የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል ሦስት)

ጥያቄ፡- ሀ) የሙሉ ወንጌል መጋቢ ወይም ወንጌላዊ የሆነን ሰው በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ስለሚፈጸመው ሁለተኛ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ማስረጃ የሆኑ ጥቅሶችን እንዲነግርህ ጠይቅ። ለ) ለእነዚህ ጥቅሶች የሚሰጠውን ማብራሪያ (ትርጉም) አድምጥ። ሐ) እነዚህን ጥቅሶች የምንረዳባቸው ሌሎች መንገዶች የትኞቹ ናቸው? መ) የትኛውን ትርጉም ትመርጣለህ? ለምን? 

ጰንጠቆስጤ በሆኑትና ባልሆኑት መካከል ያለው የትርጉም ልዩነት ከየት መጣ። በመሠረቱ የጰንጠቆስጤ የሥነ መለኮት ትምህርት የተመሠረተው የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን በሚረዱበት ሁኔታ ላይ ነው። የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች የሐዋ. ምዕራፍ 2፣ 8፣ 10ና 19 ያሉት አሳቦች ክርስቲያኖች ሁሉ ሊያልፉበት የሚገባ የድነት (ደኅንነት) ሁለት ደረጃዎች ናቸው ይላሉ። የመጀመሪያው የድነት (ደኅንነት) ደረጃ ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ ለአገልግሎት አዲስ ኃይል መቀበል ነው። እነዚህ ሁለት ደረጃ ዎች እንድ ሰው በሚያምንበት ጊዜ ወዲያውኑ ሊፈጸሙ ይችላሉ። ሆኖም ግን ኃይልን መቀበል ብዙ ጊዜ የሚፈጸመው አንድ ሰው ክርስቲያን ከሆነ በኋላ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ልምምድንም ይጠቅሳሉ። የተወለደው በመንፈስ ቅዱስ ነበር። ሆኖም ግን መንፈስ ቅዱስ በኃይል የወረደበት በሚጠመቅበት ጊዜ ነበር። ይህ በመንፈስ ቅዱስ መወለድና ለአገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ መቀባት ሁለት ደረጃ ለእነርሱ የተለመደ የማንኛውም ክርስቲያን ልምምድ መሆኑን ያመለክታል። እነዚህ የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች ወደ ራሳቸው ልምምድም በማመልከት እዚህ ሁለት ደረጃዎች ማንኛውም ክርስቲያን ሊያልፍባቸው የሚገቡ ናቸው ይላሉ። ለብዙዎቹ መንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸውን አስደናቂ በሆነ መንገድ የለወጠበት የተለየ ጊዜ አላቸው። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትንና የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን አንድ ልምምድ አድርገው ይመለከታሉ። 

ይህ ሁለተኛው በረከት ወይም የመንፈስ ቅዱስ ቅባት የሚፈጸመው እንዴት ነው? ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት በአዲስ ኪዳን በኢየሱስ በቀደሙት ደቀ መዛሙርትና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ደግሞ እንደ ጳውሎስ ባሉ ሰዎች ሕይወት የሚታይ ወጥ የሆነ ምሳሌ አለ። ይህም በመጀመሪያ የሕይወት ለውጥ ይኖራል። ቀጥሎ ጸሎት ከዚያም እራስን ፈጽሞ መስጠትና በመጨረሻም የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመቀበል መጠበቅን ያካተተ ሂደት ነው። መቶ ሃያዎቹ ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ አመኑ። ከዚያም በጸሎትና መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በጉጉት በመጠባበቅ በኢየሩሳሌም ቆዩ። ሳውልም (ጳውሎስም) ሆነ የመቶ አለቃው (የሐዋ. 10) መንፈስ ቅዱስን ከመቀበላቸው በፊት ጸሎት መደረግ ነበረበት። ስለዚህ የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች ይህን ልዩ የሆነ በረከት እንቀበል ዘንድ ካስፈለገን በጸሎት አንዳንድ ጊዜም በተራዘመ ጸሎት ልንፈልገው ይጠበቅብናል ይላሉ። በተጨማሪ እግዚአብሔር መንፈሱን ለእኛ እስኪልክ ድረስ በከፍተኛ ጉጉት መጠባበቅ አለብን ይላሉ። እንደ እነርሱ አመለካከት፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድባቸው በግል ጥረታቸው የሚያስገድዱት ሳይሆን በእምነት ላለመቀበል የሚፈጽሙት ድርጊት ነው። 

ለካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ይህ ሁለተኛ በረክት የሚረጋገጠው እንዴት ነው? መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ በኃይል መውረዱን የሚያውቁት እንዴት ነው? ኢየሱስ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ሊሰጠን በርካታ ነርች እንደሚፈጸሙ ይናገራሉ። 

1. በሳውዲው ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ህልውና በከፍተኛ ደረጃ የሚሰማ ይሆናል። መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን የሚያስወድድ ክፍተኛ ፍቅርን ይሰጣል። 

2. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ለመሆኑ ግልጽ የሆነ ማረጋገጥ በሰው ልብ ውስጥ ይቀመጣል። 

3. የሚያስፈነድቅ ደስታ ከሰው ልብ ውስጥ እየገነፈለ ይወጣል። 

4. የክርስቶስ አካል ከሆኑት ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር የኅብረትና የአንድነት መንፈስ የጠበቀ ይሆናል። 

5. ብዙ ጊዜ ደግሞ በልሳናት የመናገር ስጦታ ይሰጣል። በካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እምነት በልሳን መናገር እርስ በርስ ወይም ከማያምኑ ሰዎች ጋር የምንነጋገርበት ቋንቋ ከመሆን ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር የምንግባባበት ነው። ስልሳን የሚናገር ሰው ብዙ ጊዜ ምን እንደሚናገር አያውቅም። ይልቁኑ በእርሱ ምትክ ስለ እርሱ ሆኖ ለእግዚእብሔር የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው። (በወደፊት ትምህርታችን ይህንን በበለጠ በጥልቀት እንመለከታለን) በአእምሮ ሳይሆን በመንፈስ መጸለይና መዘመርን ያጠብቃሉ። ብዙ ክርስቲያኖች በተለይ በጸሎት ጊዜ በጸጥታ ስልሳናት የሚናገሩትና በልሳናት በዜማ የሚዘምሩት ለዚህ ነው። ይህን ማድረጋቸው በመንፈስ የመጸለያቸውን ሁኔታ ያነሣሣል። 

እነዚህ ሁሉ በአጠቃላይ ስሕተት ባይሆኑም እንኳ የሚከተሉት ልንመልሳቸው የሚገቡን ጥያቄዎች ናቸው። ) መጽሐፍ ቅዱስ እንደ «ሁለተኛ በረከት» ያለ ልምምድ መኖሩን ያስተምረናልን? እና 2) ይህ በረከት በልሳናት መናገርን ያጠቃልላል? ወይስ ማጠቃለል አለበት ብሎ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል? የካሪዝማቲክ ክርስቲያናዊ ሥነ መለኮት እንደ ግዴታ ለሚያስቀምጣቸው ሁላተኛ በረከትና በልሳን መናገር በመልእክቶች ውስጥ ድጋፍ የሚሰጥ በቂ መረጃ አይገኝም። የሥነ መለኮት ትምህርታቸው በሙሉ የሚመነጨው ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ነው። ይህ መጽሐፍ ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የተደረገውን ሽግግር የሚያሳይ ነው። 

ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች እምነታቸውን ለመደገፍ የሚጠቀሙበትን የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ በዝርዝር ከመመልከታችን በፊት የሚጠቀሙበት መጽሐፍ ምን እንደሚያስተምር እንቃኝ። 

ጥያቄ፡ ሀ) የሚከተሉትን ጥቅሶች አጥና። የሐዋ. 1፡5፥ 2፡4፥ 38-39፥ 4፡8፤ 31፤ 6፡3፥ 5፥7፤ 55፤ 8፡14-17፤ 9፡17-18 (22፡16)፤ 10፡44-47 (11፡5-17)፤ 13፡9፥ 52፤ 19፡1-7 አንብብ። ለ) በሚከተሉት ርእሶች ሠንጠረዥ በመሥራት መልሶቹን ከተዘረዘሩት ጥቅሶች ወስደህ ሙላባቸው። (1) ለመንፈስ ቅዱስ ተግባር የተሰጠ ስም (2) መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉበት ጊዜ (ሐ) በልሳን ተናግረዋልን? (መ) እጅ በመጫን ጸሎት ተደርጓልን?

