የጰንጠቆስጤና የአንዳንድ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ዋና ትምህርቶች ምን ምን ናቸው?

1. ማንኛውም ክርስቲያን ልምምድ ውስጥ ሁለት ደረጃዎች አሉ። የመጀመሪያው፥ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝ መቀበል ነው። አብዛኛዎቹ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የመጀመሪያው ደረጃ ሰውን ክርስቲያን ያደርገዋል በማለት ያስተምራሉ። አብዛኛዎቹ እንደሚያስተምሩት መንፈስ ቅዱስ በዚህ ጊዜ በተወሰነ ደረጃ በዚያ ሰው ሕይወት ውስጥ ያድራል። ይህ አንዳንድ ጊዜ «ለድነት (ደኅንነት) በመንፈስ መወለድ» ተብሎ ይጠራል። ሆኖም ቀን ይህ የመጀመሪያ ደረጃ የተሟላ አይደለም በማለት ያስተምራሉ። 

ሁለተኛው ደረጃ ፥ «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት» ሲሆን፥ ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ ለአንዴና ለመጨረሻ በሆነ መንገድ በኃይል በመምጣት ለአገልግሎት ይቀባዋል ማለት ነው። ይህ ድርጊት በበርካታ የተለያዩ ስሞች የተጠራ ሲሆን አንዳንዶች በመንፈስ መሞላት ይሉታል። ሌሎች ደግሞ «የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ» ይሉታል። በአንድ ወቅት «በመንፈስ መቀባት» ተብሎ ተጠርቷል። መንፈስ ቅዱስ ወደ አንድ ሰው ሕይወት የመምጣቱ ዋና ምልክት በልሳን መናገር ነው። የመንፈስ ቅዱስ ህልውና በልሳናት በመናገር የሚረጋገጥ ቢሆንም የመንፈስ ቅዱስ ተቀዳሚ ዓላማ ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር መኖር ይችሉ ዘንድ በኃይል ማስታጠቅ ነው። ለአንዳንድ ክርስቲያኖች ይህ ድርጊት ልክ በሚድኑበት ቅጽበት የሚፈጸም ቢሆንም ብዙ ጊዜ ግን ከዳኑ በኋላ የሚፈጸም ነው። (ማስታወሻ፡- በአሁኑ ወቅት በልሳን መናገር ለሁሉም ክርስቲያኖች የግድ መሰጠት ያለበት ስጦታ እንዳልሆነ የሚያምኑ የበሰሉ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ቢኖሩም በልሳናት የመናገር እስፈላጊነት የብዙ ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች የተለመደ ትምህርት ነው)። 

2. መንፈስ ቅዱስ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመኖሩ ክስተት በ1ኛ ቆሮ 12፡8-10 በተዘረዘሩት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች የሚረጋገጥ ነው ይላሉ። የቤተ ክርስቲያን ጤናማ ሕይወት እንደ ፈውስ ተአምራትና መገለጥ በመሳሰሉ ነገሮች መረጋገጥ አለበት። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህንን ትምህርት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ከተሞች በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሲሰጥ ያየኻው እንዴት ነው? ለ) ከዚህ ትምህርትና እንቅስቃሴ ለአብያተ ክርስቲያናት የወጡ መልካም ናቸው ብላህ የምታስባቸውን ነገሮች ዘርዝር። ሐ) የዚህ አዲስ እንቅስቃሴ ትምህርቶች ነባቤተ ክርስቲያን ያስከትላሉ የምትላቸው ስጋቶች ምን ምን ናቸው? 

ጰንጠቆስጤ ወይም ካሪዝማቲክ ያልሆኑ አብያተ ክርስቲያናት «የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት» አንድ ሰው በክርስቶስ አምኖ በሚድንበት ወቅት ወዲያውኑ የሚፈጸምና አማኙን ወደ ክርስቶስ አካል የሚጨምር ድርጊት እንደሆነ ያስተምራሉ። ሰው በሚድንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በልቡ ውስጥ መኖር መጀመሩና የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በአንድነት የሚከናወኑ ናቸው። ከዚህ ሌላ ካሪዝማቲክ ያልሆኑት በልሳናት የመናገርና ተአምራታዊ የመንፈስ ቅቶለ ስጦታዎች ሚና ላይ ልዩነት ያሳያሉ። አንዳንዶቹ እነዚህ ስጦታዎች ለመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ብቻ የነበሩ፥ ሐዋርያት ሊሞቱና አዲስ ኪን ሲፈጸም ቀርተዋል ብለው ያምናሉ (1ኛ ቆሮ. 13፡8 ተመልከት)። ሌሎች ደግሞ እዚህ ለጦታዎች ዛሬም ቢሆን ለክርስቲያኖች ይሠራሉ ይላሉ። ነገር ን በልሳናት መናገር ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አንደኛው ብቻ ነው። በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሱት ከሌሎች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በተለየ ሁኔታ ለመንፈስ ቅዱስ ህልውና ማስረጃ አይሆንም። ካሪዝማቲክ ያልሆኑት ክፍሎች ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ይልቅ በገላ. 5፡22 ላይ በተጻፉት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ላይ ያተኩራሉ። ካሪዝማቲክ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት በመንፈስ ቅዱስ በማምለክ ላይ ሲያተኩሩ፥ ካሪዝማቲክ ያልሆኑት የእግዚአብሔርን ቃል በማወቅና በእርሱ በመኖር ላይ ያተኩራሉ። ካሪዝማቲክ ያልሆኑትን አብያተ ክርስቲያናት ለካሪዝማቲኮች የሚያስጨንቃቸው ነገር የትምህርታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እነስተኛ መሆን ነው። 

ካሪዝማቲክ የሆኑትም ሆነ ያልሆኑት በታማኝነት እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንደሚናፍቁ መገንዘብ አስፈላጊ ነው። አንዱ ከሌላው የሚያንስ ወይም የሚበልጥ መንፈሳዊ የመሆን ጉዳይ አይደለም። ይልቁኑ ጉዳዩ ሁለቱም ቡድኖች የተለያዩ የሥነ መለኮት አመለካከት፥ በተለየ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት፥ በተለይ ደግሞ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለሚኖረው ኅብረት የተለየ አመለካከት አላቸው ማለት ነው። እውነታውን ከተመለከትን አንዱ ቡድን ሌላውን የሚያስተምረው በርካታ ነገር አለው። ሁለቱም ቡድኖች ሚዛናቸውን በመጠበቅ ትልቅ ችግሮች ውስጥ እንዳይወድቁ እርስ በርስ መጠባበቅ ይችላሉ። ካሪዝማቲክ ክርስቲያኖች ልምምጻቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው ትምህርት ጋር ጎን ለጎን ለማስኬድ ይችሉ ዘንድ እምነቶቻቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ላይ ለማድረግ ማተኮር አለባቸው። ካሪዝማቲክ ያልሆኑት ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን ሕያው በሆነ መንገድ በመለማመድ እግዚአብሔርን በማምለክ ከተራ የሃይማኖት ሥርዓት እንዲድኑ በዚህ አቅጣጫ አትኩሮት ማድረግ አለባቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ከእነዚህ ሁለት የሥነ መለኮት ትምህርት ቡድኖች የትኛው ውስጥ ትካተታለህ? ይህ የሆነው ለምን ይመስልሃል? ለ) ሁለቱም ቡድኖች በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ እድገት ውስጥ ሚዛናዊ የሆነ ነገር እንዲኖር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉበትን መንገድ በምን ሁኔታ ታየዋለህ?

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.