የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ክፍል አንድ)

(ማስታወሻ፡- ለሚቀጥሉት በርካታ ትምህርቶች የሚሆኑት መረጃዎች በአብዛኛው የተገኙት የኤስ አይ ኤም ሚሲዮናዊና የኢቫንጀሊካል ሥነ መለኮት ኮሌጅ ዳይሬክተር ክሆነው ከስቲቭ ስትራውስ የክፍል መማሪያ ማስታወሻ ሲሆን የተጠቀምኩባቸውም በእርሱ ፈቃድ ነው።) 

አዲስ ኪዳን ስለ ሁለቱ አገልግሎቶች ማለትም ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ላለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚያስተምረውን ትምህርት ግልጽ ለማድረግ በሁሉም የአዲስ ኪዳን ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ትምህርታችን ማየት አለብን። በመጀመሪያ አዲስ ኪዳን በአጠቃላይ የሚያስተምረውን በመመልክት እንጀምርና ቀጥሎ ለጰንጠቆስጤ የሥነ መለኮት ትምህርት ምንጭ በሆነው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ እናተኩራለን። 

ጥያቄ፡- የሚክተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። የሐዋ. 2፡42። 5፡24፤ 1ኛ ጢሞ. 4፡13፤ 2ኛ ጢሞ 3፡16። መጽሐፍ ቅዱስ ለምናምነውም ሆነ ለምናስተምረው ትምህርት ማዕከላዊ መሆን እንዳለበት እነዚህ ጥቅሶች እያንዳንዳቸው ምን ያስተምሩናል? 

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለይም በፍጥነት በምታድግ ቤተ ክርስቲያን እጅግ አደገኛ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ብዙ ክርስቲያኖች በእግዚአብሔር ቃል ጥልቅ መሠረት የሌላቸው መሆኑ ነው። እምነታቸውና ተግባራቸው የሚመነጨው ከእግዚአብሔር ቃል አይደለም። ነገር ግን ከባሕላቸው፥ ከቤተ ክርስቲያን ወግና ልምድ ወይም በቪዲዮ ከተመለከቱትና በቴፕሪኮርደር ከሰሙት ነው። 

ጥያቄ፡ ይህ ነገር በቤተ ክርስቲያን ሲፈጸም እንዴት እንዳየህ ግለጽ። 

ይህ በጣም አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው? በአዲስ ኪዳን በተደጋጋሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሐሰተኛ አስተማሪዎችና ሐሰተኛ ትምህርት እንደሚኖር ተነግሮናል (ለምሳሌ፡- የሐዋ. 20፡29-31)። የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት አብዛኛዎቹ የተጻፉት የተሳሳቱ አሳቦችንና የተሳሳቱ ትምህርቶችን ለመዋጋት ነው። ለምሳሌ– የገላትያ መጽሐፍ የተጻፈው የእይሁድ ሕጎችን በአሕዛብ ክርስቲያኖች ላይ ለመጫን የጣሩትን ለመዋጋት ነበር። 1ኛ ቆሮንቶስ የተጻፈው ክርስቲያኖችን በልሳናት ከመናገር ጋር የተያያዘውን ሐሰተኛ አካሄድ ጨምሮ የተለያዩ ኃጢአቶቻቸውን፥ የተሳሳቱ ትምህርቶቻቸውንና ልምምዳቸውን እንዲያስተካክሉ ለማቅናት ነበር። ጸሐፊዎቹ ስተው የሄዱትን ክርስቲያኖች ይመለሱና ይስተካክሉ ዘንድ ቸርነት የሞላበት ተግሳጽ የሰጡ ቢሆኑም፥ በግልጽና በድፍረት ለእውነት ቆመዋል። እውነትን ለፍቅር ብለው ለመለወጥ ፈቃደኛ አልነበሩም። (ፍቅርን ያጎድላላል ብለው እውነትን ከመናገር ዝም አላሉም።) ስምምነት ከመጣ በማለት ዛሬ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የማይመስል ነገርን ቢጠየቁ በዘመናችን የመጽሐፍ ቅዱሳቸውን ትምህርት እንደሚያቃልሉ እንደ ብዙዎች አይደለም። 

