የብሉይ ኪዳን ነቢያት መሢሑ የሚመጣበትን ወቅትና የመንፈስ ቅዱስ አገልግሉት የሚለወጥበትን ጊዜ እስቀድመው አመልክተው ነበር

ጥያቄ፡ ኢሳ 1-5፤ 42፡1-4፤ 61፡1-3 አንብብ። ሀ) እነዚህ ጥቅሶች በሚመጣው መሣሕ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን እንደሆነ ያስተምሩናል? ለ) ይህ አገልግሎት በኢየሱስ የተፈጸመው እንዴት ነበር? ኢሳ 44፡3፤ 59፡21 ሕዝ 11፡9፤ 36፡27 ና 37፡14፤ 39፡29፤ ኢዩ፤ 2፡28-29። ሐ) እዚህ ጥቅሶች ስለ መጨረሻዎቹ ቀናት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ምን ያላተምሩናል? 

የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት በብሉይ ኪዳን ዘመን ታላቅ እንደነበር ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የሚለወጥበት አዲስ ዘመን እንደሚመጣም ነቢያት ተገንዝበው ነበር። በመጀመሪያ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ልዩ ግንኙነት ያለው ሰው እንደሚመጣ ነበር። ይህ ሰው ከዳዊት ዘር የሚመጣው ንጉሥ መሢሑ ነበር (ኢሳ. 11፡23 42፡1)። ላለ መሢሑ በተነገረበት በእነዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ተቀዳሚ ትኩረት እግዚአብሔርን በሚያስከበር መንገድ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንዲመራ መሢሑን በማስቻል ላይ ነበር። ከሌሎች መሪዎች በተለየ መንገድ በጥበብና በእውቀት የተሞላ ሆኖ ጌታን በመፍራት ይኖራል። በምድር ላይ ጽድቅን ያመጣል። የታሠሩትን ነፃ ሚያወጣና ልባቸው የተሠበረባቸውን የሚፈውስ የምሥራች ቃል ይሰብካል። 

ሁለተኛ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ለሁሉም የሚዳረስ ስለመሆኑ ነበር። በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ያለውን በእግዚአብሔር ላይ የማመጽ ዝንባሌ ማለትም የድንጋዩን ልብ ይወለድና በሚታዘዝ ልብ ይቀይራል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል በሕዝቡ ፊት ያላማቋረጥ እንዲገኝ ያደርጋል። መንፈስ ቅዱስ ልዩ አገልግሎት በሚሰጡ በጥቂት ነቢያትና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ብቻ መሆኑ ይቀርና የዕድሜና የዘር ልዩነት ሳያደርግ አሕዛብም ሲሆኑ አይሁድ በሁሉም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ላይ ይወርዳል። በእነዚህ ምርጥ ሰዎች ላይ ለተወሰነ ጊዜ ይወርድ እንደነበረው ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሰዎች ሕይወት ውስጥ ይኖራል። የትንቢት ስጦታ ለፖለቲካ መሪዎች ወይም ነቢያት ብቻ የሚታደል መሆኑ ቀርቶ ይህ ለመንፈስ ቅዱስ ህውና ምልክት (ማስረጃ ) የሆነው ስጦታ ለሰዎች ሁሉ ይሰጣል። 

ጥያቄ፡- መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን የሰጠውን አገልግሎት ክልስ። ሀ) በዚያ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ሚና ምን ይመስል ነበር? ላ) ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከሚሠራባቸው መንገዶች ጋር ምን ተመሳሳይነት [አላው? ሐ) ዛሬ መንፈስ ቅዱስ ከሚሠራባቸው መንገዶች ጋር ልዩነቶቹስ ምን ምን ናቸው? መ) ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ስላለን ንኙነት በብሉይ ኪዳን ከነበረው አገልግሎቱ ልንማራቸው የምንችላቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው? 

ብዙ ጊዜ ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ስናስብ አንዳንድ ጊዜ ከሚያደርጋቸው ድንቅ ነገሮች አኳያ ብቻ እንመለከተዋለን፤ ወይም በአንድ የአገልግሎት ገጽታው ላይ ብቻ በማተኮር ስለ መንፈስ ቅዱስ ያለን ሥነ መለኮታዊ መረዳት ሚዛናዊነትን ያጣል። መንፈስ ቅዱስ ግን መጠነ-ሰፊ በሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ይሠራል። ከእዚህም ብዙዎቹ የማይታዩና በሚሩጸሙበት ጊዜ እንኳ የማናስተውላቸው ናቸው። የሕይውት መገኝትም ሆነ ዘላቂነቱ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተደገፈ ነው። እግዚአብሔር ሕይወታችንን የሚያስተምርበትም ሆነ የሚመራበት አገልግሎት በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው። በብሉይ ኪዳን የምንመለከተው የመንፈስ ቅዱስ ተቀጻሚ አገልግሎት ቀን እግዚአብሔር የመረጣቸው መሪዎች ሕዝቡን እንዲመሩ ማድረግ ነበር። ይህ ችሎታ አንዳንድ ጊዜ እንደ ሳምሶን ብርታትና እንደ ሳኦል ትንቢት ተአምራዊ ተግባራትን ያካተተ ቢሆንም ብዙ ጊዜ ግን የመንፈስ ቅዱስ ህልውና የሚታየው በመሪዎች ጥበባዊ አመራር፥ ከጠላት የመታደግና ሕዝቡን በእግዚአብሔር ፊት የተቀደሰ ኑሮ እንዲኖሩ በማስቻል በማድረግ) ችሎታቸው ውስጥ ነው። 

የብሉይ ኪዳን ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር ለሕዝቡ አዲስ ሥራን ሲሠራ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል የሠራበትን መንገድ እንደሚለውጥ ተነግሮናል። አገልግሎቱ ምን ይመስል ነበር? በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ዘመናት መካከል ያለው ልዩነት ምን ይሆናል? በሚቀጥለው ሳምንት መንፈስ ቅዱስ በወንጌላት ውስጥ ስለ ሰጠው አገልግሎት በተለይ ደግሞ በኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ውስጥ ስለነበረው አገልግሎት እንመለከታለን።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.