንገኝ ሰሥራ ባልደረቦቻችን የተጠላን እንሆናለን። 

3. ስሕተትን በአብያተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያስተምሩ ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ስንቃወም ያለመግባባት ይኖራል። እግዚአብሔር ወይም የእግዚአብሔር ሕዝብ መሪዎች ለእውነት ሲሉ በግልጽ ስለመዋጋታቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ማስረጃ ዎች አሉ። የገላትያ መጽሐፍ በሙሉ ጳውሎስ እጅግ ጠቃሚ ለሆኑ እውነቶች ለመዋጋት ሲል የጻፈው ነው (ገላ. 1፡6-9 እንብብ)። የሚያሳዝነው ነገር ክርስቲያኖች ወንጌልን የሚያጣምሙ ሰዎችን የመቃወም ዝንባሌ ሳይኖረን ይልቁኑ ከእኛ እምነት ወይም ልምምድ ኢምንት ያህል የሚለዩትን ከመዋጋት አንመለስም። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሊሠሯቸው ከሚችሉት ትላልቅ ስሕተቶች አንዱ ለእውነት ያለመታገልና ሐሰተኛ አስተማሪዎችን ያለመቋቋም ነው። 

ችግሩ በአስፈላጊ ነገር ላይ መቼ መቃወም እንደሚገባንና ለአላስፈላጊ ነገር ደግሞ መቼ ዝም ማለት እንዳለብን ለይቶ ያለማወቅ ነው። እኛ ትክክል ነው ብለን ለምናስበው አመለካክት ሁሉ እንገደላለንን? ወይስ ከእነርሱ ጋር ያለመግባባትን ላለመፍጠር ላንል የፈለጉትን እንዲያደርጉና የፈለጉትን እንዲያምኑ እንተዋቸዋለን? እነዚህ ሁለቱም ዝንባሌዎች ትክክል አይደሉም። የሚያሳዝነው ግን ክርስቲያኖች ብዙ ጊዜ ከሁለት በአንዱ ውስጥ መውደቃችው ነው። 

ዋና ዋና መሠረታዊ ትምህርቶችና ዋና ዋና ትእዛዛት የሚያመላክተው በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለሚገኙና ከምንም ዓይነት ለውጥ ልንጠብቃቸው ስለሚገቡ ትምህርቶች ነው። በዚህ ውስጥ ቀጥሉ የተመለከቱ እውነቶችን መዘርዘር እንችላለን። ሀ) የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ ለ) ሥላሴና ሐ) የድነት (የደኅንነት) መንገድ። እነዚህ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ የእምነት ትምህርቶች ሊሆኑ ከእነዚህም እውነቶች በተቃራኒ የሚያስተምሩትን ጠንክረን ልንቋቋማቸው ይገባል። አንዳንድ ዋና የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ የእምነት ትምህርት አፍልሰው የሚያስተምሩትን እንደ ኢየሱስ ብቻ ኑፋቄ፥ እስልምና ወይም ባሃኡላህ እምነት ጋር የሚደረገው ትግል በዚህ ውስጥ ይካተታል። በሁሉም ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሊታዘዙአቸው የሚገቡ ግልጽ የሆኑ ትእዛዛትም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ይካተታሉ። ለምሳሌ፡- ሀ) አታመንዝር፥ ለ) አትግደል፥ ወይም ሐ) አትዋሽ የሚሉ ይገኙበታል። 

ጥያቄ፡- ሀ) በተለየ መንገድ ትምህርት ቢሰጥባቸው እጥብቀን ልንቃወማቸው የሚገቡ ሌሎች የመሠረተ እምነት ትምህርቶችን ዘርዝር። ለ) ክርስቲያኖች ሁሉ ሊታዘዙአቸው የሚገቡአቸው ባይታዘዙአቸው ቅጣት የሚያስከትሉ ሌሉች ትእዛዛትን ዘርዝር። 

ሁለተኛው፣ ውጫዊ የሆኑ መሠረታዊ የእምነት አስተምህሮዎችና ትእዛዛት ናቸው። እነዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እውነቶች ሲሆኑ የአቀራረባቸው ግልጽነት ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ልንሆንባቸው አንችልም። እነዚህን እውነቶች እንዴት እንደምንረዳቸውና ተግባራዊ እንደምናደርጋቸው የእግዚአብሔር ሰዎች በአሳብ ልንለያይ እንችላለን። 

ጥያቄ፡– በዚህ ክልል ውስጥ ይፈረጃሉ ብለህ የምታስባቸው አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የትኞቹ ናቸው? 