የወንጌልን እውነት ከመጠበቅ ይልቅ ከሌላው ክርስቲያን ጋር ወይም ከሌላው ቤተ ክርስቲያን ጋር ሰላምን መጠበቅ ይመርጣሉ። የቅናት መንፈስና ሌላውን ክርስቲያን በንግግር ማጥቃት ትክክል አይደለም። እውነትን ለማወቅና ትምህርቶችን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል እውነት መርምሮ መፈረጅ ግን እግዚአብሔር ከእኛ የሚጠብቀው ነገር ነው። የቤርያ ክርስቲያኖች የተመሰኑት ማናቸውንም አዲስ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማሙ መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ለመቀበል ፈቃደኞች ስላልነበሩ ነው (የሐዋ. 17፡11)። ማንኛውም ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል በተለየ መንገድ በመረዳቱ ከእኔ ጋር ባይስማማ ግድ የለኝም። በኢትዮጵያ ላለች ቤተ ክርስቲያን ችግሯ የሚመነጨው መጽሐፍ ቅዱስን ለእምነታቸው ዋና መለኪያ ለማድረግ፥ እና ሌሎች ደግሞ አዳዲስ እምነቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አኳያ እንዲመረምሩ ከማይፈቅዱ ሰዎች ነው። ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ሲመክረው «የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍር ሠራተኛ እንዲሆን ይነግረዋል (2ኛ ጢሞ 2፡15)። ይህን በአእምሮአችን አድርገን የሚቀጥሉትን ሦስት ቀናት ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀትና ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ምን እንደሚያስተምር ለማወቅ መጽሐፍ ቅዱስን እናጠናለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) አሳባቸው ወይም ልምምዶቻቸው በእግዚአብሔር ቃል ብርሃን እንዲመረመር የማይፈልጉ ሰዎችን በምሳሌነት ጥቀስ። ለ) ይህ አደገኛ የሚሆነው ለምንድን ነው? ሐህ ለእምነቶችና ለልምምዶች የእግዚአብሔር ቃል መመዘኛ የማይሆን ከሆነ ሌሎች ምን መመዘኛዎች ይኖራሉ? ሐህ እነዚህ መመዘኛዎች ምን ያህል አስተማማኝ ናቸው? 

የእኔ አመለካከት እምነታችሁ ላይ የሚያደርገውን ተጽእኖ ለመገደብ ስላ እነዚህ ሁለት የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች የሚናገሩ የአዲስ ኪዳን ዋና ዋና ክፍሎችን በጥንቃቄ በመመልክት ትጀምሩና አዲስ ኪዳን ስለ እነዚህ ጉዳዮች ምን እንደሚያስተምር ላራላችሁ ለመወሰን ትሞክራላችሁ። 

1. የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ማደር 

ጥያቄ፡– መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ስለመኖሩ የሚናገሩትን የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብብ። ዮሐ 7፡37-39፤ ሮሜ. 8፡9፤ 1ኛ ቆሮ. 6፡19፤ ቲቶ 3፡5-6። በእነዚህ ጥቅሶች በእያንዳንዳቸው፡- ሀ መንፈስ ቅዱስ ላላቸው ሁሉ ሊሰጣቸው ቃል የተገባላቸውን በረከቶች ዘርዝር። 2) ክእነዚህ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ለጥቂት ክርስቲያኖች ወይም ለሁሉም ላለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ? 3) እነዚህ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ ስለሌላው ሰው በግልጽ የሚናገሩት አሊያም የሚጠቁሙት ነገር ምንድን ነው? 4) መዝገበ ቃላት በቤትህ ካለ ስለ መንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ የማደር አገልግሎት ምን እንደሚል በአጭሩ አቅርብ። 

2. የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት 

ጥያቄ፡- በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ስለሚሆነው የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የተጻፉትን የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ማቴ. 3፡11፤ የሐዋ. 1፡5፤ 2፡1-4፤ 16-21፥ 33፥38-39፤ 11፡15-17፤ 1ኛ ቆሮ. 12፡13። ሀ) ለእነዚህ ጥቅሶች በሙሉ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ። ) እነዚህ ጥቅሶች ስለ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምን ይላሉ? 2) እነዚህ ጥቅሶች የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት መቼ እንደሚሆን ይናገራሉ? ሰው በሚድንበት ጊዜ ወይስ ከዳነ በኋላ? 3) በመንፈስ ቅዱስ የሚጠመቁ ክርስቲያኖች ሁሉ ናቸው ወይም አንዳንድ ክርስቲያኖች ብቻ? 4) የግሡን ጊዜ ልብ በል። ቃሉ የሚያመላክተው የወደፊትን፥ ያላፈን ወይስ ሁልጊዜ ተደጋግሞ የሚፈጸምን ድርጊት ነው? 5) የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ልናደርገው የታዘዝነው ነገር ነው ወይስ እንደ ስጦታ የተደረገልን ነገር ነው? ሊ አዲስ ኪዳን ስለ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ያለውን አመለካከት በአጭሩ ጻፍ። ህ የመንፈስ ቅዱስ ጥመቀት ዓላማ ምንድን ነው? 2) ጥምቀቱ የሚካሄደው መቼ ነው? 3) የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የሚቀበል ማን ነው? 4) የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀትን የምንቀበለው እንዴት ነው? 5) የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚረጋገጠው በምንድን ነው? የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማረጋገጥ ይህ ብቻ ነውን? አስረዳ። 6) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ካለህ ስላ መንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አገልግሎት ምን እንደሚል በአጭሩ ጻፍ። 

3. የመንፈስ ቅዱስ ሙላት 

ጥያቄ፡– መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያን ሕይወት ስላለው የሙላት አገልግሎት የሚናገሩትን የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። የሐዋ. 2፡11፤ 4፡8፣ 31፤ 9፡17፤ 13፡8–11፤ ኤፌ. 5፡8። ሀ) ለእያንዳንዱ ጥቅስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ። ህ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት እነዚህ ጥቅሶች ምን ይላሉ? 2) እነዚህ ጥቅሶች መንፈስ ቅዱስ የምንሞላው መኝ ነው ይላሉ? ሰው በሚድንበት ወቅት ወይስ ከዳነ በኋላ? 3) በመንፈስ ቅዱስ የሚሞሉ እንዳንድ ክርስቲያኖች ናቸው ወይስ ሁሉም? 4) የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (አገልግሎት በክርስቲያን ሕይወት እንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም ወይስ በተደጋጋሚ የሚሆን ነው? ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ብቸኛ የሚናገረውን የግሥ ጊዜ ስታጤን፥ የሚያመለክተው የወደፊት፥ ያላፈ ወይስ ተደጋጋሚ ድርጊትን ነው? 6) በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ ታዘናል ወይስ እንዲሁ የሚደረግልን ነገር ነው? 

ለ. አዲስ ኪዳን ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ስለሚያገኝበት ሁኔታ በሚያስተምረው ትምህርት ላይ ያለህን አመለካከት አጠር አድርገህ ጻፍ። ) የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ዓላማ ምንድን ነው? 2) ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን የሚሞላው መቼ ነው? 3) የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን ማን ይቀበላል? 4) ሰዎች የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን የሚቀበሉት እንዴት ነው? 5) የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚረጋገጠው እንዴት ነው? ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ማረጋገጥ ነውን? 6) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በቤትህ ካለ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት አንብብና የተረዳኸውን አሳጥረህ ጻፍ። 

ጥያቄ፡- የመንፈስ ቅዱስን በሰው ልብ ማደር፥ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀኛንና የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን አወዳድር። ሀ) ተመሳሳይ የሆኑት እንዴት ነው? ለ) የሚለያዩትስ እንዴት ነው? ሐህ በእያንዳንዳቸው መካከል ያለውን ልዩነት በአንድ ዐረፍተ ነገር አጣቃለህ ጻፍ። 