የመንፈስ ቅዱስ አጠቃላይ ገጽታ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ 

1. ብዙ የጴንጠቆስጤ አማኞች ሉቃስ ጥምቀት፥ መሞላት፥ መቀበልና መውረድ የሚሉትን ቃላት የተጠቀመው በዓይነቱ እንድ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎትን ለመግለጽ ነው፤ ይህም አንድ አማኝ ከዳነ በኋላ የአገልግሎት ኃይልን . የሚጎናጸፍበት ነው ይላሉ። ጰንጠቆስጤ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ይህ የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት አገልግሎቶችን የሚያመለክት ሆኖ እንዳንዶቹ አገልግሎቶች በአንድ ጊዜ የሚፈጸሙ ሊሆኑ አይችሉምን? ይላሉ። ሉቃስ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመግለጥ የተለያዩ ቃላትን እንደተጠቀመ የሚያሳይ አይሆንምን? አንዳንድ ጰንጠቆስጢዎች ሁለት ዓይነት መሞላት በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንዳለ ይታያቸዋል። ከድነት (ደኅንነት) በኋላ የሚጀምር የመጀመሪያ ጊዜ መሞላትና ከዚያ በየጊዜው የሚመጣ መሞላት ነው ይላሉ። 

2. ከእነዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች አንዳንዶቹ በድነት (ደኅንነት) ወቅት የተፈጸሙ ቢመስሉም ብዙ ጰንጠቆስጤዎች ግን እነዚህ ሰዎች በሙሉ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የተቀበሉት ከድነት (ደኅንነት) በኋላ ነው በማለት ይናገራሉ። አንዳንዶች መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ከድነት (ደኅንነት) በኋላ ስለሆነ ደንቡ ይህ ነው ይላሉ። በሐዋ. 2 ላይ የምናገኛቸው አዲስ ክርስቲያኖችና በሐዋ 10 ላይ የተጠቀሰው ቆርኔሌዎስ በመንፈስ ቅዱስ ጥምቀታቸውና በደኅንነታቸው መካከል ጥቂትም ቢሆን ጊዜ ነበር ይላሉ። ጳውሎስ ዳግም የተወለደው በደማስቆ መንገድ ሲሆን መንፈስ ቅዱስን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበላው ቀን ከሦስት ቀን በኋላ ነበር ይላሉ። ሆኖም ግን እነዚህን ክፍሎች እንዳሉ ስንመረምራቸው እነዚህ ሰዎች የተጠቀሱትን የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች የተቀበሉት በሚድኑበት ጊዜ ነበር። በሚቀጥለው ሳምንት ይህን ክፍል በጥልቀት እናጠናዋለን።) 

3. አብዛኛዎቹ የጰንጤቆስጤ ክርስቲያኖች ስልሳናት ላለመናገር ባልተጠቀሱባቸው ቦታዎችም በልሳናት መናገር እንደነበር ያምናሉ። ጳውሎስ በኋላ በልሳናት ይናገር ስለነበር (1ኛ ቆሮ. 14፡18) በመንፈስ ቅዱስ በሚጠመቅበት ጊዜ ተናግሯል ይላሉ። በሐዋ. 4፡3 ላይ ሰዎቹ «የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ ተናገሩ» የሚለው ቃል በልሳናት መናገርን የሚያመለክት አሳብ ነው ብለው ያምናሉ። በሐዋ. 8 ላይ የሰማሪያ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ መቀበላቸው በማስረጃ ነት በሌሎች ሦስት ቦታዎች ስለታየ በእነዚህ ቦታዎችም መኖር ነበረበት ይላሉ። ሆኖም ግን በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እነዚህ ሰዎች በልሳን ተናገሩ አይልም። እንደገና በልሳናት መናገር ከታየባቸው ሦስት ግልጽ ሁኔታዎች ሌላ ክፍሎቹን እንዳሉ በምናነባቸው ወቅት በልሳናት መናገር እንዳልነበረ እንገነዘባለን። ስለዚህ የሚባል ነገር ካለ በልሳናት ስለ መናገር ምንም ነገር አለመጠቀሱ ነው። 

4. ብዙ የጰንጠቆስጤ ክርስቲያኖች የሐዋ. 2፡38 በክርስቲያን ልምምድ ውስጥ ስላሉ ሦስት ተከታታይ ደረጃ ዎች የሚያስተምር ነው የሚል ግንዛቤ አላቸው። መጀመሪያ ንስሐ መግባት፥ ከዚያም መጠመቅ፥ በመጨረሻም መንፈስ ቅዱስን መቀበል ናቸው። መጽሐፉ ግን ሁለት ትእዛዞችን ብቻ ይሰጣል። ‹ንስሐ ግቡና ተጠመቁ›፥ ከዚያም የተስፋ ቃል ይከተላል። ‹ትቀበላላችሁ› {የወደፊቱን የሚያመላክት})። ተስፋው የመጀመሪያዎቹን ሁላት ትእዛዞች መፈጸምን በቀጥታ የሚከተል ነው። ክፍሉን በግልጽ ስናነብ የሚያመለከቱን ንስሐ የገቡና የተጠመቁ መንፈስ ቅዱስን መቀበላቸውን ነው። በተጨማሪ ጥምቀት ለድነት (ደኅንነት) አስፈላጊ መሆኑን ክፍሉ እያስተምርም። ሐረጉ በዚህ መልክ መተርጎም ይችላል። ‹ንስሐ ግቡ ከኃጢአታችሁ ይቅር መባል የተነሣም ተጠመቁን። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ንስሐ በመግባት ለተገኘ ውስጣዊ ምሕረት ውጪአዊ ምልክት ነው። በኢየሱስ ማመናቸው ትክክለኛ እምነት መሆኑን ለማረጋገጥ፥ በኢየሱስ ስም መጠመቅበዚህ ወቅት ለነበሩ የአይሁድ ቡድን በጣም አስፈላጊ ነበር። 

5. ሰዎች በአብዛኛው ሐናንያን ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ በመቀበል ሕይወቱ የተለወጠው በደማስቆ መንገድ ላይ ነው ይላሉ። ሆኖም ግን የሐዋ 22፡16 ግልጽ እንደሚያደርገው ሐናንያ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ጳውሎስ ሲመጣ ጳውሎስን ያገኘው ገና ሳይለወጥና ኃጢአቱ ሳይታጠብ ነበር። ጳውሎስ የሦስት ቀን ዕውርነቱን ያሳለፈው ባየው ድንገተኛ መገለጥ አማካኝነት ኢየሱስ በሰማይ ሕያው ሆኖ መኖሩንና ጌታም መሆኑን ላለ መመልከቱ እያሰበና ከዚህ ቀደም ስለፈጸማቸው ተግባራት እያሰላሰለ ነበር። ሐናንያ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ በግሉ በመቀበል ምላሹን ልክ እኛ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና በተቀበልንበት ዓይነት ሁኔታ፥ ጳውሎስም በመንፈስ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሞላው በዚህ በተለወጠበት ቅጽበት ይመስላል። 

6. እዚህ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ሳይገናኛቸው በፊት ድነው ነበርን? የጰንጠቆስጤ እማኞች እዎን የሚል መልስ የሚሰጡ ቢሆንም እንኳ ክፍሉን በቅርብ በምንመረምርበት ጊዜ ይህን እንደማይደግፍ እንገነዘባለን። የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ መሢሕ እንደሆነ ከዮሐንስ ትምህርት ተረድተው ይሆናል ነገር ግን የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤ ሳላለመረዳታቸው የምናውቀው ነገር የለም። አለበለዚያ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ለምን አልሆኑም? ስለዚህ ይህ ክፍል የሚያስተምረን የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ባመኑ ጊዜ መሆኑን ነው። 

ማጠቃለያ፡- የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላትና ጥምቀት ተመሳሳይ የሆነ ትምህርት አይሰጥም። በሁሉም ጊዜያት ውስጥ ያሉትን ነገሮች የሚያስር አንድ ወጥ አሠራር እናገኝም። አብዛኛዎቹ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት በዳኑበት ቅጽበት ነው። ግን ሁሉም አይደሉም። (ለዚህ ምክንያት እንደነበረው ወደፊት እንመለከታለን።) እጅን በመጫን መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉት ጥቂቶች ብቻ ናቸው። መንፈስ ቅዱስን ለመቀበላቸው ማስረጃ ይሆን ዘንድ በልሳናት የተናገሩ ሲሆን ልምምዶቹ ዛሬም ያሉ ክርስቲያኖች በሕይወታቸው መከተል የሚገባቸው ምሳሌ መሆኑን በግልጽ አይነግሩንም። 

ጥያቄ፡- ቀደም ብሎ የነበረውን ሠንጠረዥ እጥና። ሀ) የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ሙላትን ስለምንረዳበት ሁኔታ አንዳንድ ፍንጮች የሚሰጡ ከሠንጠረዥ ጐልተው የሚወጡ ምን ዓይነት ወጥ አካሄዶች ትመለከታለህ? ለ) ስለ እነዚህ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች የምታምነው ምንድን ነው? ለምን? 

በአብዛኛው ይህ ክርክር አላስፈላጊ ይመስላል? ልዩነቱ ምንድን ነው? በሕይወቴ ላይ ምን ተጽእኖ አላው? የምንነጋገረው ነገር እንድን እውነት በተለያዩ መንገዶች • መግለጥ ከሆነ ወይም ቅዱሳት መጻሕፍትን በምንረዳባቸው መንገዶች የሚታይ አነስተኛ ልዩነት ከሆነ ለምን እንጨነቃለን? መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ለመረዳት ጥረት ለማድረግና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አቋምን ለመረዳት ጊዜ መውሰድ የሚያስፈልግበት ሁለት ዋና ምክንያቶች አሉ። በመጀመሪያ፥ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በእርግጥ ካመንን እንደ ክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጻፉትን ላማመንና ብሎም ለመለማመድ ግዴታ እለብን። ይህ ማለት ትምህርቶችን በሙሉ የራሳችንንም ቢሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን መመርመርና ትክክለኛ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን። ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይጣጣም ማንኛውም ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ቅኝት መሠረት መስተካክል አለበት። አለበለዚያ ትምህርታችን በመጽሐፍ ቅዱስ ሊዳኝ ሊገባ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ራሳችን ጻኞች ሆንን ማለት ነው። እንደ እግዚአብሔር ቃል ለመኖር የትሕትናን ስፍራ ከመያዝ ይልቅ የትዕቢት ኮርቻ ላይ ወጥተናል ማለት ነው። 

ሁለተኛ፥ በስሕተት ውስጥ መውደቅ ራሱን የቻለ ሂደት ነው። ብዙ ጊዜ ስለ ስሕተቱ የመጀመሪያው እርምጃ መሠረታዊ የእምነት ትምህርታችን ከእግዚአብሔር ቃል መጣጣሙን ለማረጋገጥ አለመትጋት ነው። የተወሰኑ ክፍሎችን ብቻ መርጠን እነዚያን ስናስተምር ሰይጣን ለራሱ ጥቅም በሚገለገልበት የአዘቅት ነጻና ማሽቆልቆል ጀምረናል ማለት ነው። ስለዚህ በመሠረታዊ የእምነት ትምህርታችን ሚዛን ማጣት እንጀምራለን። ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣ ማንኛውም ነገር ክፍት በር ያገኛል። ብዙም ሳይቆይ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ከሚያስተምረው ሳዝነው ይገኛሉ። እንድን ሰው ወይም የእምነት ክፍል የሚፈልጉት ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መሄዱን ሳያረጋግጡ እንዲያምኑ ብንፈቅድ ስሕተታቸውንና የብዙ ሌሎች ክርስቲያኖችን በስሕተት ላይ መውደቅ እያበረታታን ነው ማለት ነው። 

2ኛ ጴጥ፡- 3፡16-18 «…ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። እንግዲህ እናንናተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስላምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።» ይላል። ምሳ. 27፡5-6 ደግሞ «የተገለጠ ዘለፋ ከተሰወረ ፍቅር ይሻላል። የወዳጅ ማቍሰል የታመነ ነው፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው» ይላል። 

ስለዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ ስናጠና ስለ ሁለት ነገሮች ግድ ሊለን ይገባል። የመጀመሪያው፥ የምናምነውና የምናስተምረው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ስላ መሆኑ ነው። ይህም ማናችንም ብንሆን እውነትን ሙሉ ለሙሉ አለመያዛችንን ሁልጊዜ ስለምናውቅ እምነታችንን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ለማስተካከል እንጥራለን ማለት ነው። ሁለተኛ፥ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በእውነት ሲሄዱ፥ እግዚእብሔርን በሚያከብር መንገድ ሊኖሩና ሲያመልኩ ለመመልክት እንመኛለን፤ ይገደናልም። 

ጥያቄ፡- ሀ) እነዚህ ሁለት እውነቶች አስፈላጊ የሚሆኑት ለምን ይመስልሃል? ለ) በሕይወትህ ወይም በቤተ ክርስቲያንህ እነዚህ እውነቶች (ሲተገበሩ እንዴት እንዳየህ ምሳሌ ስጥ። ሐህ እነዚህ እውነቶች በቤተ ክርስቲያን ካልተፈጸሙ አደገኛ የሚሆነው ለምንድን ነው?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.