ክርስቲያኖች አንድ አቋም ይይዙ ዘንድ ግልጽ ያልሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰጡ በርካታ ትምህርቶች አሉ። ለምሳሌ፡- ሀ) ስለመጨረሻው ዘመን ትንቢቶች ያለን አመለካከት ኢየሱስ መቼ እንደሚመጣና በምድር ላይ በሥጋ ይነግሥ እንደሆነና እንዳልሆነ ለ) በአምልኮ ውስጥ በልሳን መናገር፥ ፈውስና ትንቢት ያላቸው ስፍራ። የሚያሰክር መጠጥ አለመጠጣት ወይም ከአንድ በላይ ሚስት ያገቡ ሰዎችን ያለማጥመቅ የመሳሰሉ ትምህርቶች እዚህ ውስጥ ይካተታሉ። በዚህ የሥነ መለኮት ትምህርት መጽሐፍ ውስጥ ስለ መንፈስ ቅዱስ የምንማራቸው ትምህርቶች ሰዎች በአንድ አሳብ የማይስማሙባቸው ብዙዎቹ በዚህ ክፍል ይመደባሉ። 

እነዚህ እምነቶች ክርስቲያን መሆን ወይም ያለመሆንን እውነት አይለውጡም። ክርስቲያኖች ክርስቲያንነታቸው ሳይነካ በእነዚህ እውነቶች ላይ ያላቸው መረዳት ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን የምናምነውን ወይም በተግባር የምንለማመደውን ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑልን መጠበቅ የለብንም። መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ ማጥናትና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምራቸውን ትምህርቶች ለመረዳት ተገቢውን ጥረት ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል ብለን ያመንበትን ነገር በተግባር የምንለውጠው ከዚህ በኋላ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ በሚመራው አእምሮአችን መገዛት አለብን። ይሁንና፥ ሌሎች ክርስቲያኖች ለእነዚህ እውነቶች የተለየ አተረጓጐም ቢሰጡም የመረዳታቸው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ እስከሆነና ተገቢ የአተረጓጐም መርሆዎችን እስከተከተሉ ድረስ ትርጓሜያቸውን በልበ ሰፊነት ልንቀበል ይገባል። 

ሦስተኛው፣ የተለየ አምልኮ ወይም የአኗኗር ዘይቤዎች (ልምምዶች) በመባል ይታወቃል። እነዚህ ከባሕል፥ ባሕል ወይም ከሰው ሰው የሚታዩ ልዩነቶች ወይም ምርጫዎች ናቸው። ከእነዚህ ልምምዶች አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን እንዴት እንደምናመልክ ተጽእኖ ያደርጋሉ። አንዳንድ · ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፀጥታንና ሃይማኖታዊ እክብሮትን ይመርጣሉ። ሌሎች ደግሞ እምልኮአቸውን ለመፈጸም ማጨብጨብና በደስታ መጮህ ይቀናቸዋል። የተለየ ከመሆኑ በቀር አንዱ ከሌላው አይሻ ልም። ወይም አይብስም። ሁሉም በተለያዩ ጊዜያት ጠቃሚ ናቸው። ሌሎች ደግሞ የአኗኗር ዘይቤ ልዩነቶች ናቸው። ለምሳሌ፥ በአንዳንድ ምዕራባውያን አገሮች የአሳማ ሥጋ ይበላል። ይህ በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ባሕላዊ ተቀባይነት የለውም። አንዳንድ ክርስቲያኖች ፊልም ቤት ይገባሉ፥ ወይም እንዳንድ ክርስቲያን ልጃ ገረዶች ሱሪ ይለብሳሉ፥ ወዘተ…። በአንዳንዶች ዘንድ ይህ ተቀባይነት የለውም። እነዚህ የተለያዩ ልምምዶች የሰውን መንፈሳዊነት ከፍ ወይም ዝቅ አያደርጉም። በእርግጥ ፊልሞቹ ላመንፈሳዊ ሕይወት ጐጂ የሆኑ ወይም የሰውን ምስክርነት የሚያበላሹ ከሆነ ልንመለክታቸው አይገባም። በመንፈሳዊ ሕይወታችን ላይ ብዙ የሚጫኑት ነገር ከሌለ በእነዚህ ጉዳዮች ስንጋጭ እንዳንገኝ መጠንቀቅ እላብን። ሰይጣን በክርስቲያኖች መካከል ያለመግባባት መኖሩ ያላደስተዋል። ምክንያቱም ይህን ልዩነት ላክፍፍል ምክንያት ያደርገውና እድገት እን ዳይኖር ወንጌልም እንጃይስፋፋ ይጠቀምበታል። 

ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች እርስ የማይስማሙባቸው በዚህ ክፍል የሚመደቡ ምሳሌዎችን ዘርዝር። 