ቃላት ልዩ ነገሮች ናቸው። ዘወትር የምንጠቀምባቸው ሊሆኑ ያሉንን አሳቦች ለሌሎች ለማካፈል የምንጠቀምባቸው ዋነኛ መንገድ ናቸው። ሆኖም ግን ቃላት ጠቃሚ የሚሆኑት በምንጠቀምባቸው ጊዜ በትርጉማቸው የምንስማማ ከሆነ ነው። የሚናገሩት ነገር ለሌሎች ሰዎች የሚገባቸው እየመሰላቸው ብዙ ጊዜ አንድ ቃልን ይጠቀማሉ። ነገር ግን ሌሎች ሰዎች ስለ ቃሉ ያላቸው መረዳት ሙሉ በሙሉ የተለየ ስለሆነ ወደ አድማጮቹ የሚደርሰው ተናጋሪዎች ሊሉት የሚፈልጉት ነገር አይደለም። ስለዚህ አንድን ነገር በግልጽ ለማስረዳት ከፈለግን የሚሰሙን ሁሉ የምንጠቀምበትን ቃል ባሰብነው መንገድ መረዳታቸውን ማረጋገጥ አለብን። 

ብዙ ክርስቲያኖች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሉ እውነቶች ሲከራከሩ የሚከራክሩበት ዋና ምክንያት ለአንድ ቃል የተለያየ ትርጉም በመስጠታቸው ነው። ለምሳሌ «የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት» የሚለውን ቃል ውሰዱ። ካሪዝማቲክ የሆኑ ክርስቲያኖች የሚሰጡት ትርጉምና ካሪዝማቲክ ያልሆኑት ክርስቲያኖች የሚሰጡት ትርጉም ይለያያል። ካሪዝማቲክ የሆኑ ክርስቲያኖች «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት» ብለው የሚጠሩት ልምምድ ካሪዝማቲክ ባልሆኑ መካከል «የመንፈስ ቅዱስ ሙላት» የሚባለው ነው። 

ስለ አንድ ነገር እየተስማማን የተለያዩ ቃላት በመጠቀማችን ብቻ ከመከራከር ይልቅ በእርግጥ አሳባችን የተለያየ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። ይህንን ለማድረግ አንዳንድ ቃሎችን ወይም ሐረጎችን ስንጠቀም የምንለውን ነገር ስለ መረዳታችን እርግጠኞች መሆን አለብን። 

ጥያቄ፡- ሀ) በሁለት ሁኔታዎች ውስጥ የተለያዩ ትርጉሞች ስለሚኖሩት ቃል ግላጽ። ለ) ለአንተ አንድ ዓይነት መረዳት፥ ለሌላው ደግሞ የተለየ ግንዛቤ መስጠቱን ስለምታስታውሰው የሆነ ሰው አለተናገረው ቃል ሁኔታ ግለጽ። 

ማብራራት የሚገባን፥ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ” ስት ሐረጎች ወይም አሳቦች አሉ። የመጀመሪያው «የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ ማደር»፥ ሁለተኛው «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት» ሲሆን፥ ሦስተኛው ደግሞ «የመንፈስ ቅዱስ ሙላት» ነው። እነዚህን ሐረጎች በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሙሉ በመከታተል አዲስ ኪዳን ስለ እነርሱ ምን እንደሚያስተምር እንመለከታለን።  

1. የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ ማደር 

የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ ማደር መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የመኖሩን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የሚገልጥ ነው። እብዛኛዎቹ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖችና ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች አንድ ሰው ክርስቶስን አምኖ በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሆነ መንገድ ሰውዩው ውስጥ ለመኖር እንደሚመጣ ይስማማሉ (የትምህርት 6ን ሁለተኛ ቀን ትምህርት ተመልከት)። በዮሐ 37-39፤ በሮሜ 8፡9 ኛ ቆሮ. 6፡19 እና በቲቶ 3፡5-6 ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መረጃዎች መንፈስ ቅዱስ በሆነ መንገድ በእያንዳንዱ ክርስቲያን ሕይወት ለመኖር እንደሚመጣ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ካሪዝማቲክ የሆኑ ክርስቲያኖች ያልሆኑት መንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ ስለሚያድርበት ሁኔታ ሁለት አሳብ ይዘው ይለያያሉ። 

