የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 2

ብዙ ጊዜ የድነት (ደኅንነት)ን ጉዳይ እንደቀላል ሂደት እናቀርበዋለን። ነገር ግን ትናንትና እንዳየነው በጣም የተወሳሰበ ነው። እግዚአብሔር ከሚያደርጋቸው ታላላቅ ተአምራት አንዱ ሲሆን አፈጻጸሙም በፀጥታና በማይታይ መንገድ ነው። ሆኖም ግን ለዘላለም የሚዘልቅ ውጤት ያለው ብቸኛ ተአምር ነው። ሌሎች ተአምራት በሙሉ (እንደፈውስና በልሳን መናገር የመሳሰሉት ጊዜያዊ ጥቅም ነው ያላቸው። በዘላለም ሕይወታችን ላይ ግን ሚና የላቸውም። ትናንትና እንዳየነው ድነት (ደኅንነት) ታላላቅ ለውጦችን ያመጣል። በሕይወታችን የተደረጉት እነዚህ ለውጦች በጥቅል «ዳግም ልደት» ይባላሉ። 

ጥያቄ፡ የሚከተሉትን ክፍሎች አንብብ። ዮሐ 1፡12፤ 3፡5-8፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡11፤ 2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 5፡17፤ 1ኛ ዮሐ 2፡20፣ 26-27፡፡ ሰው በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ስለሚሠራቸው የተለያዩ ሥራዎች እነዚህ ጥቅሶች ምን ያስተምሩናል? 

1. መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያን አዲስ ሰማያዊ ልደት ይሰጠዋል፡- በአጠቃላይ አዲስ ፍጥረት ያደርጋቸዋል (ዮሐ 1፡12፤ 3፡5-8፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡17)። እግዚአብሔር በሕይወታችን ጥገናዊ ለውጥ አያደርግም። እንዳረጀ ልብስ አይደርስብንም። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አዲስ ያደርገናል። ወደዚህ ዓለም ተወልደን በመጣንበት ጊዜ አዲስ እንደነበርን ሁሉ መንፈሳዊ ልደት የሆነው ሁለተኛ ልደታችንም ሙሉ በሙሉ አዲስ ያደርገናል። ስለዚህ አዲስ ልደት በርካታ እውነቶች አሉ። 

በመጀመሪያ፥ ወዲያውኑ የሚሆን (ቅጽበታዊ) ነው። ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችን እንደተቀበልን ወዲያውኑ ይፈጸማል። ኢየሱስን እንደ ብል አዳኛችን የምንቀበልበት ሂደት ረጅም ቢሆንም በቅጽበት የእግዚአብሔር ልጆች የምንሆንበት የተወሰነ ጊዜ በእግዚአብሔር ዓይን ፊት አለ። የሰይጣን ልጆች የነበርን ቢሆንም እንኳ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር ልጆች እንሆናለን። በግሪክ ቋንቋ ይህ ሂደት የማይደገም የመንፈስ ቅዱስ ፍጹም ተግባር ነው። የሂደቱ ውጤት ቀን አንድ ጊዜ ከተጀመረ በኋላ ይቀጥላል። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ አዲስና ልዩ የሆነ ልማት ቢሰማንም ባይሰማንም የሚሆን ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በሕይወታችን ታላቅ ለውጥ መደረጉን ከመንፈሳችን ጋር ያረጋግጥልናል። አንዳንድ ጊዜ የለውጡ ውጫዊ ፍሬዎች ለመታየት ጊዜ ይወስዳሉ። 

ይህ አዲስ ልደት ሰማያዊ የሆነ አዲስ ተፈጥሮን ይሰጠናል። ይህ ሰማያዊ ተፈጥሮ ከኃጢአት ነፃ ሆነን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ተግባር እንድንፈጽም የማድረግ ችሎታ አለው። በመንፈሳዊ ብስለት እንድናድግና ክርስቶስን እንድንመስልም ያደርገናል። በዚህ አዲስ ተፈጥሮ ልባችን የመንፈስ ቅዱስ ዙሩን ወይም ቤተ መቅደስ ይሆናል። እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ፍሬ እንድናፈራ ያደርገናል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህን አዲስ ልደት የተለማመድከው መቼ ነበር? ላ) በሕይወትህ ለውጥ ያመጣው በምን መንገድ ነበር? 

ጥያቄ፡- ሀ) አንድ ክርስቲያን ኃጢአት ሲያደርግ መንፈስ ቅዱስ ትቶት ይሄዳል የሚል ትምህርት ክርስቲያን ሲያስተምር ሰምተህ ታውቃለህን? ለ) ያስተማሩትን ግለጽ። ሰው ኃጢአትን በሚያደርግበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ትቶት እንደሚሄድ ለማረጋገጥ የተጠቀሙት ጥቅስ ምን ነበር? ሐ) አንተ ስለዚህ ጉዳይ ምን ታምናለህ? ለምን? 

2. መንፈስ ቅዱስ ወደ ክርስቲያን ሕይወት ይመጣና ማደሪያው ያደርገዋል፡- የአዲስ ኪዳንን ዘመን ክብሉይ ኪዳን የተለየ የሚያደርገው ዋናው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ይህ ነው። አንድ ሰው በልሳን ካልተናገረ በስተቀር መንፈስ ቅዱስ ወደ ሕይወቱ ለመግባቱ ማስረጃ የላንም የሚሉ አንዳንድ ክርስቲያኖች አሉ። ይሁንና ካሪዝማቲክ የሆኑትንም ይሁን ያልሆኑትን አካትቶ የብዙ ክርስቲያኖች አጠቃላይ አስተሳሰብ እንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በሚያምንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ልጅ ልብ በመምጣት ማደሪያውን በዚያ ያደርጋል የሚል ነው። ጥቂት ቆይተን እንድ ሰው ከዳነ በኋላ መንፈስ ቅዱስ «ወሙሉ» ክርስቲያን እንዲሆን ማድረግ ስለሚገባው ነገር ያሉትን የአመለካከት ልዩነቶች እንመለከታለን። መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እንደሚኖር የሚያስረዱ ሦስት ዋና ማረጋገጫዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሉ። 

ሀ. መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ የሌለው ሁሉ ከእግዚአብሔር ኦይደለም ይላል (ሮሜ 8፡9 ተመልከት)። ይሁዳ ስለ ዘባቾች ሲናገር፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች መንፈስ ስላሌላቸው ከእግዚአብሔር አይደሉም ብሏል (ይሁዳ 19)። በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ከተጠቀሱት አንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች በስተቀር አንድ ሰው አማኝ ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ስለሌለው እግዚአብሔር እንዲሰጠው መጸለይ ያስፈለገበት ጊዜ አልነበረም። (ማስታወሻ፡— በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ክፍሎች አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ሳይኖረው ክርስቲያን ሊሆን እንደሚችል የሚያስተምሩ ቢመስሉም፥ እነዚሁ ክፍሎች መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ክርስቲያኖች ሊኖሩ መቻላቸውን እንደማያስተምሩ ቆይተን እንመለከታለን።) ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በውስጣቸው ለዘላለም እንደሚኖር ለደቀ መዛሙርት ነግሮአቸዋል (ዮሐ 14፡16-18፤ ማቴ. 28፡20)። ኃጢአት መንፈስ ቅዱስ ትቶን እንዲሄድ የሚያደርግ ከሆነ ኢየሱስም ትተን ይሄዳል ማለት ነው። ደግሞም አልዳንም ማለት ነው። ምክንያቱም መዳን ማለት መንፈስ ቅዱስን ማግኘት ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ የሌለው ማንኛውም ሰው አልዳነም። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ስጦታ ስለመሆኑ ሁልጊዜ የተነገረ ነው። (ዮሐ 7፡37-39፤ የሐዋ. 11፡16-17፤ ሮሜ 5፡5፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡12፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡5)። እነዚህን ጥቅሶች በሙሉ በቅርበት ብንመረምራቸው የሚያሳዩት መንፈስ ቅዱስ ለአንዳንዶች በአድልዎ የሚሰጥ ለሌሎች ክርስቲያኖች ደግሞ የሚከላከል እንዳልሆነ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ እንጂ ለጸሎት ወይም ለመልካም ሥነ ምግባር የሚሰጥ ሽልማት አይደለም። 

ሐ. ኃጢአትን በሚያደርጉ ክርስቲያኖች ሕይወት መንፈስ ቅዱስ መኖሩን እንደማይተው ተነግሮአል። ይህ አንዳንዶች ኃጢአት ስለሠሩ መንፈስ ቅዱስ እንዳይተዋቸው ከሚጸልዩበትም ሆነ፥ በኃጢአት ምክንያት መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያንን ሊተው ይችላል ብለው ከሚያስተምሩ ሰዎች ትምህርት ተቃራኒ .. ነው። በ1ኛ ቆሮ. 6፡19-20 በብዙ ኃጢአት ስለተቸገሩ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ጳውሎስ ሲናገር መንፈስ ቅዱስ እንደሚገኝ ጠቅሷል። (ማስታወሻ፡- የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በመክፋፈል ይኖሩ ነበር፤ በመንፈስ ትዕቢት ተሞልተው ነበር፤ በዝሙት የሚኖር ክርስቲያን በመካከላቸው ነበር። 

አንዳንድ ክርስቲያኖች ሌሎች ክርስቲያኖችን ለፍርድ ቤት ይከሱአቸው ነበር።) ጳውሉላ መንፈስ ቅዱስ ትቶአቸው እንዳይሄድ ይጸልዩ ዘንድ እላዘዛቸውም። ይልቁኑ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ስለሚኖር አኗኗራቸውን እንዲለውጡ ወቀሳቸው። ኃጢአት መንፈስ ቅዱስ በኃይል እንዳይሠራና ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠር ሊያግድ ይችላል። ኃጢአት መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል (ኤፌ. 4፡30፤ 1ኛ ተሰ 5፡19)። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ክሕይወታችን አያባርርም። 

ስለዚህ የአዲስ ኪዳን ግልጽ ትምህርት እንደሚያሳየው በየትኛውም ስፍራ በማንኛውም ባሕል የሚኖር ማንኛውም አማኝ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ አለው። ኃጢአት የመንፈስ ቅዱስን ህልውና አያስቀርም። ሆኖም ግን ኃጢአት ከሕይወታችን የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ሊወስድ እንደሚችል እንመለከታለን። ኃጢአት በመንፈስ ቅዱስ ሙላት» ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከላይ የቀረቡት ምክሮች ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ክርስቲያኖች ከሚያስተምሩት በምን ይለያሉ? ለ) የትኛውን አመለካከት ትመርጣለህ? ለምን? 

3. መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያንን ያጥባል (1ኛ ቆሮ. 6፡11)። በአዲስ ኪዳን ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ በኋላ ወዲያውኑ ይጠመቅ ነበር። የማመን ተግባርና የጥምቀት ሥርዓት በአንድ ጊዜ ይፈጸም ስለነበር በአንዳንድ ጥቅሶች እጅግ ተቆራኝተው ቀርበዋል። በሕዝቡ እእምሮና በትምህርቱ ይህ ሥርዓት በጥምቀት የኃጢአትን ታጥቦ መወገድ የሚያመላክት ነበር። ነገር ግን ጥምቀት ሰውን የሚያድነው ነገር አልነበረም። ይህ መንፈስ ቅዱስ የሚያደርገውን ውስጣዊ ማንጻት የሚያሳይ ውጫዊ ምላሴ ነበር። አዲስ ኪዳን የጥምቀት ሥርዓት በራሱ ሰውን እንደሚያድን በየትም ስፍራ አያስተምርም። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምረው መንፈሳዊ መንጻትን የሚያስገኝልን በኢየሱስ ላይ ያለን እምነት እንደሆነና ሰውን በመኮነን የእግዚአብሔር ፍርድ በላዩ እንዲሆን የሚያደርገው አለማመን ስለመሆኑ ነው። 

በአዲስ ኪዳን ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከልብላ ላይ ቆሻሻን እንደሚያስወግድ ውኃ ሆኖ ቀርቧል። መንፈሳዊ ቁሻሻችን የሆነውን ኃጢአታችንን አጥቦ ይጥላል። ከኃጢአት የነፃን ያደርገናል (1ኛ ዮሐ 1፡9)። የመንፈስ ቅዱስ ማንጻት ሁለት መልኮች አሉት። በመጀመሪያ፥ መንፈስ ቅዱስ በአቋም ‹ንጹሕን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ወደ እግዚአብሔር ህልውና ለመግባት የሚያስችል ዘላቂ መንጻት ይሰጠናል። በ1ኛ ቆሮ. 6፡11 ጳውሎስ ስለ መንፈስ ቅዱስ ማንጻት ስሚናገርበት ጊዜ የኃላፊ ጊዜን የተጠቀመው ለዚህ ነው። በሁለተኛ ደረጃ፥ በየቀኑ ከምንሠራው ኃጢአት በተደጋጋሚ የመንጻት ጉዳይም አለ። ይህንን የሚያደርገው የክርስቶስን ደም ወደ ሕይወታችን በማምጣት ነው። 

4. መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ይቀድሳል (1ኛ ቆሮ. 6፡11)። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ ተዘውትረው ከሚጠቀሱ ቃሎች አንዱ «መቀደስ» የሚለው ቃል ነው። ብዙ ጊዜ መቀደስ የሚለው ቃል ትርጉሙ ከኃጢአት ነፃ መሆንን የሚያመለክት ቢመስለንም፥ አሳቡ ግን «መለየት» ነው። በብሉይ ኪዳን እንስሳት፥ ከተሞችም እንኳ ለአምልኮ ወይም ሙሉ በሙሉ ለመጥፋት ለብቻ በመለየት ተቀድሰው እናያለን። ስለዚህ መቀደስ ማለት ከአንድ ነገር ለእግዚአብሔር አገልግሎት መለየት ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ስለ ግለሰቦች ስንናገር ይህ መለየት ከኃጢአት ሕይወት የመለየትን አሳብ ይይዛል። ይህን አሳብ በአዲስ ኪዳንም ቀጥሎ እናየዋለን። ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰዋል። ጳውሎስ በዚህ ስፍራም የተጠቀመው የኃላፊ ጊዜን እንደሆነ ልብ በሉ። ክርስቲያኖች ከዓለም ስለተመረጡ ከዓለም የተለዩ ናቸው። ለእግዚእብሔር ተለይተው ለእርሱ ጥቅምና ክብር ይሆናሉ። ይህ መለየት እራሳችንን ከኃጢአት ነፃ ማድረግን ይጨምራል። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ሲቀድሰን ከዓለም አውጥቶ ልዩ አድርጎ ሠራን። እርሱ እንዲጠቀምብን ለእግዚአብሔር አቀረበን። በሕይወታችን ላይ ያለውን የኃጢአት ኃይል የደመሰሰውም እርሱ ነው። (ማስታወሻ፡— መንፈስ ቅዱስ እኛን የቀደሰን በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ ሳይሆን በዕለታዊ ሕይወታችንም በተግባራችን ንጹሕ እንድንሆን ይሠራናል። ስለዚህ መቀደስ ሙሉ በሙሉ የተፈጸመ ኃላፊ ሥራንና በጊዜው የሚከናወነውን ቀጣይ የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ያጠቃልላል።) 

5. መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያንን ያጸድቃል (1ኛ ቆሮ. 6፡11)። በዚህ ጥቅስ ውስጥ የምንመለከተው የመንፈስ ቅዱስ ምስተኛ ሥራ ይኸውም የጽድቅ ሥራ ነው። እንደምታስታውሱት ‹ጻድቅ» የሚለው ቃል ‹ጥፋተኛ አይደለም› ለማላት በፍርድ ችሎት የሚሰነዘር እነጋገር ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ የኃጢአትን ቅጣት ስለከፈለና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የክርስቶስን የመስቀል ሥራ በሕይወታችን ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኃጢአታችንን ስለሚሸፍንልን እግዚአብሔር ክርስቲያኖች በሙሉ «ጥፋተኞች አይደላችሁም» ወይም ጻድቅ ናቸሁ ብሎ ያውጃል። አዎን አሁንም ቢሆን ኃጢአትን እናደርጋለን። ነገር ግን የኃጢአታችን ዋጋ በመስቀል ላይ ተከፍሎእል። ከምንፈጽመው ኃጢአት በመስቀል ላይ በፈሰሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሊሸፈን የማይችል አንድም እንኳ የለም። ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ እኛ በሚመለከትበት ጊዜ በእርሱ ፊት በኃጢአት ምክንያት ጥፋተኞች ያለመሆናችንን እንደሚናገር እናውቃለን። ክዳንን በኋላ የምንፈጽማቸው ኃጢአቶች ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ያበላሹብናል። ነገር ግን በዳንንበት ጊዜ እግዚአብሔር «ጥሩተኞች አይደላችሁም» ብሎ ያወጀውን አዋጅ ሊያሽሩ አይችሉም። ለክርስቲያኖች የኃጢአት ኑዛዜ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለማደስ እንጂ እግዚአብሔር በእኛ የጣለውን «ጥፋተኛ ነህ» የሚል ፍርድ ለማንሣት አይደለም። 

ጥያቄ፡- በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ስለሠራህ፥ ከእርሱ ፍቅርንና ተቀባይነትን ማግኘት የማይገባህ አድርጎ ሰይጣን ሊከስስህ፥ እዚህ ሦስት የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ልዩ በረከት የሆኑልህ እንዴት ነው? 

6. የመንፈስ ቅዱስ ቅባት (2ኛ ቆሮ. 1፡21፤ 1ኛ ዮሐ 2፡20፣ 26-27)። በብሉይ ኪዳን ዘመን አንድ ሰው በዘይት ሲቀባ ድርጊቱ የሚያሳየው ያ ሰው ወይም ነገር እንደ ልዩና ቅዱስ ተደርጎ ለብቻ መለየቱን ነበር (ዘፀአ 30፡25-33)። በኋላ በዘይት መቀባት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በቅርበት በመያያዝ፥ መንፈስ ግለሰቡን ለአገልግሎት ማስታጠቁን የሚያመለክት ሆነ (ለምሳሌ ዳዊት)። በአዲስ ኪዳን መቀባት የሚለው ቃል በአብዛኛው የተጠቀሰው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ለምሳሌ ሉቃ. 4፡18፤ የሐዋ. 4፡27)። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ አማኞችን እንደሚቀባ ሦስት ጊዜ ተጽፎ እንመለከታለን። (ማስታወሻ፡- በ1ኛ ዮሐንስ በአማኞች ውስጥ የሚኖር፥ የሚያስተምራቸውና ከስሕተት የሚጠብቃቸው መንፈስ ቅዱስ፥ ቅባት የሚል ሌላ ስም ተሰጥቶታል።) የእነዚህ ሦስት ጥቅሶች ዘለቅ ያላ ጥናት የሚከተሉትን እውነቶች ግልጽ ያደርጋል። 

ሀ. በመንፈስ ቅዱላ መቀባት በእግዚአብሔር እንጂ በሰዎች የሚከናወን ነገር አይደለም። 

ለ. በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ያለቀ የተጠናቀቀ ተግባር ነው። ለአንዴና ለመጨረሻ የተደረገ ነው። ይህን የሚያረጋግጠው፥ በእነዚህ ጥቅሶች በእያንዳንዳቸው፥ በግሪኩ ቋንቋ የተመለከተው ግሥ በአሁኑ ጊዜ ውጤትን ለሚሰጥ የኃላፊ ጊዜ የሚያገለግል መሆኑ ነው። በመንፈስ ቅዱስ እንድንቀባ የታዘዝንበትም ቦታ የለም። 

ሐ. ቅባቱ በክርስቲያኖች ሁሉ ላይ ነው። አንዳንድ ክርስቲያኖች እንደሚቀቡ ሌሎች እንዳማይቀቡ የሚገልጽ ምንም መረጃ የለም። 

ሰው በመንፈስ ቅዱስ ለምን እንደሚቀባ እዲስ ኪዳን ፈጽሞ በግልጽ አይናገረም። መንፈስ ቅዱስ ክርስቲያኖችን እንዲያስተምር ከተፈለገ መቀባት እንደሚቀድም እናውቃለን። ነገር ግን ይህን አሳብ በብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ውስጥና በክርስቶስ ውስጥ ስንመለከተው ለእግዚአብሔር ከሚሰጥ አገልግሎት ጋር ተቆራኝቶ እናገኘዋለን። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚሰጠው ቅባት ዓላማ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየት ነው ብንል ከእውነት አንርቅም። 

ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ መቀባት የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከመሆን ጋር ተመሳሳይ ነው። ሁለቱም ተመሳሳይ የሚሆኑት ለአንዴና ለመጨረሻ ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚደረጉ በመሆናቸው ነው። ይህ እውነት የመንፈስ ቅዱስ ልዩ መቀባት አለን ስለዚህ ልዩ ተአምራትን ለማድረግ እንችላለን በማለት ከሚያስተምሩት ጋር ተመሳሳይ አይደለም። ብሉይ ኪዳንም ሆነ እዲስ ኪዳን በመንፈስ ቅዱስ መቀባትን በዚህ መልክ እያቀርቡትም። ስለዚህ ይህ ነገር ልዩ «ቅባት» ብለው የሚናገሩትን ከመሻት እንድንጠነቀቅ ሊያደርገን ይገባል። 

ጥያቄ፡- የመጀመሪያዎቹን ሁለት ቀናት ትምህርት ስልስ። መዳን ትችል ዘንድና በጻንክበትም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሕይወትህ ያደረገውን ዘርዝር፡ ያንን ዝርዝር በመጠቀም ሥላሴ የሆነውን አምላክ በጸሎት አመስግን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.