ስለ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ወይም ልምምድ የልዩነት አሳቦች በሚኖሩበት ጊዜ ማድረግ ያለብን ቀዳሚ ነገር ይህ ጉዳይ በየትኛው ክብ እንደሚመደብ መወሰን ነው። ከዚህ በኋላ፥ በተቃውሞአችን በርትተን ለመግፋት ወይም የተለየ አመለካከት (እምነት) ወይም የአምልኮ ሥርዓት ስለሆነ በልበ-ሰፊነት መቀበል እንድንችል ትምህርቱን እንዴት እንደምናስተናግድ እናውቃለን። የምንጋደለው ለመሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መሆኑን አስታወሱ። በጣም አንገብጋቢ ባልሆኑ እውነቶችና ልምምዶች ላይ ክርስቲያኖች ሊለያዩ ነፃነት እንዳላቸው መገንዘብ ያስፈልጋል። ከመካከለኛው ክብ እየራቅን በሄድን ቁጥር ለመጋጨት ያላን ዝንባሌ መቀነስ አለበት። የሚያሳዝነው ነገር ብዙ ጊዜ የምናደርገው ተቃራኒውን መሆኑ ነው። ቀንደኛ የሆኑ የሐሰት ትምህርቶች ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲገቡ በመፍቀድ የእምነታችን ማዕከል እንዲናጋ እናደርጋለን። በአንጻሩ ከእኛ እምነት ጥቂት ለየት ያለ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ወይም ልምምድ ያላቸውን ለመዋጋት ፈጥነን እንነሣለን። 

ሆኖም ግን አንድ የማስጠንቀቂያ ቃል አለ። አንዳንድ ነገሮች በውጭ ባሉት ሁለት ክቦች ውስጥ ያሉ የሚመስሉ ሥራቸው ግን በውስጠኛው ክብ የሆነ አሉ። ለምሳሌ፡- አንድ ቡድን በልሳን መናገር ለክርስቲያን መንፈሳዊነት ብቸኛው መንገድ ነው ወይም በልሳን ካልተናገረ ወይም ካልተጠመቀ አንድ ሰው ክርስቲያን ወይም ሙሉ ክርስቲያን አይደለም ብሎ ቢያስተምር፥ እንዲህ ዓይነት ትምህርት ሰው በእግዚአብሔር ተቀባይነት ስለሚያገኝበትና እውነተኛው መንፈሳዊነት ምን እንደሆነ የሚያስተምረውን ውስጠኛውን ክብ ይነካልያ ወይም እግዚአብሔርን ስእውነት የምናመልከው እጆቻችንን ወደ ላይ ስናነሣ ብቻ ነው ቢል ሁለቱም አመለካከቶች ሰው በእግዚአብሔር ፊት ትክክል ሆኖ ጽድቅን የሚያገኝበትን ዋነኛውን መሠረታዊ የእምነት አስተምህሮ ስለሚነኩ መስተካከል አለባቸው። ይህ ማለት በውስጠኛው ክብ ውስጥ የተገለጹ ዋነኛ የመሠረታዊ እምነት አስተምህሮዎችን የሚፃረሩ አመላካከቶችን እንደምንፋለም ሁሉ፥ ይህን የሐሰት ትምህርትም መቃወም አለብን ማለት ነው። ጥያቄ፡– ሀ) በቤተ ክርስቲያንህ ዘልቀው በመግባት ክርስቲያኖችን ላሚግኑ ትምህርተች ባለቤት የሆኑ የሐሰት አስተማሪዎች እያጣመሙ የሚያስተምሩትን ሌሎች መነሻ የመሠረታዊ እምነት አስተምሮህዎችን ዘርዝር። የቤተ ክርስቲያንህ መሪዎች በግልጽ የሚቃወሙአቸው በየትኞቹ አቅጣጫዎች ነው? ለ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች እርስ በርስ የማይስማሙባቸውን ውጫዊ የሆኑ መሠረታዊ የእምነት ትምህርቶች ዘርዝር። ከላይ በተመለከቱት የክቦች ምሳሌ መሠረት እነዚህ ልዩነቶች መያዝ ያላባቸው እንዴት ነው? ሐ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ወይም በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ችግር የፈጠሩ አንዳንድ የእምልኮ ልምምዶችን ዘርዝር። እነዚህን ልዩነቶች እግዚአብሔርን በሚያስከብር መንገድ መያዝ ያለባቸው እንዴት ነው። መ) ክርስቲያኖች ስለ መንፈስ ቅዱስ ሚና ያላቸውን የተለያዩ መረዳቶች አስብ። እነዚህ አሳቦች በየትኛው ክብ ውስጥ የሚመደቡ ናቸው? ይህን ማወቅ አንድ የተለየ እመለካከትን የሚያስተምርን ሰው በጥብቅ ለመቃወም የሚረዳህ እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡- በመጀመሪያው ቀን ባየነው ታሪክ የመኮንንና የተስፋዩን ልዩነት ከልዕ። ሀ) የእነዚህ ሁለት ሰዎች ልዩነቶች በየትኛው ክፍል ውስጥ የሚመደቡ ናቸው? ለ) በዛሬው ትምህርት መሠረት እነዚህ ሁለት የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና የቀሩት የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች በቤተ ክርስቲያን ሰላምና መግባባትን ለማምጣት እንዴት መሥራት ይችላሉ?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.