ሀ. አብዛኛዎቹ የካሪዝማቲክ ክርስቲያኖችና አንዳንድ ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች አንድ ክርስቲያን ከባድ ኃጢአትን ሲያደርግ መንፈስ ቅዱስ ትቶት ይሄድና በውጤቱም ደኅንነቱን ሊያጣ ይችላል ብለው ያስተምራሉ። መንፈስ ቅዱስን ከሕይወታችን የሚያስወጡ ኃጢአቶች በየጊዜው የምንፈጽማቸው ጥቃቅን ኃጢአቶች ሳይሆኑ፥ እንደ ነፍስ ማጥፋት፥ ምንዝርናና ኢየሱስን መካድ የመሳሰሉት እንደሆኑ ይናገራሉ። አብዛኛዎቹ ካሪዝማቲክ ያልሆኑ ክርስቲያኖች ግን አንድ ሰው በእውነት ከዳነና መንፈስ ቅዱስ በልቡ የሚኖር ከሆነ ደኅንነቱንም ሆነ የመንፈስ ቅዱስ ህልውናን ከሕይወቱ ሊያጣ አይችልም ይላሉ። አንድ ሰው ከዳነ ደኅንነቱ ለዘላለም የተጠበቀ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው በእርግጥ የሚያድን እምነት ያለው መሆኑን ወይም ድኛለሁ ብቻ የሚል መሆኑን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው ይላሉ። 

ለ. ካሪዝማቲክ የሆኑና ያልሆኑ ክርስቲያኖች የሚለያዩበት ሌላው መንገድ አንድ ሰው በዳነበት ጊዜና ከዳነ በኋላ በሕይወቱ የሚፈጸመውን የመንፈስ ቅዱስ እገልግሎት አስመልክቶ ነው። ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች አንድ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ መንፈሳዊ ሕይወት የሚያደርስ ልዩ የሆነ ሁለተኛ በረከት ወይም የመንፈስ ቅዱስ ሁለተኛ ተግባር አለ ብለው ያስተምራሉ። ለምሳሌ ብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች አንድን ሰው ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብነት የሚያስገባበት (ገላ 4፡5፤ ሮሜ 8፡23)፥ ወይም በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስን የማተምና በመያዣነት የማስቀመጥ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት (2ኛ ቆሮ. 1፡22፤ ኤፌ. 1፡13-14፤ 4፡30) የሚፈጸመው ሰው በሚድንበት ጊዜ ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ሁለተኛ ሥራ አካል ነው። 

ሆኖም ግን እነዚህን ጥቅሶች አንድ በአንድ ስንመረምር እዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ለአንዳንድ ክርስቲያኖች ብቻ ስለመሰጠታቸው የትኞቹም አይናገሩም። ማስረጃ ው የበለጠ የሚያስረዳው ይህ አገልግሎት ለሁሉም ክርስቲያኖች መሰጠቱን ነው። የተጠናቀቁና የኃላፊ ጊዜ ሥራዎች እንደሆኑም ይታያል። ስለዚህ እነዚህ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች (በትምህርት ስድስት ያጠናናቸው በሙሉ) ለክርስቲያኖች ሁሉ ባመኑበት ቅጽበት የተፈጸሙ ናቸው ብሎ መገመቱ ያዋጣል። 

(ማስታወሻ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ወደ ሰው ሕይወት የሚመጣው በጥምቀት የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ ታስተምራላች። ሕፃኑ ከተጠመቀ በኋላ ካህኑ ወዲያውኑ ሕፃኑን ዘይት በመቀባት እፍ ይልበታል። ይህም የመንፈስ ቅዱስን በእርሱ ላይ መምጣት ያሳያል። በጥምቀት አማካኝነት የሚሰጠውን አዲስ ሕይወት 

መንፈስ ቅዱስ ያረጋግጥልናል። ይህ ሂደት ቅብዓ ቅዱስ በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም የመቀባቱ ተግባር የሚካሄደው በተቀደሰ ዘይት ስለሆነ ነው። ይህ የኦርቶዶክስ መሠረታዊ የእምነት ትምህርት ጋር የተቆራኘ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ላኛው ጥያቄ የሰጠኸውን መልስ ከላይ ከተሰጠው መልስ ጋር አወዳድር። ምን ያህል ተመሳሳይ ነው? ምን ያህልስ ይለያያል? ለ) መልሶችህን አሁን እንዴት ትከልሳቸዋለህ?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: